Wednesday, September 16, 2015

voa

የቀድሞ የህወሃት ሊቀመንበር ማብራሪያ ዶ/ር አረጋዊ በርኸ ስለ ሞላ አስገዶምና ትሕዴን ሁኔታ ለVOA ትንተና ሰጡ


የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ መሪ አቶ ሞላ አስገዶም ብዛታቸው በመቶዎች የተቆጠረ የድርጅቱን ታጣቂዎች ይዘው ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ድርጅቱን “ከመጉዳት ይልቅ ያጠናክረዋል” ብለዋል የቀድሞ የሕወሓት ታጋይ ዶ/ር አረጋዊ በርኸ ለቪኦኤ በሰጡት የሰሞኑ ሁኔታ ትንተና፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ከወጡት መካከል አሁንም ሱዳን ውስጥ ያሉትን ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የትሕዴን ምክትል ሊቀመንበር አቶ መኮንን ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡ የሱዳን ባለሥልጣናት ከስድስት መቶ ከሚበልጡ ታጣቂዎች ላይ ትጥቅ መረከባቸውን ሱዳን ትሪቡን የሚባለው የኢንተርኔት ጋዜጣ አመልክቷል፡፡ ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ → 

No comments:

Post a Comment