ለአቡነ ጴጥሮስን ክብር የተቀመጠው ታሪካዊ ሃውልት ለባቡር መንገድ እንቅፋት ሆነ ተብሎ ሲነሳ መንገዱ ተስርቶ ሲያልቅ በቦታው እንደሚመለስ ተገልፆ ነበር ። ሆኖም ግን ዛሬ ያ መንገድ ተስርቶ አልቆ ግልጋሎት ላይ እየዋለ ሲሆን የአቡናችን ሃውልት ግን በክብር በቦታው አልተቀመጠም ።
አቡነ ጴጥሮስ ቅርሳችን ታሪካችን ናቸው ። ለውጭ ወራሪ እጅ አልሰጥም ሲሉ የኢትዮጵያ ህዝብ እጅ አይሰጥም ማለታቸው ነው ። የአቡነ ታሪክ በተወሳ ቁጥር ፋሽሽት ጣልያን አንገቱን በእፍረት የሚደፋበት ነው ። እና እኝህን ትልቅ አባታችንን ከፊታችን ሲያገሉብን ለምን ብለን አንጠይቅም ? መቼ ነው ግን እኛ ለምን እና እንዴት ብለንስ የምንጠይቀው ? ብዙ የጠፋ ነገሮችን ለግዜው ዋይ ዋይ ብለን የዘነጋናቸው አሉ እና ብንችል የአባታችን የአቡነ ጴጥሮስን ሃውልት በቦታው በክብር ለማስቀመጥ እንሞክር ። ዝም ከማለት የሚገኝ ወይም የሚመጣ ነገር የለም ። እኛም የፋሽሽትን ፍላጎት በማወቅም ሆነ ባለማወቅ አናስፈጽም።
No comments:
Post a Comment