Saturday, September 26, 2015

አርበኞች ግንቦት7ን ለመቀላቀል ጥያቄ የሚያቀርበው ህዝብ ቁጥር ጨምሯል

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከድርጅቱ በተገኘው መረጃ መሰረት በቀን ውስጥ ወደ ንቅናቄው ከሚደውሉ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ስልኮች መካከል 80 በመቶው ፣ ንቅናቄውን ለመቀላቀል መረጃ የሚፈልጉ ሰዎች ናቸው። በሁለተኛ ደረጃ የሚመጣው ደግሞ የማበረታቻ ሃሳቦችን ለመስጠት የሚፈልጉ ሰዎች ሲሆኑ፣ 2 በመቶ የሚሆነው ደግሞ መረጃ ለመስጠት የሚፈልገው ነው። የድርጅቱ የስልክ መረጃ አያያዝ እንደሚያመለክተው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ለድርጅቱ የሚደወሉ ስልኮች በእጥፍ ጨምሯል። ምንም እንኳ አብዛኛውን ጥሪ የሚያደርጉት ወጣት ወንዶች ቢሆንም፣ ጎልማሶችና ሴቶችም ይገኙበታል ሲል የመረጃ ክፍሉ ለኢሳት ገልጿል። ድርጀቱ ትግሉን እንቀላቀል ለሚሉት ሃይሎች " በአገር ውስጥ ሆነው ራሳቸውን እንዲያደራጁ ምክር እንደሚሰጥ " የገለጸ ሲሆን፣ ሁኔታዎችን ላመቻቹ ወጣቶች ደግሞ ጉዞአቸውን በምን መንገድ ማድረግ እንዳለባቸው እንደሚገልጽላቸው ገልጿል። የደሚት ሊቀመንበር ሞላ አስጎደም መክዳት ለድርጀቱ በሚደውሉ ሰዎች ቁጥር ላይ ያመጣው ተጽእኖ እንደሌለ የገለጸው የመረጃ ክፍሉ፣ እንዴያውም ህዝቡ በቁጭት ስሜቱን እና ድጋፉን ሳያቋርጥ እንዲገልጽ አድርጎታል ሲል አክሏል። ህዝቡ በአገር ውስጥ ባለው አፈና በመማረር አስቸኳይ ለውጥ እንዲመጠብቅ የሚገልጸው ድርጅቱ፣ ትግሉ ትእግስትንና ጽናትን የሚጠይቅ በመሆኑ ታግሶ በውስጥ የሚያደርገውን ትግል እንዲገፋበት ጠይቋል።
መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከድርጅቱ በተገኘው መረጃ መሰረት በቀን ውስጥ ወደ ንቅናቄው ከሚደውሉ በመቶዎች ከሚቆጠሩ ስልኮች መካከል 80 በመቶው ፣ ንቅናቄውን ለመቀላቀል መረጃ...
ETHSAT.COM

No comments:

Post a Comment