Tuesday, September 15, 2015

ሞላ አስገዶም አዲስ አበባ መግለጫ ሲሰጡ የተጻፈላቸውን ደጋግመው ሲያነቡና ሲደናገሩ ተስተዋሉ ፣የአገዛዙ የማጥላላት ቅስቀሳ ኤርትራ ለሚገኙት የነጻነት ተዋጊዎች ያልተጠበቀ የሕዝብ ግንኙነት ስራ ማስገኘቱ ተገለጸ

Molla_first_araival_second_drama_etv_02

ከኤርትራ ከድተው በሱዳን በኩል አዲስ አበባ የገቡትና የቀድሞው የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ትህዴን) ሊቀመንበር ታጋይ ሞላ አስገዶም ዛሬ በአዲስ አበባ የህወሓት-ኢህአዴግ አገዛዝ ደህንነት ያዘጋጀላቸውን ጋዜጣዊ መግለቻ በሰጡበት ወቅት ተረጋግተው ሳይሆን የሚናገሩት የተቆራረጠ አረፍተ ነገር ደጋግመው ተጽፎ የተሰጣቸውንና በኤርትራ ያለውን የነጻነት ትግል በተለይም ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን ደጋግመው ላማጥላላት ሲሞክሩ ተስተውሏል።

ለአገዛዙ የተለያዩ የፓርቲና በመንግስት ስም የሚንቀሳቀሱ መገናኛ ብዙሃን በተዘጋጀላቸው ጋዜጣዊ መግለቻ አስቀድሞ በደህንነቱ ባለስልጣናት ተጽፎ የተሰጣቸውን ወረቀት ደጋግመው ሲያነቡ በርካታ ቦታዎች ላይ አንዱን ጉዳይ ሳይጨርሱ ሳይጠየቁ ጭምር ሌላውን ለማብራራት ሲሞክሩ የተቆራረጠ አረፍተ ነገር ሲናገሩ ላያቸው የሰውዬው መደናገርና ተፅፎ ከተሰጣቸው ላለመውታት የሚያደርጉትን ጥረት አሳያል ሲሉ ከመግለጫው በሁዋላ ዩህብር ምንጮች ከአዲስ አበባ ገለጹ።
<<ደጋግሞ በመዋሸቱ የማይታመን ስርዓት ሞላን ጭኖ ቢአናግር የሚሰማው የለም>> የሚሉት እነዚህ ምንጮቻችን ከዚያ ቀደም ሰው ፈራ ተባ እያለ ውስጥ ውስጡን የሚያወራበትንና በአገር ቤት ሰፊ መነቃቃት የፈጠረበትን የዶ/ር ብርሃኑ በአካል ትግሉን ለመምራት መሄድ ለስርዓቱ ትልቅ ስጋት የፈጠረበት እንደነበር የሰሞኑ የመግለቻ ጋጋታ አሳያል ብለዋል።
ከኤርትራ ሞላ አስገዶም ሳያውቁት ጭምር ይዟቸው የገባው ወታደሮች ቁጥር በሰሞኑ የአገዛዙ ሚዲአዎች በየቀኑ ሲጨመር መቆየቱን የጠቀሱት እነዚሁ ምንጮች ዕሁድ እለት ፋና ራዲዮ ከሰባት ሞቶ በላይ ወታደሮች ተከትለዋቸው ገቡ ያለውን በማግስቱ ራሱ ይሄው ራዲዮ ከስምንት ሞቶ በላይ ሲል ቁጥሩን በአንድ ቀን ጨምሮት አደረ ሲሆን በቀድሞ ስሙ ኢቲቪ ተመሳሳይ የተምታታ ቁጥር ማቅረባቸው በሕዝቡ መካከል የቀልድ ምንጭ እየሆነ <<ምርጫ ቦርድ እንዳይሆን ወታደሮቹን የቆጠራቸው >> የሚል ቀልድ ጭምር መደመጥ መጀመሩን ምንጮቻችን ገልጸዋል።
የስርዓቱ ከዱትን ሞላ አስገዶምን አስመልክቶ የቀረበው የዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫቸውም ሆነ የሰሞኑ ቅስቀሳ ከኤርትራ ያሉትን የነጻነት ተዋጊዎች ከዚህ ቀደም ጦርነት ማድረግ አቅም ሌላቸው ሰላሳዎቹን ደመሰስካቸው እንዳላለ በኢትዮጵያ ላይ ጥፋት ለማድረስ የተዘጋጀው ሀይልን ይዘው ገቡ ሲል ለነጻነት ተዋጊዎቹ ያልተጠበቀ የሕዝብ ግንኙነት ስራ ራሱ ስርኣቱ እየሰራ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ቀድሞው ታጋይ ሞላ አስገዶም በኤርትራ የሚገኘውና ከ24 ሺህ በላይ የነጻነት ተዋጊዎች እንዳሉት ከሚነገረው የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትህዴን) ራሳቸውን ጨምረው የተወሰኑ ወታደሮችን በማሳሳት በስምንት ላንድ ክሩዘር ከድተው ወደ ሱዳን መግባታቸውን ህብር ሬዲዮ ባለፈው ዕሁድ ከኤርትራ ያሉ ምንጮቻችንን ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል። ድርጅቱ ካሉት ዘጠኝ ከፍተኛ የንቅናቄው ስራ አስፈጻሚ መካከል ሞላና አንድ ሰው ሲከዱ ሰባቱ ከፍተና አመራሮች አሁንም ድርጅቱን እየመሩ መሆኑን ለማወቅ ተችላል። ቀደም ሲል ድርጅቱ አመራሮች ሰባት የሚል ዘገባ ያወታን ቢሆንም ዘግይቶ መደረሰን መረጃ ከዘጠኙ አመራሮች ሊቀመንበሩ የቀድሞው ታጋይ ሞላና አንድ ሌላ የስራ አስፈጻሚ አባል ከከዱት መካከል የሚገኙ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ሞላ በዛሬው መግለቻ ከኤርትራ ሲመጡ የሻዕቢአን ወታደር ጠራርገን፣ የተወሰኑ ቆሰሉብን ይበሉ እንጂ የቆሰሉት እነማንና ምን ያህል እንደሆኑ እንደማይታወቅ፣ ደመሰስን ያሏቸውን የሻዕቢያ ጦር ምን ያህል እንደሆኑ ሳይገልጹ ቀርተዋል። የከዱት ድርጅታቸው ትህዴን የግለሰቦች መክዳት ትግሉን አያቆመውም ነግል ጥቅም እና ግለሰባዊ ባህሪ የተወሰደ እርምጃ ነው ትግላችንን አያቆመውም ሲል መግለቻ ሰጥቷል። አርበኞች ግንቦት ሰባት በበኩሉ ባወጣው መግለጫ የትህዴንን መግለጫ የደገፈ ሲሆን የወያኔ አገዛዝ የከዱትን ሞላ አስቀድመው አብረውኝ ይሰሩ ነበር ማለቱን አገዛዙ ለራሱ ሞራል የሚአወራው ሀሰተኛ መረጃ መሆኑን በመግለጽ ትግሉን የግለሰቦች መክዳት የማያቆመው መሆኑን ጠቅሷል።
ትህዴን በቅርቡ የተመሰረተውን አገር አድን ግብረ ሀይል የበለጠ እንደሚያጠናክር የገለጸ ሲሆን በቅርቡ ሊቀመንበሩን ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል።
የህብር ሬዲዮን ዘገባ ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችን በተጨማሪ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው። በእንግሊዝ ለምትኖሩበ01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችን ወይም ከgoogel store Hiber radio አፕሊኬሽንን ዳውን ሎድ በማድረግና  ከዘሐበሻም ማዳመጥ ይቻላል።

No comments:

Post a Comment