Monday, September 14, 2015

የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ትህዴን መግለጪያ ሰጥቷል።

መሳይ መኮንን
የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ትህዴን መግለጪያ ሰጥቷል።
''ትህዴን ይዞት የተነሳ ዓላማ የመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ፍላጎት ስለሆነ ሊቅበለውም ውይም ላይቅበለውም የሚችለው ህዝብ እንጂ ግለሰቦች አይደሉም። ትግላችን ደግሞ በሃገራችን ያለውን ፀረህዝብ ስርዓት ከስልጣኑ ተወግዶ ህዝባችን የጀመረውን የትጥቅ ትግል ግቡን ሳይመታ ለአፍታም ቢሆን አይቆምም።'' ብሏል ትህዴን
በዓል ለማክበር ነው ተብለው በሞላ የተወሰዱትና አሁን በህወሀት እጅ የወደቁት ታጋዮች የአፈና ተግባር ተፈጽሞባቸዋል። Molla kidnapped his fighters
ከታች በፎቶግራፉ የምትመለከቱት የትህዴን የኪነት ቡድን አባላት በጉዞ ላይ እያሉ መንገድ ላይ ሲያዙ ያሉት ነገር ቢኖር ይሄንኑ ነው ........''ተጋዳላይ ሞላ በዓል አለ ብሎ ጠርቶን ነው።'' ምንም የሚያውቁት ነገር የለም። ገቡ የተባሉትም እንደዚያው።
ትህዴን ከ20ሺህ በላይ ሰራዊቱን ይዞ ከሀገር አድን ንቅናቄው ጋር ለመስራት የሚያስችለውን ሂደት እንደቀጠለ ከወደ አስመራ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። ሀገር አድን ንቅናቄውም መግለጪያ ያወጣል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚያው ያነጋገርኳቸው አንድ የንቅናቄው አመራር እንዳሉኝ ትግሉ ማርሹን ቀይሯል። የማንቂያ ደውሉ በሚገባ ተሰምቷል።


No comments:

Post a Comment