Sunday, February 28, 2016

ኢንስፔክተር ተስፉ የተሰኘ የፌደራል ፖሊስ ጦር መሪ በርካታ አባላትን ከነሙሉ ትጥቃቸው ይዞ ከሁመራ ስርዓቱን ከዳ፡፡(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)




ኢንስፔክተር ተስፉ ሁመራ እና አካባቢው የሚንቀሳቀሰው ፌደራል ፖሊስ መሪ፣ ለህወሓት ታማኝ እና ጠንካራ ከሚባሉት ቀዳሚው የነበረ ሲሆን በትናንትናው ዕለት የካቲት 19 2008 ዓ.ም የሚመራቸውን በርካታ አባላት ከነሙሉ ትጠቃቸው ይዞ ሁመራ ከሚገኝ ጦር ግንባር ጠፍቷል፡፡
የኢንስፔክተር ተስፉን እና በርካታ ተከታዮቹ የሆኑ የፌደራል ፖሊስ አባላትን መጥፋት ተከትሎ ህወሓት ጎዳናዎችን በጦር ዘግቶ ወጥሯል፤ ከፍተኛ አሰሳም እየተካሄደ ይገኛል፡፡ ነገር ግን ኢንስፔክተር ተስፉና ተከታዮቹ እስካሁን የገቡበት አልታወቀም፡፡ አገዛዙ እነ ኢንስፔክተር ተስፉ ወደ ኤርትራ ተሻግረው ብረት ያነሱ የነፃነት ድርጅቶችን እንደተቀላቀሉ ያምናል፡፡

ከወልቃይት ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በወልቃይት ምድርና አካባቢው የሰፈነው ውጥረት አይሎ ሊፈነዳ ተቃርቧል፡፡(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)


ህወሓት ደጋፊዎቹን ከትግራይ በማጓጓዝ የወልቃይት ህዝብ የማንነቱን ጥያቄ ተቃውሞ አደባባይ የወጣ በማስመሰል የውሸት ሰላማዊ ሰልፎች እያደረገ ነው፡፡ ከሰሞኑ በጠገዴ ወረዳ ከተካሄደው የሀሰት የድጋፍ ሰልፍ በተጨማሪ ህወሓት 16 አውቶብስ ሙሉ ህዝብ ከመሃል ትግራይ አጓጉዞ በጠለምት፣ ደጀና፣ አደባይ እና በሌሎችም ቦታወች የወልቃይትን ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ የሚቃወሙ ሰልፎች አካሂዷል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የሽፍቶች ቡድን ህወሓት በወልቃይት ህዝብ ላይ የሚያደርገውን እስር፣ አፈና እና ማዋከብ በእጅጉ አበርትቶታል፡፡ የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄውን ህወሓት እመራበታለሁ በሚለው ህገ መንግስቱ መሰረት በሰላማዊ መንገድ ይፈቱልኛል ብሎ የመረጣቸው ወኪሎቹ እየታደኑ በመታሰር ላይ ናቸው፡፡ ህዝቡን ያስተባብራሉ ተብለው የተጠረጠሩ ቁጥር ስፍር የሌላቸው የወልቃይት ወጣቶችም በየቀኑ እየታፈኑ ደብዛቸው እየጠፋ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ ህወሓት ህዝብ ከመሃል ትግራይ አጓጉዞ በወልቃይት ህዝብ ስም “እኛ ትግሬዎች ነን አማራዎች አይደለንም” በማሰኘቱ የወልቃይት ህዝብ ከመቸውም ጊዜ በላይ ውስጡ እንደሻከረ እየተነገረ ነው፡፡
በመሆኑም በወልቃይት ሰማይ ስር ሊፈነዳ ከጫፍ የደረሰ የአመፅና የቁጣ ድባብ እያንዣበበ ነው፡፡

ዳግማዊ ምንሊክ እና የአድዋ ድል ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የማንነታችን መሰረትና የህልውናችን መገለጫ ... አደዋ ደረሰ! ጎጠኞች ከፋቸው! ኢትዮጵያዊነት ሊተረክባቸው!!

ከባንዳ ሁሉ የበለጠ የሚዶክከኝ ከባንዳ አያቶቹ የክህደት ታሪክ እራሱን አርቆ የራሱን የጀግንነት ታሪክ በመጻፍ ፋንታ የምንተ እፍረቱን የባንዳ አያቶቹን ቅሌት ሊሸፋፍን እና ሊያወድስ የሚቀባጥር ባንዳ ነው። ጀግንነትም ሆነ ክህደት በደም ይወረሳል የሚል እምነ የለኝም። የጀግና ልጅ እንዳባቱ ጀግና ካልሆነ ሙገሳ፣ የባንዳም ልጅ እንዳባቱ ባንዳ ሆኖ ካልተገኘ ወቀሳ ይገባቸዋል ብዬ አላምንም። ሁላችንም በግዜያችን ባለን አቋም እና ስራ መለካት ይኖርብናል-ፍትሃዊ የሆነ አመለካከት ነው ብዬ አምናለሁ።

Saturday, February 27, 2016

Breaking: የቴዲ አፍሮ የአዲስ አበባ ኮንሰርት ተከለከለ – ለምን? ዝርዝር አለን

Breaking: የቴዲ አፍሮ የአዲስ አበባ ኮንሰርት ተከለከለ – ለምን? ዝርዝር አለን

አድዋ – “ያባከንነው ድላችን!” – ባዩልኝ አያሌው

Adwa Arbይህች ሀገር ብዙ የተከፈለባት ምድር ናት! ለውድቀቷ የተጉ የመኖራቸውን ያህል፣ ብዙዎች ሕይወታቸውን ከፍለው ለዛሬ ያበቋት ሀገር ናት፡፡… እኒህ ባለውለታዎቿ ሰው እንደመሆናቸው፣ የሰው ልጅ በዘመኑ የሚፈጽመውን ስህተት የፈጸሙ ቢሆን እንኳን፣ እናት ላሏት ኢትዮጵያ የከፈሉት ዋጋ ከዋጋ በላይ ነው፡፡ ይህንን መካድ፣ አለማክበርና ማባከን አለመታደል ነው፡፡ ራስንም ለውርደት አሳልፎ መስጠት!

BREAKING: The military has officially taken over Oromia




Today high ranking military, intelligence and federal police officers held emergency security meeting with President of Oromia, Muktar Kedir, at his office located in Addis Ababa. The meeting was chaired by General Asefa Abiyu,Commissioner of Federal Police and Muktar Kedir, President of Oromia. In attendance were mostly military officers above the rank of Colonel and commanders of federal police.
Intelligence Officers presented analysis and assessment of security situation in Oromia, which concluded the civilian leadership has failed to contain the situation hence the matter is now a national security crisis. They proposed the military formally take over security operations in the region. Accordingly Oromia has been subdivided into eight ( 8) military regions ( wetderawi ketena) each to be led by military generals. Civilian administration is cooperate and report to the commanding generals. The generals are to report to a command post which includes chief of armed forces, intelligence and federal police. Oromo generals strongly opposed the decision but no one heard them.

This is an official coup d’etat against civilian leaders in Oromia and perhaps the first step towards staging one at federal level. Stay tune for more details about which generals are put in charge and analysis of how this impacts the ongoing conflict

የትግራይ ነጻ አዉጭ ቡድን (ህወሃት) በሰሜኑ በኩል የሚደያረገዉ ዉጊያና ሰራዊቱ

(ልኡል አለም) — መላዉ ኢትዮጵያዊያንን በሐይልና በጉልበት ሲገዛ የነበረዉ ህዝባዊ ጠላት ወያኔ አሉኝ የሚላቸዉን የመከላከያ ሰራዊት አባልት በኤርትራ ላይ ለማዝመት ሁለት ዋነኛ አላማዎ ችን ለሰራዊቱ አስቀምጧል።
ኤርትራ ለዘመናት የደከምንበትን እና ያጎለበትነዉን ሐገራዊ እድገት ለመቀልበስ አሸባሪዎችን አሰልጥና ወደ ሐገራችን እየላከች አርበኞች ግንቦት 7 በተባለ የሻቢያ ሐይል እየተመታን እንገኛለን በመሆኑም ከኤርትራ ድንበር ዉጭ በገዛ መሬታችን ላይ ገዢ ቦታዎችን በቁጥጥራቸዉ ስር ያደረጉት እነዚህ የሻቢያ ተላላኪዎችን መደምሰስ ዋና አጀንዳን ነው።
ኤርትራ የተቀመጠዉ መንግስት በኢትዮጵያ ዉስጥ ለተቀሰቀሰዉ ህዝባዊ አመጽ ዋነኛ ተጠያቂና ምክንያት ነዉ፣ ይህንን ድርጊት ለአመታት ሲፈጽሙብን ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መልኩ ለማግባባት ብንሞክርም አልቻልንም፣ ዛሬ የኦሮምን ህዝብ በመቀሰቀና መንግስትን በመገልበጡ ሂደት ላይ እየሰራ የሚገኘዉን ሻቢያ ከስር መሰረቱ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በሌላ መተካት አላማችን ነዉ።
የሚል መንደርደሪያ በመሆኑ ምክንያት የመከላከያ ሰራዊቱ በሁለት ጎራ ተከፍሎ እንዲጋጭ አይነተኛ መንገድ ተከፍቷል።
በተለይም የኦሮሞ ብሔር ተወላጆችና የአማራ ብሔር ተወላጆች የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ወገናዊ ተቆርቋሪዎች... ከአመራር ጀምሮ እስከ ጓድ መሪ ድረስ የስልጣን እርከን ዉስጥ የሚገኙ... የህዝብን ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ ጦርነት መመረጡ አግባብ አይደለም! አርበኞች ግንቦት7ም ሆነ ኦነግ ወገኖቻችን ናቸዉ መንግስት ሰላማዊ በሆነ መልኩ ልዩነቶችን ለመፍታት ያደረገዉ ጥረት የለም! ለምን ጦርነት እንደ መፍትሄ ይወሰዳል? በሚል እስተሳሰብ እርስ በእርሱ እየተመካከረ ሲሆን ..ገና ጦርነቱ ሳይጀመር ሰራዊቱ እየተሰወረ ለመሆኑ ታማኝ ምንጮቻችን ገለጸዋ።

የሕወሓት ጦር ኦሮሚያን በ8 ቀጠናዎች ከፋፍሎ በሕዝቡ ላይ እርምጃ ለመውሰድ መወሰኑ ተጋለጠ

የኦሮሞ ሕዝብ እንቅስቃሴ 4ኛ ወራት እያስቆጠረ ነው:: ቀደም ሲል የኦሮሞ ሕዝብ ቁጣ እየተቀጣጠለ ሲሄድ ክልሎ ከኦህዴድ አስተዳደር እጅ ወጥቶ በቀጥታ በሕወሓት መሪዎች; የደህነነት ኃይሎች እና ወታደሮች እንዲመራ መደረጉን ዘ-ሐበሻ በተደጋጋሚ ስትዘግብ ነበር::
ሕወሓት ክልሉን በደህንነት እና በወታደሮች እንዲመራ ቢያደርግም ምንም ዓይነት መፍትሄ ሳይመጣ ይበልጡኑ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ ከማስተር ፕላኑ አልፎ ወደ ሰብ አዊ መብቶች እና እስከ ነፃነት ጥያቄ ተሸጋግሯል:: በአንዳንድ ከተሞች እንደውም የኦህዴድ ባንዲራዎች በኦነግ ተተክተው መታየታቸው የሚታወስ ነው::
እስካሁን 4ኛ ወሩን ባስቆጠረው የኦሮሞ ሕዝብ አመጽ ከ200 ሰዎች በላይ መገደላቸውን የሰብ አዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ይናገራሉ:: የሕዝቡ ቁጣ አሁንም ያስፈራው ሕወሓት የሚመራው መንግስት ዛሬ በኦሮሚያ በግልጽ የወታደራዊ አስተዳደር አውጇል:: በዚህም መሠረት ክልሉን በ8 ቀጠናዎች በመከፋፈል በሕወሃት ጦር እንዲመራ ወስኗል::
ይህ በኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ተደረገ በተባለው የሕወሓቶች እና የድህነነቶች ስብሰባ እንደተገለጸው 8ቱን ቀጠናዎች የሚመሩት የሕወሓት አባል የሆኑ የጦር መኮንኖች ናቸው::
ይህን የሕወሓትንና የድህነንቱን ውሳኔ አንዳንድ የኦሮሞ ብሄረሰብ ተወላጅ የሆኑ የመከላከያ አባላት ቢያወግዙትም “ኦነጎች ናችሁ” እየተባሉ እንደተሽሟጠጡና ሃሳባቸውም በሕወሃት ሰዎች ተቀባይነት እንዳላገኘ ተገልጿል:: እንደዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጻ በሠራዊቱ ውስጥ ያሉት የኦሮሞ ተወላጆች እየተሰለሉ እንደሆነ በሌላ ሰው እንዲነገራቸው እየተደረገ ይገኛል::

ጭፍጨፋውን ለማስቆም ሆ ብሎ መነሳት ብቸኛው መፍትሄ ነው ! February 26, 2016

ጭፍጨፋውን ለማስቆም ሆ ብሎ መነሳት ብቸኛው መፍትሄ ነው !

February 26, 2016
የዛሬ 79 አመት ባህር አቋርጦ ድንበር ተሻግሮ የመጣው የጣሊያን ፋሽስት ሠራዊት በአዲስ አበባ ነዋሪ ወገኖቻችን ላይ ከፈጸመው ዘግናኝ የጭፍጨፋ እርምጃ የማይተናነስ እልቂት፣ ዛሬም በኦሮሞ ወገናችን ላይ በአገር በቀል የህወሃት አልሞ ተኳሽ የአጋዚ ጦር ሠራዊት እየተፈጸመ ይገኛል።
የካቲት 12 ቀን 1929፣ በሮዶልፎ ግራዚያኒ ትዕዛዝ የአዲስ አበባን ነዋሪ ሕዝብ በደም ጎርፍ ባጥለቀለቀው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ህጻናት፣ ጎልማሶች ፣ ሽማግሌዎች፣ አሮጊቶች፤ ነፍሰጡሮች፣ ለጋ ወጣቶች፣ በአጭሩ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ሁሉ ዘራቸው ፣ ሃይማኖታቸውና ጾታቸው ሳይለይ በጅምላ በመታረዳቸው፣ ደማቸው በስድስት ኪሎ አደባባይ እንደ ወራጅ ወንዝ መፍሰሱን፣ ታሪክ ጊዜ በማያደበዝዘው ብዕሩ መዝግቦት ይገኛል። የግራዚያኒ ጦር በወገኖቻችን ላይ ያንን አሰቃቂ እልቂት የፈጸመው ለነጻነታቸው ቀናይ የሆኑት ሞገስ አስግዶምና አብረሃ ደቦጭን የመሳሰሉ ጀግኖች ኢትዮጵያኖች፣ የጣሊያንን ቅኝ አገዛዝ በመቃወም በጠላት ላይ የፈጸሙትን ጥቃት ለመበቀልና በጠመንጃ ሃይል የአገሪቱን ህዝቦች በባርነት ቀንበር ሥር አውሎ ሃብትና ንብረት ለመዝረፍ በማለም ነበር።
ከጊዜ ወደ ጊዜ ግልጽ እየሆነ የመጣው በፋሽስት ጣሊያንና ለጠባብ የቡድንና የግል ጥቅም የመንግሥትን ሥልጣን የሙጥኝ ባለው ህወሃት መካከል ያለው ልዩነት አንዱ ባዕድ ወራሪ ሌላኛው አገር በቀል ከመሆን ያለፈ አይደለም። ጣሊያን የኢትዮጵያን ማዕከላዊ ሥልጣን የፈለገው ለአገሩ ኢንዱስትሪ የሚሆን ጥሬ የተፈጥሮ ሃብት ፍለጋ ሲሆን፣ ህወሃት ደግሞ የአገሪቱን ለም መሬት በርካሽ ዋጋ ለባዕድ በመቸብቸብ ጭምር ባለሥልጣናቱና የጥቅም ተጋሪዎቹ ሃብት እንዲያካብቱ ከማድረግ የዘለለ ራዕይ ኖሮት እንዳልሆነ በበርካታ ተግባሮቹ አስመስክሯል።
ወያኔ አጋዚ የሚባል ልዩ ጦር አሰልጥኖና አስታጥቆ ከህዝብ የሚነሳን ተቃውሞና እሮሮ ለመጨፍለቅ የሚወሰደው ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ፣ መነሻው ለዘረፋ መሣሪያ አድርጎ የሚጠቀምበትን በትረ ስልጣን ለመከላከል እንደሆነ በተደጋጋሚ ገልጿል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኦሮሚያ አካባቢ የተጀመረውን ህዝባዊ ተቃውሞ በሃይል ለመጨፍለቅ የህወሃት ልዩ ቅልብ ጦር በህዝባችን ላይ እየወሰደ ያለው ጭፍጨፋ የፋሺስት ግራዚያን ጦር አዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ህዝብ ላይ የዛሬ 79 አመት ከፈጸመው የሚለየው በሟቹች ቁጥር እና በገዳዮቹ ማንነት ብቻ ነው። የአጋዚን ጦር አሰልጥኖና አስታጥቆ በገዛ ወገኑ ላይ ፣ እንደባዕድ ሠራዊት፣ ጭካኔ የተሞላበት ጭፍጨፋ እንዲፈጽም ያሰማራው ህወሃትም ሆነ ከአለቆቹ የተሰጠውን ትዕዛዝ በፍጹም ታማኝነት ተቀብሎ በገዛ ወገኖቹ ላይ ታሪክ ይቅር የማይል ወንጀል በመፈጸም ላይ የሚገኘው ይህ ሠራዊት፣ ላለፉት 25 አመታት ያልአግባብ ያፈሰሰው ደምና የቀጠፈው ወገኖቻችን ህይወት ቁጥር ለመቁጠር እያዳገተ መጥቷል።
በተለያዩ ጊዜዎች በኦጋዴን፤ በጋምቤላ፤ በቤኔሻንጉል፤ በአፋር፤ በአማራና ደቡብ አካባቢዎች ከደረሰው የግድያ ፍጅት በተጨማሪ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኦሮሚያ አካባቢ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለመደፍጠጥ የአጋዚ ጦር ከአለቆቹ በተሰጠው ትዕዛዝ የጨፈጨፋቸው ዜጎች ቁጥር ከ300 በላይ ደርሷል:: ቁጥሩ ከዚህ በእጥፍ የሚበልጥ ቁስለኛና ከ8 ሺህ በላይ እስረኞችም እንዳሉ ገለልተኛ የሆኑ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እየተናገሩ ነው። በአልሞ ተኳሾች ህይወታቸው ከተቀጠፉት መሃል ዕድሜያቸው ገና 8ና 9 አመት የልበለጣቸው ታዳጊዎች፤ አሮጊቶችና እርጉዝ ሴቶች ይገኛሉ። ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በአምቦ ከተማ በደረሰው ጥቃት የ9 አመት ታዳጊ ህጻንን ግንባር አነጣጥሮ የመታው የአጋዚ ጦር፣ ወንድሟን ከወደቀበት ለማንሳት ጎንበስ ያለቺውን እህቱን በሌላ ጥይት በመምታት ቤተሰቦቿንና የከተማውን ህዝብ የመረረ ሃዘን ውስጥ ጥሏል፤ ተመሳሳይ ግድያ በአሰላ ከተማ ውስጥ በምትኖር የ8 ዓመት ታዳጊ ላይም ተደግሟል።

መነበብ ያለበት የጊሼይ ገጠመኝና ግርምታ – በፍራንክፈርት ኤርፖርት ያገኘው ግለሰብ በዋሽንግተን ዲሲ የህውሃት ጄነራል

                        ግርምታመነበብ ያለበት የጊሼይ ገጠመኝና ግርምታ – በፍራንክፈርት ኤርፖርት ያገኘው ግለሰብ በዋሽንግተን ዲሲ የህውሃት ጄነራል

 June 19, 2015
የዛሬ ኣመት ተኩል በቤተሰብ ችግር ምክንያት ሃገር ቤት ሄጄ ስመለስ ፍራንክፉርት ላይ በቺካጎ በኩል ወደ ካሊፎርንያ ግዛቴ የሚወስደኝን ኮኔክሽን ለማግኘት ስጣደፍ በተርሚናሉ ውስጥ አንድ ግራ የገባው የሚመስል ኢትዮጵያዊ አየሁና ሰላም ካልኩት በሁዋላ ወደ ኣሜሪካ ሲጕዋዝ የመጀመሪያው መሆኑን እሱም በቺካጎ በኩል ወደ ሂውስተን የሚሄድ መሆኑን ስለነገረኝ የውጭው ኣለም የመጀመሪያው ለሆነው ኢትዮጵያዊ ወገኔ መርዳት ግዴታየም ኣድርጌ ካረጋጋሁትና ሁለታችንም ኮኔክሽናችንን ካገኘን በሁዋላ በተርሚናሉ ውስጥ ካለው ኣግዳሚ ወንበር ኣረፍ ብለን ጨዋታ ጀመርን። ኢትዮጵያዊው ወንድሜ ስሙን ሲያስተዋውቀኝ የትግራይ ተወላጅ ለመሆኑ ብገነዝብም እስካረጋግጥ ኣልደመደምኩም። ለማረጋገጥ ደግሞ ትግሬ ነህ ወይም ኦሮሞ ነህ ብየ የማይጠይቅ ሰብእና ያለኝ ነኝና ይልቁንም ባስተሳሰረን ኢትዮጵያዊነትና ለሱም እንድራራለት ያስገደደኝን ሰውነት ወይም ሰው መሆኑ ብቻ ላይ አትኩሬ በሰውነቱ ላይ የሚታየው ጠባሳ ( በኣደጋ ይሁን በበሽታ ባላውቅም)የተበላሸ ፊቱና ቆዳውን እያየሁ በሃዘን ስሜት ወደጨዋታ ገባሁ። ወደ ውጭ ሲወጡ አንኩዋን ለመጀመሪያ ጊዜ ለሆናቸውና ለሚደጋጉትም የሚያስቸግሩ ብዙ ነገሮች መኖራቸውን ከተነጋገርን በሁዋላ በቀጥታ እሱና ኢትዮጵያ ኣሁን የተሳሰሩበትን ገመድ መምዘዝ ጀመርኩ ፥ ለዚህም በውጭ የምኖር መሆኔን ሃገር ቤት በቤተሰብ ችግር ደርሼ እየተመለስኩ መሆኑን ከነገርኩት በሁዋላ እሱም ኑሮው ሃገር ቤት አንደሆነ ኣሁን የሚሔደውም ለ ፩ ኣመት ትምህርት አንደሆነ ነገረኝ።

የሕወሓት ጦር ኦሮሚያን በ8 ቀጠናዎች ከፋፍሎ በሕዝቡ ላይ እርምጃ ለመውሰድ መወሰኑ ተጋለጠ

 የኦሮሞ ሕዝብ እንቅስቃሴ 4ኛ ወራት እያስቆጠረ ነው:: ቀደም ሲል የኦሮሞ ሕዝብ ቁጣ እየተቀጣጠለ ሲሄድ ክልሎ ከኦህዴድ አስተዳደር እጅ ወጥቶ በቀጥታ በሕወሓት መሪዎች; የደህነነት ኃይሎች እና ወታደሮች እንዲመራ መደረጉን ዘ-ሐበሻ በተደጋጋሚ ስትዘግብ ነበር::
ሕወሓት ክልሉን በደህንነት እና በወታደሮች እንዲመራ ቢያደርግም ምንም ዓይነት መፍትሄ ሳይመጣ ይበልጡኑ የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄ ከማስተር ፕላኑ አልፎ ወደ ሰብ አዊ መብቶች እና እስከ ነፃነት ጥያቄ ተሸጋግሯል:: በአንዳንድ ከተሞች እንደውም የኦህዴድ ባንዲራዎች በኦነግ ተተክተው መታየታቸው የሚታወስ ነው::
እስካሁን 4ኛ ወሩን ባስቆጠረው የኦሮሞ ሕዝብ አመጽ ከ200 ሰዎች በላይ መገደላቸውን የሰብ አዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ይናገራሉ:: የሕዝቡ ቁጣ አሁንም ያስፈራው ሕወሓት የሚመራው መንግስት ዛሬ በኦሮሚያ በግልጽ የወታደራዊ አስተዳደር አውጇል:: በዚህም መሠረት ክልሉን በ8 ቀጠናዎች በመከፋፈል በሕወሃት ጦር እንዲመራ ወስኗል::
ይህ በኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ተደረገ በተባለው የሕወሓቶች እና የድህነነቶች ስብሰባ እንደተገለጸው 8ቱን ቀጠናዎች የሚመሩት የሕወሓት አባል የሆኑ የጦር መኮንኖች ናቸው::
ይህን የሕወሓትንና የድህነንቱን ውሳኔ አንዳንድ የኦሮሞ ብሄረሰብ ተወላጅ የሆኑ የመከላከያ አባላት ቢያወግዙትም “ኦነጎች ናችሁ” እየተባሉ እንደተሽሟጠጡና ሃሳባቸውም በሕወሃት ሰዎች ተቀባይነት እንዳላገኘ ተገልጿል:: እንደዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጻ በሠራዊቱ ውስጥ ያሉት የኦሮሞ ተወላጆች እየተሰለሉ እንደሆነ በሌላ ሰው እንዲነገራቸው እየተደረገ ይገኛል::http://www.zehabesha.com/amharic/archives/51502

Friday, February 26, 2016

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) አዲስ አበባ ላይ ያልተሳካላቸው የህወሓት አገዛዝ ፌደራል ፖሊስ አዛዦች ባህር ዳር ላይ በድጋሚ ስብሰባ አካሂደው የባሰውን ተበጣበጡ፡፡


የፌደራል ፖሊስ አመራሮቹ ከእሁድ የካቲት 13 እስከ 16 2008 ዓ.ም ድረስ ነው በባህር ዳር ከተማ ምንም አይነት አዎንታዊ ውጤት ያላመጣ ውይይት ለማድረግ የሞከሩት፡፡ በስብሰባው ላይ “ባልተማሩ የህውሓት ታጋዮች አንመራም... ” የሚል ተቃውሞ ተነስቷል፡፡

በልዩ ልዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተነሳውን የህዝብ ተቃውሞ የጠብመንጃ ጉልበት ተጠቅሞ ፀጥ የማስኘትን የአገዛዙን የፀና አቋም በሚመለከት ደግሞ በአዛዦች መካከል እስከ አምባጓሮ የዘለቀ አለመግባባት ተከስቶ ነበር፡፡ “ወደ ህዝባችን እንዲተኮስ ትእዛዝ አንሰጥም...“ በማለት በግልፅ ተቃውሟቸውን ያሰሙ በርካታ የፈዴራል ፖሊስ አመራሮች ነበሩ፡፡
በመጨረሻም ስብሰባው እንደተለመደው ያለምንም ውጤት ተበትኗል፡፡ ከስብሰባው በኋላ 4 የፌደራል ፖሊስ አመራሮች ስርአቱን ከድተዋል፡፡ ከአራቱ መካከል አንዱ ኢንስፔክተር ፀጉ ይሰኛል፡፡ አራቱም መኮንኖች እስካሁን የት እንደደረሱ የታወቀ ነገር የለም፡፡

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) የህወሓት አገዛዝ የህዝቡን ትኩረት ለማስቀየር የጦር ኃይሉን ኤርትራ ድንበር አካባቢ ከወዲያ ወዲህ በማተራመስ ጦርነት የሚከፍት በመምሰል የተለመደ የማስመሰል ተግባሩን በማከናወን ላይ ነው፡፡


በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተለይም በኦሮምያ በህዝባዊ አመፅ እየተናጠ እና በበረሃ በአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት የሽምቅ ውጊያ ጥቃት እየተፈፀመበት የሚገኘው የህወሓት አገዛዝ ከኤርትራ ድንበር ሰፍሮ የቆየውን ጦር ወደ ኋላ፣ በደጀን የነበረውን ደግሞ ወደፊት እንዲሁም በአንድ ግንባር የነበረውን ወደ ሌላ ግንባር የመቀያየር ሲጨንቀው የሚያደርገውን የተለመደ የውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ስራውን እየከለሰው ይገኛል፡፡

ህወሓት ይህን መከላከያ ሰራዊቱን በእጅጉ ያሰለቸና ያማረረ ወዲያ ወዲህ የማተረማመስ በጭንቅ ሲያዝ እያማጠ ደጋግሞ ሲወልደው የኖረውን የተለመደ ተግባሩን አሁን ደግሞ ከሰሞኑ ከበፊቱ በተለየ መልኩ የተያያዘው በኤርትራ ድንበር አጠገብ "የትግራይ ወጣቶች ማንነታቸው ባልታወቀ የታጠቁ ኃይሎች ታፍነው ወደ ኤርትራ ተወስደዋል..." የሚለው ዜና ከተሰራጨ በኋላ ከውስጥ ከራሱ ሰዎች በገጠመው ተቃውሞ የሰፈነውን ውጥረት ለማርገብም ጭምር ነው፡፡
በቅጥፈት የተካነው የሽፍቶች ቡድን ህወሓት እንዲህ የጦር ኃይሉን በኤርትራ ድንበርና አካባቢው እየወሰደ እያመጣ ካተራመሰ በኋላ ተጠለፉ ለተባሉት የትግራይ ወጣቶች "ተመጣጣኝ የሆነ የአፀፋ እርምጃ ወስጃለሁ..." ብሎ በመገናኛ ብዙኃን ለማስነገር ማቀዱን ለአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ከውስጥ ምንጮች የተላከው መረጃ ይጠቁማል፡፡

ጭፍጨፋውን ለማስቆም ሆ ብሎ መነሳት ብቸኛው መፍትሄ ነው ! ============================


የዛሬ 79 አመት ባህር አቋርጦ ድንበር ተሻግሮ የመጣው የጣሊያን ፋሽስት ሠራዊት በአዲስ አበባ ነዋሪ ወገኖቻችን ላይ ከፈጸመው ዘግናኝ የጭፍጨፋ እርምጃ የማይተናነስ እልቂት፣ ዛሬም በኦሮሞ ወገናችን ላይ በአገር በቀል የህወሃት አልሞ ተኳሽ የአጋዚ ጦር ሠራዊት እየተፈጸመ ይገኛል ::
የካቲት 12 ቀን 1929፣ በሮዶልፎ ግራዚያኒ ትዕዛዝ የአዲስ አበባን ነዋሪ ሕዝብ በደም ጎርፍ ባጥለቀለቀው ዘግናኝ ጭፍጨፋ ህጻናት፣ ጎልማሶች ፣ ሽማግሌዎች፣ አሮጊቶች፤ ነፍሰጡሮች፣ ለጋ ወጣቶች፣ በአጭሩ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ሁሉ ዘራቸው ፣ ሃይማኖታቸውና ጾታቸው ሳይለይ በጅምላ በመታረዳቸው፣ ደማቸው በስድስት ኪሎ አደባባይ እንደ ወራጅ ወንዝ መፍሰሱን፣ ታሪክ ጊዜ በማያደበዝዘው ብዕሩ መዝግቦት ይገኛል። የግራዚያኒ ጦር በወገኖቻችን ላይ ያንን አሰቃቂ እልቂት የፈጸመው ለነጻነታቸው ቀናይ የሆኑት ሞገስ አስግዶምና አብረሃ ደቦጭን የመሳሰሉ ጀግኖች ኢትዮጵያኖች፣ የጣሊያንን ቅኝ አገዛዝ በመቃወም በጠላት ላይ የፈጸሙትን ጥቃት ለመበቀልና በጠመንጃ ሃይል የአገሪቱን ህዝቦች በባርነት ቀንበር ሥር አውሎ ሃብትና ንብረት ለመዝረፍ በማለም ነበር። 
ከጊዜ ወደ ጊዜ ግልጽ እየሆነ የመጣው በፋሽስት ጣሊያንና ለጠባብ የቡድንና የግል ጥቅም የመንግሥትን ሥልጣን የሙጥኝ ባለው ህወሃት መካከል ያለው ልዩነት አንዱ ባዕድ ወራሪ ሌላኛው አገር በቀል ከመሆን ያለፈ አይደለም:: ጣሊያን የኢትዮጵያን ማዕከላዊ ሥልጣን የፈለገው ለአገሩ ኢንዱስትሪ የሚሆን ጥሬ የተፈጥሮ ሃብት ፍለጋ ሲሆን፣ ህወሃት ደግሞ የአገሪቱን ለም መሬት በርካሽ ዋጋ ለባዕድ በመቸብቸብ ጭምር ባለሥልጣናቱና የጥቅም ተጋሪዎቹ ሃብት እንዲያካብቱ ከማድረግ የዘለለ ራዕይ ኖሮት እንዳልሆነ በበርካታ ተግባሮቹ አስመስክሯል ::

ወያኔ አጋዚ የሚባል ልዩ ጦር አሰልጥኖና አስታጥቆ ከህዝብ የሚነሳን ተቃውሞና እሮሮ ለመጨፍለቅ የሚወሰደው ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ፣ መነሻው ለዘረፋ መሣሪያ አድርጎ የሚጠቀምበትን በትረ ስልጣን ለመከላከል እንደሆነ በተደጋጋሚ ገልጿል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኦሮሚያ አካባቢ የተጀመረውን ህዝባዊ ተቃውሞ በሃይል ለመጨፍለቅ የህወሃት ልዩ ቅልብ ጦር በህዝባችን ላይ እየወሰደ ያለው ጭፍጨፋ የፋሺስት ግራዚያን ጦር አዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ህዝብ ላይ የዛሬ 79 አመት ከፈጸመው የሚለየው በሟቹች ቁጥር እና በገዳዮቹ ማንነት ብቻ ነው:: የአጋዚን ጦር አሰልጥኖና አስታጥቆ በገዛ ወገኑ ላይ ፣ እንደባዕድ ሠራዊት፣ ጭካኔ የተሞላበት ጭፍጨፋ እንዲፈጽም ያሰማራው ህወሃትም ሆነ ከአለቆቹ የተሰጠውን ትዕዛዝ በፍጹም ታማኝነት ተቀብሎ በገዛ ወገኖቹ ላይ ታሪክ ይቅር የማይል ወንጀል በመፈጸም ላይ የሚገኘው ይህ ሠራዊት፣ ላለፉት 25 አመታት ያልአግባብ ያፈሰሰው ደምና የቀጠፈው ወገኖቻችን ህይወት ቁጥር ለመቁጠር እያዳገተ መጥቷል።

Atse Menelik and Adwa, Poemአደዋ ደረሰ ጎጠኞች ከፋቸው ኢትዮጵያዊነት ሊተረክባቸው ። የአድዋ ድል ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የማንነታችን መሰረትና የህልውናችንም መገለጫ ነው፡፡ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ብቻም ሳይሆን ለመላው የጥቁር ህዝብ የነፃነት ተምሳሌትና የአርነት መስታዎትም ጭምር ነው፡፡ የሰው ልጅ በቆዳው ቀለም ምክንያት መዋረድም ሆነ ማነስ እንደሌለበት፣ ጥቁር ህዝብ በአፈጣጠሩም ሆነ በአስተሳሰቡ ‘ልዩና ድንቅ ነን’ ብለው ከሚኮፈሱት ነጮች ያላነሰ ማንነት እንዳለው፣ ካልነኩት ተንኮል የማይሸርብ ሲነካ ግን በማንነቱ ላይ የማይደራደር ድንቅ ፍጥረት መሆኑ የታየበት ድል ነው የአድዋ ድል፡፡ ዛሬ አለም አብዝታ ስለሰው ልጆች እኩልነት እየሰበከችና በዚህም ስም አያሌ መድረኮችን እያዘጋጀች ቢሆንም ገና ብዙ ያልተፈቱ ተያያዥ ችግሮች እያየን መሆኑ የሚካድ ሃቅ አይደለም፡፡ የአድዋ ድል ግን ገና ያኔ ስልጣኔ ባላደገበት፣ የሰው ልጅ አስተሳሰቡ ባልጎለመሰበት፣ እንኳን ነጮች ጥቁሮች ራሳቸው ባርነት የመፈጠራቸው ዕጣ ፈንታ፣ የአርባ ቀን እድላቸው እንደሆነ አስበው ባርነታቸውን ከእንባቸው ጋር እያጣጣሙ በነበሩበት በዚያ ዘመን… የጥቁርነት ትርጉሙን ፣ የሃገርና ህዝብን ሉአላዊ ክብርን ለመላው አለም በወሬ ሳይሆን በተግባር ያሳየ ዘመን አይሽሬ የመመኪያችን መድረክ ነው የአድዋ ድል፡፡ Atse Menelik and Adwa, Poem

Thursday, February 25, 2016

የኢህአዴግ መንግስት በኤርትራ ላይ ጥቃት ለመክፈት እየተዘጋጀ ነው ተባለ




የካቲት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ምንጮች እንዳሉት በተለያዩ የውስጥ ችግሮች ተወጥሮ የሚገኘው ኢህአዴግ በኤርትራ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ነው። በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች በአካባቢው በሚገኙ የመንግስት ወታደሮች ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ ቆይተዋል። በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶችም እነዚህን ነጻ አውጭዎች ለመቀላቀል ድንበር አቋርጠው እየተጓዙ ነው። ይህ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ስጋት ላይ የጣለው የኢህአዴግ መንግስት፣ በኤርትራ ላይ ድንገተኛ ጥቃት ለመክፈት ወታደራዊ ልምምዶችንና ዘግጅቶችን በማድረግ ላይ ነው። ሰሞኑን በኦሮምያ ለተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ የኤርትራ እጅ አለበት ሲሉ አቶ ሃይለማርያም መናገራቸው ይታወሳል። ምንም እንኳ የተፈለገውን ያክል የሰው ሃይል ባይገኝም፣ ኢህአዴግ መንግስት ሁለተኛ ዙር ወታደራዊ ምልመላ ለመጀመር ማስታወቂያዎችን በየቦታው ለጥፏል። መከለከያ ሰራዊቱ በከፍተኛ ሁኔታ በዘር ተከፋፍሎ በሚገኝበት በዚህ ወቀት ፣ በኤርትራ ላይ ጥቃት መፈጸም፣ የኢህአዴግን ፍጻሜ ያፋጥነዋል በማለት ምንጮች አስተያየታቸውን አስፍረዋል። በኢትዮጵያ በኩል የሚደረገውን የጦር ዝግጅት በተመለከተ የኤርትራ መንግስት የሰጠው መግለጫ የለም።

http://amharic.ethsat.com/%e1%8b%a8%e1%8a%a2%e1%88%85%e1%8…/

ESAT Bezhisamint Professor Berhanu Nega February 20 2016

የአባይ ወልዱ በወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ላይ የጦርነት ነጋሪት መጎሰም የህይወት ዋጋ ያስከፍላል! | ጎንደር ህብረት


ጎንደር ህብረት
የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር ብሎ እራሱን የሚጠራዉ ድርጅት መሪ አቶ አባ ወልዱ እና የክልሉ የፀጥታና የአስተዳደር ኃላፊ አቶ ሐድስ ዘነበ ከዘራፊ ካድሬወቻቸው ጋር በመሰባሰብ፤ በወልቃይት፤ በጠገዴ እና በጠለምት ህዝብ ላይ የማያዳግም ጦርነት ለማካሄድ የጦር ነጋሪት እየደለቁ በማስፈራራት ላይ ይገኛሉ። ጦርነቱን በሚፈልጉት መንገድ በድል ለመወጣት እየተጠቀሙበት ያለው የሞራል መምቻ ደግሞ፤ ህብረተሰቡን፤ በገብያ፤ በቤተክርስቲያን እና ቤት ለቤት በማደን እያስፈራሩ ወደፖሊስ ጣቢ እየወሰዱ፤ ወልቃይት የትግራይ ክልል እንደሆነች እንድትቀጥል እንደሚፈልጉ በማሥመሰል በማሥገደድ እያስፈረሙ ናቸው።
Gondor Hibret
ሌላ የዚህ ሳምንት አስገራሚዉ የወያኔ ቲያትር ደግሞ፤ ከስህተት ላይ ሥተት በመደራረብ ህዝብና ህዝብን ለማጋጨት የትግራይ ተወላጆችን ስልፍ አሰልፎ በጉልበት ይዞት የቆየዉን መሬት የትግራ ነዉ እያለ ማስጨፈሩ ነዉ። ወያኔ በመላዉ ኢትዮጵያ ሰልፍ ከልክሎ ሰላማዊ ሰልፈኞችን በታንክና መትረየስ እዬጨፈጨፈ፤ ጎንድር መሪ የሌለዉ መሆኑን የተረዳዉ ወያኔ ወገራ አዉራጃ ላይ የትግራይ ተወላጆችን ከጎንደር ህዝብ ጋር ቂም ለመትከል የዉሸት ሰልፉን አቀነባብሮ ያስጨፍራል። የተቃዉሞ ስሜትን በአደባባይ መግለጽ ከሆነማ ይህ አይነቱ ወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት ብሎም ለመላዉ ጎንደር/ አማራ ህዝብ መፈቀድ የግድ ይላል።
ጦረኛ ቡድን በአሁኑ ሰዓት ሌላ ወንጀል እና ደባ ከመፈጸም ይልቅ፤ መደረግ የነበረበት፤ የወልቃይት፤ የጠገዴ እና የጠለምትን ህዝብ ባለፉት 25 ዓመታት በተፈጸመበት ግፍና በደል ይቅርታ መጠየቅ ነበር እንጂ አድሮ ጥጃ የሆነዉ የትግራይ ነፃ አዉጭ ግንባር የአማራን መሬት በሰፊዉ ለመቆጣጠር የጦርነት ክተት አዋጅ ነጋሪት መደለቅ እና በቴለቭዥን መስኮት ውሸት መርጨት አልነበረበትም። ይህ ድርጊት ታሪክ ይቅር የማይለው አሳዛኝ ተግባር ነው። ለዚህ ሰይጣናዊ ስራው የሚገጥመዉ ምላሽም በጣም የከፋ ሊሆን ስለሚችል ለጥፋት ብቻ ትግራይ መሬት ላይ የተቀመጠዉ አቶ አባይ ወልዱ በጊዜው የያዘውን ሥልጣን እና ያስታጠቀውን ሚሊሺያ ሌላ ሊበግረው የሚችል ሃይል መሥሎት በትቢት ወይም በድንቁርና ከአንድ ጥፋት ወደ ሌላ ጥፋት መሸጋገሩ ትልቅ አደጋ ነዉ። በመላው አገሪቱ በዜግነታቸው ኮርተው፤ የሚኖሩበትን ህብረተሰብ አምነው እና ተዋደው የሚኖሩትን የትግራይ ተወላጆች በወልቃይት ጠገዴ የግፍ እሳት ላለማቃጠል ቆም ብሎ እንዲያስብ እጅግ እናሳስባለን።

Wednesday, February 24, 2016

የአቶ ሃይለማርያም ዛቻም ሆነ የሃይማኖት አባቶች ተማጽኖ በኦሮምያ የሚካሄደውን ህዝባዊ ተቃውሞ አላስቆመውም

የካቲት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአጋዚ ወታደሮች ለተቃውሞ በሚወጡት ወጣቶች ላይ በቀጥታ እንዲተኩሱ ትእዛዝ ተሰጥቷቸዋል፣አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝም መንግስታቸው የማያዳግም እርምጃ እንደሚወስድ በአደባባይ ዝተዋል። የተለያዩ ሃይማኖቶችን የሚወክሉ የሃይማኖት አባቶች፣ በመንግስትና በህዝቡ መካከል መነጋጋር እንዲጀመር ጥሪ አቅርበዋል። ይህ ሁሉ ዛቻና ምክር እየተሰጠ ቢሆንም፣ የክልሉ ወጣቶች የሚያቆመን የለም በማለት ዛሬም ትግላቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል። የቦረና እና የጉጂ ዞኖች የዛሬው ተቃውሞ ማእከል ሆነዋል። በቡሌ ሆራ ከተማ ተማሪዎች ምሽት ላይ በሶስት ኦራል መኪኖች ተጭነው ከመጡ የአጋዚ ወታደሮች ጋር ተፋጠው አርፍደዋል።ወታደሮቹ ተማሪዎች ከግቢያቸው እንዳይወጡ ሲያስጠነቅቁ ቢያረፍዱም ተማሪዎች ግን ማን ነው የሚያቆመን በማለት ትእዛዙን ጥሰው ወደ አደባባይ ወጥተዋል። የአጋዚ ወታደሮችም መትረጊስ ሳይቀር በመተኮስ የተማሪዎችን ሰልፍ ለመበትን ሙከራ አድርገዋል። ተቃውሞው ከሰአት በሁዋላም ቀጠለ ሲሆን ፣ በርካታ ተማሪዎች ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።

“የአዲስ አበባን የወደፊት እጣ የሚወስነው ሕዝቡ ነው” | ቃለምልልስ የኦነግ ከፍተኛ አመራር አቶ ኦዳ ጣሴ ጋር

“የአዲስ አበባን የወደፊት እጣ የሚወስነው ሕዝቡ ነው” | ቃለምልልስ የኦነግ ከፍተኛ አመራር አቶ ኦዳ ጣሴ ጋር

Tuesday, February 23, 2016

Bloodiest weekend in protests in the Oromia region of Ethiopia as regime forces indiscriminately shoot at protesters, children as young as 10 killed ESAT News (February 23, 2016)


Dozens of protesters were reportedly killed by Ethiopian regime forces in the Oromia region where a three month protest by the people for political and economic rights has met with deadly response by the army and security.
Children as young as ten were shot and killed by the regime’s Agazi forces on Monday, on a day of carnage that saw at least 40 dead of which 7 were children under the age of 15, according to posts by Jawar Mohammed, Executive Director of the Oromo Media Network.
Gruesome photo and video posts by Jawar, who receive them directly from the protesting areas and updated by the minutes on his Facebook page shocked the nation, in what Ethiopians see as further evidence of the brutality of the minority regime whose forces killed at least 200 protesters in the last three months. 
Protesters were peaceful and their only weapon of defence was blocking the roads with stones and logs to prevent the forces from entering their villages.

Video and pictures in the social media are too grisly to share here but protesters are seen in one video carrying a body of a young man who was shot on his torso, while other pictures show bodies of children shot in the neck and head.
Another photo show Abdi Adulla, a ten year old in East Harage, was shot in the neck and killed yesterday.
In just one locality called Machara, ten people were killed and over twenty were wounded as the Agazi forces arbitrarily shot at the protesters.

Protests were held in Hararge, Wollega, Arsi, Guji and a number of other localities in the last three days and reports show that they were still continuing today.
(Pictures obtained from Jawar Mohammed/OMN)

" የጥፋት ልጆችን እንዴት እንታገል"

መነበብ ያለበት--በኤርሚያስ ለገሰ
" የጥፋት ልጆችን እንዴት እንታገል"
ብዙ ሰዎች የወይዘሪት ሚሚ ስብሀቱ ስብእና ፊቱ ላይ እየተደቀነ ሴትየዋን እና በዙሪያዋ የተሰባሰቡ ትናንሽ ሰዎች የሚያቀርቡትን ፕሮግራም የመስማት ፍላጐት ያጣል። ርግጥም የእነ ሚሚ ፕሮግራም በቅዱስ መጵሀፋ " የአመጳ ሰው እርሱም የጥፋት ልጅ" እንደሚለው የሚፀነሰው በአደንዛዥ እጵ እና በስካር መንፈስ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም ምክንያት አብዛሀው በንቀት ፣ በመፀየፍ እና አቃሎ በመመልከት ቢያልፈው የሚያስገርም አይደለም። እውነትም እነዚህ የመንፈስ ድሀዎችን ማዳመጥ ጊዜ እንደማጥፋት ቢቆጥረው እና ትእግስት ቢያጣ ትክክል አይደለህም አይባልም።
ነገር ግን እንደ አንድ ስርአቱ ውስጥ እንደነበረ እና የአገዛዙ የኮሙዩኒኬሽን መልእክቶች እንዴት ተቀርፀው፣ እንዴት እንደሚተላለፋ ለሚያውቅ ሰው ጉዳዩን ከብዙ ኢትዬጲያውያን በተለየ እመለከተዋለሁ። በአጭሩ እነ ሚሚ የሚናገሩት በሙሉ ሳይቀነስ ሳይጨመር የኮሙዩኒኬሽን እና ደህንነት ጵ/ቤት ሀላፊዎች አዘጋጅተው የሚሰጧቸውን ብቻ ነው። የመልእክቱ ማእከላዊ አላማ ደግሞ ህውሀት እና መሪዎቹን የበላይነት፣ የገዥነት እና ከህግ በላይ መሆንን ማሳየት ነው። ከዚህ በተጨማሪም ለሌሎች ብሔረሰቦች ያላቸውን ንቀትና ጥላቻ ባገኙት አጋጣሚ ማሳየት ነው። እዛው ሳለ በቀጣይ ሊወሰዱ የሚችሉ ጥቃቶችን እና ሰለባዎችን የሚያመላክቱበት ነው። የእነ ሚሚ ንግግር አይን ያወጣ ክህደት እና የልብ ውፋሬ የሚታይበት በዚህ ምክንያት ነው።
እናም በፓለቲካ ውስጥ ተሳትፎ ያላችሁ ሰዎች እነዚህ የመንፈስ ድሆች እና የቤት ውስጥ ባሪያዎች ተክለ ሰውነት ወደ ጐን ትተው ከአንደበታቸው የሚወጣውን መስማት የሚከፋ አይደለም። " እኛ ከመልእክቱ እንጂ፣ ከተናጋሪው ምን አለን" የሚለው አባባል እዚህ ላይ የሚሰራ ይመስለኛል። ለማንኛው ለዛሬ ሶስት ነገሮች ላይ ላተኩር፣
1• የአሜሪካን ድምጵ (VOA) ኦሮምኛ እና አማርኛ ፕሮግራም፣
እነ ሚሚ በዛሬው ዝግጅታቸው የአሜሪካ ድምጵን (VOA) ከሽብርተኞች ጋር ግንኙነት ፈጥሯል፣ መረጃ የሚያስተላልፈው ከእነሱ እየተቀበለ ነው የሚል ክስ አቅርበዋል። ይሄ ምን ማለት ነው?…ለምን ይሔ ክስ አሁን መጣ? …የሚሉትን ጥያቄዎች ማንሳት ተገቢ ይመስለኛል። እውነት ለመናገር የአሜሪካን ድምጵ የአማርኛ እና ኦሮምኛ ፕሮግራም ባለፋት ሁለት ወራት ባስተላለፋቸው ፕሮግራሞች የህዝብን በደል እና ገፍ ለማሳየት የሔደበት እርቀት ምስጋና የሚቸረው ነው። በኦሮሚያ፣ በቅማንት፣ ወልቃይት ኢትዬ ሱዳን እና ድንበር ፣ ረሀብ ዙሪያ፣… የተቃዋሚ አመራሮችን ፣ የአገዛዙን ባለቤቶች ፣ የአገሬ ጉዳይ ያገባኛል የሚሉ ልሂቃን …ወዘተ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ይበል የሚያስብል ነው። በተለይ የኦሮምኛ ፕሮግራም አዘጋጅ እህታችን ጋጠ ወጡ ሰውዬ ሳይወድ በግድ "የተፋውን ክርፋት መልሶ እንዲውጥ!" በማድረግሽ አድናቆቴ ይድረስሽ።
እናም አሁን የሚነሳው ትልቁ ጥያቄ ቪኦኤ በዚህ መልኩ እንዲቀጥል እድል ይሰጠዋል ወይ?… ከጀርባ በሚጐነጐን ሴራ እና ጫና ተጠልፎ ይወድቅ ይሆን ወይ? የሚለው ይሆናል። …ምላሹን በቀጣይ ቀን እና ወራት በሚያቀርበው ዝግጅት ድምፀት የምንመለከተው ቢሆንም የኢትዬጲያ ህዝብ ከጐኑ ሊቆም ይገባል።
2• ኦህዴድን በተመለከተ
የደህንነት እና ኮሙዩኒኬሽን መስሪያቤቱ በእነ ሚሚ ውስጥ አድሮ እንዲነገርለት የፈለገው ሌላ ቁምነገር ኦህዴድን በተመለከተ ነው። ይኸውም " አሁን በኦሮሚያ የተፈጠረው ችግር ኦህዴድ ሊፈታው የሚችል አይደለም" የሚል ነው። ይህ አባባል ሀሰት አይደለም። በኦሮሚያ የተፈጠረው ችግር በእነ አባዱላ እና ሙክታር አቅም የሚፈታ አይደለም። እንደውም የእነሱ መሳተፍ ችግሩን የበለጠ ያሰፋዋል እንጂ መፍትሔ አያመጣም።
ሁላችንም እንደምናውቀው የኦሮሞ ህዝብ እያካሔደ ያለው ትግል ማእከላዊ አላማ ከፓለቲካ፣ ከኢኮኖሚ፣ ማህበራዊ እና መንፈሳዊ እስር ለመላቀቅ የሚደረግ ነው። ስለዚህ ራሱን ከጭቆና እና ርግጫ ማላቀቅ ያልቻለ ፍጡር የመፍትሔው አካል ሊሆን አይችልም። የእነ አባዱላን ተሳትፎ በዚህ ተራ ውስጥ አሰልፎ መመልከት ያስፈልጋል። እነሱ የለውጡ አደናቃፊ እንጂ የለውጥ ሐዋርያዎች የሚሆንበት እድል ከዜሮ በታች ነው። ባይሆን ቀኑ እስኪመጣ ድረስ ከሀገር ቤት ከሚሸሸው 26 ቢሊዬን ዶላር ድርሻቸው ስንት እንደሚሆን አሳዳሪያቸውን እንዲጠይቁ ይፈቀድላቸው።
እዚህ ላይ " በኦሮሚያ የተፈጠረው ችግር በኦህዴድ አቅም የሚፈታ አይደለም" በሚለው አባባል ላይ የለውጥ ሀይሉ እና ህውሀት (ደህንነቱም፣ ኮሙዩኒኬሽኑም እነሱ ስለሆኑ ነው) የምንስማማ ቢሆንም በትርጉም ደረጃ የምንለያይ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል። የለውጥ ሀይሉ " በኢትዬጲያዊ ስነ ምግባር " ታንጶ የሚናገር በመሆኑ የእነ አባዱላን የሰው ልጅነት ጥያቄ ውስጥ አናስገባም። እነ ሙክታር ከድር ማንነታቸውን በተለያዩ ምክንያቶች አሳልፈው የሰጡ የቤት ውስጥ አገልጋይ ፣ ግን ደግሞ የሰው ልጆች ናቸው። ከዚህ በተቃራኒ ለህውሀቶች በተለይም የመከራ ጊዜ ሲመጣ እነ ሙክታር እና መዋቅራቸው ሰዎች አይደሉም። ይህን ደግሞ እኛ የምንለው ሳይሆን በስጋ ሞቶ በመንፈስ የሚኖርላቸው አቶ መለስ በተደጋጋሚ የገለፀው ነው።
( በነገራችን ላይ በዚህ የእነ ሚሚ ስብሀቱ የጠረጴዛ ውይይት ላይ አቶ መለስ ለስድስት ያህል ጊዜ ስሙ ተጠርቶአል። በጠረጴዛው ላይ የተቀመጡት ሶስቱም ሰዎች በተናጠል ሁለት ሁለት ጊዜ በመጥራት ውዳሴ አቅርበዋል። እነሱ ላነሷቸው ቁልፍ ችግሮች መፍትሔው የሙት መንፈሱ መሆኑን አስረግጠው ተናግረዋል። ርግጥም ሚሚ እንዳለችው አቶ መለስ " ከናዳ ለማምለጥ እንደ ኤሊ ሳይሆን እንደ አቦሸማኔ እንሩጥ!" እያለ ዘወትር ይናገር ነበር። ከተናገረው በተቃራኒ ሮጠ መሰለኝ…?? …
ሌላም ነጥብ አለ። አቶ መለስ ስድስት ጊዜ እንደ ፍቱን መዳኒት ሲጠቀስ ላለፋት ስድስት አመታት በምክትል እና ዋና ጠቅላይ ሚኒስትርነት የተሾመው አቶ ሐይለማርያም አንድ ጊዜም አልተነሳም። በጥቅስ ውስጥ ገብቶ የሚነገርለት አባባልም አልተገኘለትም። ለነገሩ እኛም ፈልገን ማግኘት ስላቃተን የሰሞኑን የኦቦ ሌንጮ ለታ ለጠቅላይ ሚኒስትር ሐይለማርያም የተጳፈ ደብዳቤ ለመምዘዝ ተገደናል። ኦቦ ሌንጮ በደብዳቤያቸው ላይ <<ጀነራል ሳሞራን እና ጌታቸው አሰፋን በአስቸኳይ አባር!>>" የሚለውን ቧልት ጵፈው ዘና አድርገውናል።)
ወደቀደመው ስንመለስ በአቶ መለስ መንፈስ የሚመራው የህውሀት መስሪያቤት ኦህዴድን እንደ ሰው አይቆጥርም። ኦህዴድ ለአቶ መለስ " የዝንብ ጥርቅም" ነው። መረጃ ካስፈለገ " የአብዬታዊ ዲሞክራሲ የአመራር ጥበብ" የሚለው የምጡቁ ፣ ባለራእዩ፣ በክፈለ ዘመን አንዴ የሚፈጠሩት ታጋይ መለስ መጵሀፍ ኦህዴድን በተመለከተ ምን እንዳሰፈረ እንመልከት፣
" ስልጣን የያዝን እንደመሆናችን ወደ እኛ የተጠጋ የተለያዩ ጥቅሞችን ማግኘቱ የማይቀር ነው። ማር ባለበት አስቀድሞ የሚያርፈው ዝንብ ነው። ስልጣን ባለበት አስቀድሞ የሚያንዣብበው ከስልጣኑ ተጠቃሚ መሆን የሚፈልገው ነው። …በደቡብ እና ኦሮሚያ አባላት በብዛት እንመለምላለን። ዝንቦች ሆነው ይገኛሉ። እናራግፋቸዋለን። እንደገና እንሞላለን። ዝንብ ሆነው እናራግፋለን" በማለት ይገልጳል።
3• ጠባብ/ ትምክህት/ አክራሪነት
የህውሀቱ መስሪያቤት በእነ ሚሚ ውስጥ አድሮ እንዲተላለፍለት የፈለገው ሌላኛው መልእክት አሁን እየተካሔደ ያለውን ህዝባዊ እንቢተኝነት ስርአቱ እንደ ማስፈራሪያ የሚጠቀምባቸው " ጠባብ፣ ትምክህት፣ አክራሪ" በሚሉ ቃላት መቀባት ነው። እዚህ ላይ መናገር የማይፈልጉት በአቶ መለስ ስጋ እና መንፈስ የምትመራው " አዲሲቷ ኢትዬጲያ" ላለፋት 25 አመታት በስልጣን ላይ ቆይቶ ባለበት ሁኔታ የተባለው ችግር ቢኖር እንኳን ምንጩ ማነው? ሀላፊነቱን መውሰድ ያለበት ማን ነው? የሚለውን ይሆናል።
የመብት፣ የፍትህ መታፈን፣ ምዝበራ በተንሰራፋበት ሁኔታ (የተባሉት አመለካከቶች በተዛባ ትርጉማቸው ተቀብለንም ቢሆን) ለምን አይኖሩም? …አንዱ አካባቢ ከማሳቹሴት ኢንስትትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ(MIT) ጋር የሚመጣጠን መቀሌ ኢንስትትዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ (MIT) ሲገነባ እያየ ሌላው ቅሬታ ቢቋጥር ለምን ይገርመናል?…አንድን ብሔረሰብ አግንኖ እና የገዥነት አስተሳሰብ እንዲኖረው አድርጐ እንዲሳል ማድረግ በሌላው ላይ የሚፈጥረው ስሜት ምን እንደሆነ ማወቅ እንዴት ይቸግራል?… ለአንዱ "የወርቅነት" ማእረግ ተሰጥቶት፣ ከወርቁ ጥምዝ ውስጥ ተፈልቅቆ የወጣው "የእንቁነት" ደረጃ አግኝቶ ሌላው መኖሪያው እስርቤት ሲሆን እንዴት ቂም አይቋጥርም?…ዋናው ስልጣን ተሰብስቦ በአንድ አካባቢ ተከማችቶ እየተመለከተ ፣እንዴት የእኔ አካባቢ ሰው በቁልፍ ስልጣን ቦታ የለም ብሎ ቢቆጭ ለምን ጠባብነት እንለዋለን?… " አዲሲቱ ኢትዬጲያ" ለስርአቱ ባለቤቶች የገነት ምድር የሆነችበት ( ለንግድ እና መዝናኛ በዱባይ ፣ አሜሪካ እና አውሮፓ ቤት የሚኖራት)፣… ለሌላው ደግሞ ገበሬ፣ ባህታዊ እና ቄስ ጭምር በረሀ አቋርጠው የሚሰደዱባት በሆነበት እንዴት ቁርሾ አይያዝም?… 70% የሚሆነውን መሬት ለራሱ እና ለባእዳን ገጰ በረከት ሰጥቶ ሲያበቃ፣ መሬቱን የተነጠቀው ተኩሶ እየገደለ " መሬቴን ልቀቁ!" ቢል ለምን ይገርመናል?…አገዛዙ መሰረቴ አይደለም ከሚለው አካባቢ ማእድን፣ ቡና ፣ ሰሊጥ፣ ጫት እና የመሳሰሉትን እየነጠቀ ኤክስፓርቲ አድርጐ ሲያበቃ፣ በሌላ በኩል ባለቤቱን የበይ ተመልካች ሲያደርግ ለምን ነፍጥ አያነሳም? …ለምን " አይናችሁ ላፈር!" አይልም!!
በመሆኑም በአሁን ሰአት በኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ኢትዬጲያውያን የተነሳው እምቢተኝነት የሞራል መሰረት እና ልእልና ያለው ነው። ህዝባዊ ንቅናቄው የጥቂቶች ንቀት፣ ጥላቻ ፣ ብዝበዛ እና በመንግስት ውስጥ ሌላ መንግስት መፈጠር የለበትም የሚል ትግል ነው። ተወደደም ተጠላ የተቀጣጠለው አመጵ የኦሮሞ ህዝብ እና መላው ኢትዬጲያ የተነጠቀውን ነጳነት የማስመለስ ነው።
በዚህ ህዝባዊ ጐርፍ ውስጥ ግልጵ ያልሆኑ ነገሮች፣ ጥርጣሬ የሚፈጥሩ አጋጣሚዎች አይፈጠሩም ወይ?… ድብን አድርገው ይፈጠራሉ። ትግሉን ለመቀልበስ እና ሌላ አቅጣጫ እንዲይዝ የሚፈልጉ ሰርጐ ገቦችና ሌሎች ጥቂት ሰዎች አይኖሩም ወይ? …ያለምንም ጥርጥር ይኖራሉ። ዘረኝነትን የሚዋጉ " ዘረኞች!" አይኖሩም ወይ?…አሁንም ያለምንም ጥርጥር ይኖራሉ።
ታዲያ እነዚህ ኢምንት ችግሮች ፋፍተው ለውጡ ላይ ጥላሸት እንዳይቀቡ መፍትሔው ምንድነው?
ትላንት አመሻሽ ላይ የአሜሪካ ጥቁሮች የነጳነት ቀንዲል የሆነውን የማርቲን ሉተር ኪንግ ፣ የጓደኞቹን እና የህዝቡን ትግል የሚያሳይ አንድ መጵሀፍ ሳነብ ነበር። የጥቁሮች " ፀረ -ዘረኝነት" ትግል አጋጥሞት ከነበረው መለስተኛ ፈተና አንዱ " ዘረኝነትን የሚዋጉ ዘረኞች" እያቆጠቆጡ መሄድ ነበር። እነዚህ "ዘረኝነትን የሚዋጉ ዘረኞች " ነጭ ባዩ ቁጥር ደማቸው የሚፈላና ለመተናኮል የሚፈልጉ ነበሩ። ሁሉንም ነጭ በአንድ ቅርጫት ከተው የሚመለከቱ ነበሩ። ከዛም አልፈው ጥቁርነት ከነጭ ይበልጣል፣ ጥቁር የውበት መገለጫ ነው ( ዲንፕል፣ የመመረቂያ ጋዋን፣ የቀሳውስት ልብስ፣ ሙሉ ልብስ…ወዘተ) የሚሉም ነበሩ። በተለይ ድል በተቃረበ ቁጥር እንደዚህ አይነት አመለካከቶች እዚህም፣ እዚያም መደመጡ የማይቀር ነው። የድል አጥቢያ አርበኞች በመድረኩ ላይ ለመቆየት ህብረተሰቡን ሊያቃቅሩ የሚችሉ አባባሎችን መዘው ማውጣታቸው አይቀርም። እነዚህ ደግሞ በአብዛኛው ተማርን የሚሉ የድሉን ጭስ ከሌላው ቀድመው ማሽተት የሚችሉ ናቸው።
ስለዚህ የመጀመሪያው መፍትሔ እንደዚህ አይነት የነጳነት ትግሉን የሚያደበዝዙ ጥቂት ሐይሎች እንደሚኖሩ አምኖ መቀበል ያስፈልጋል። ወደ አደባባይ እያወጡም በግልጵ በመነጋገር እያረቁ መሄድ እና መተማመን መፍጠር ያስፈልጋል። ጥርጣሬዎች ባሉበት ሁኔታ ትግሉን ይጐዳል፣ መከፋፈል ይፈጥራል በሚል "የሆድ ይፍጀው" መፍትሔ የትም አያደርስም። የዛሬ ገዥዎቻችን የትግላቸው እንቅስቃሴ አስር አመት ሲሞላው ቁጭ ብለው ገምግመዋል። በግምገማቸው ትግራይ ሪፐብሊክ ብቻ አይበቃንም፣ ኢትዬጲያን መግዛት እንችላለን ብለው አቋማቸውን ለውጠዋል። ከፈለጉት አላማ ጋር አይሔድም የሚሉትን አራግፈዋል። ኢትዬጲያን ለመግዛት በእኛ የሚታዘዝ የሌላ ብሔረሰብ ፓርቲ እናቋቁም በማለት ጠፍጥፈው ፈጥረዋል። ይህን በማድረጋቸው የድል ባለቤት ሆኑ እንጂ ጠፍተው አልቀሩም።

የትግራይ ወራሪ ቡድን አሉኝ የሚላቸውን ደጋፊዎች አደባባይ አውቶ ማስጮህ ጀመረ!



በዚህ በመረጃ ዘመን ማንን እንደሚያጭበረብሩ አልገባኝም? እኔ እስከሚገባኝ ድረስ የወልቃይት አማራ ኢትዮጵያዉያን እያሉት ያለው እኮ 
1ኛ ከወያኔ አገዛዝ በፊት በነበሩት በየትኛውም መንግስታት ወልቃይት ወደትግራይ አልነበረም የታሪክ ማስረጃዎች ይታዩ ነው።
2ኛ ወያኔ ወደስልጣን እንደመጣ ያለህዝበውሳኔ ነው ወልቃይት ወደትግራይ የተከለለው።
3ኛ ወያኔ በአስርሺ የሚቆጠሩ አማሮች እንዲሰደዱ እንዲገደሉ እንዲታሰሩ ካደረገ በኋላ የነሱን መሬትና ንብረት ከትግራይ እያመጣ ላሰፈራቸው ትግራያን ሰቷል።
4ኛ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ጥንት ወደነበር ወደ ጎንደር የስተዳደር ክልል ወልቃይት ይመለስልን ሲሉ በሰላማዊ ሰልፍ ወይም በህዝበ ውሳኔ አደለም ምክንያቱም በአሁኑ ሰአት በዚህ በሰላማዊ ሰልፍ ላይ የምታዋቸው ነበሩን የወልቃይት የአማራ ኢትዮጵያዊያንን እያፈናቀለ ላለፉት 24 አመታት ወያኔ ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች አምጥቶ ያሰፋራቸው ናቸው። 
ስለዚህ ወያኔ ጊዜው አልፎብሀል አደልም ወልቃይት ላይ ወስደህ ያስፈርከውን ህዝብ ይቅርና መላት ትግራይን አውተህ ብታስጮህ እውቅና እሚሰጥህ የለም። ተባኖብሀል ህዝብ ነቅቷል የጨለማው ዘመን አልፎ የብርሀን ዋዜማ ላይ ነው ያለነው።welkait

ሕወሓቶች የወልቃይት ጸገዴን ሕዝብ መስለው ሰልፍ ወጡ 

ሕወሓቶች የወልቃይት ጸገዴን ሕዝብ መስለው ሰልፍ ወጡ 

Monday, February 22, 2016

ኦነግ ትግሉ የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ ደርሷል ሌሎችም የነጻነቱን ትግል ይቀላቀሉ ሲል ጥሪውን በድጋሚ አቀረበ | የአዲስ አበባ ጉዳይ በሕዝቡ ወደፊት የሚወሰን ይሆናል | ኢትዮጵያ በአወዛጋቢው የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚደረገው የጥናት ውጤት አይገዛኝም ማለቱዋ ተዘገበ | የሕወሓት ወታደራዊና የደህነት ባለስልጣናት በኦሮሚያ ያለውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ለማፈን ተጨማሪ ወታደሮች ተሰማርተው አፈናው እንዲቀጥል ወሰኑ

የህብር ሬዲዮ የካቲት 13 ቀን 2008 ፕሮግራም
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/51333
<...የኦሮሞ ወጣቶች ትግል ከወያኔ ጋር እንጂ ከማንም ጋር አይደለም ።የወያኔ የጭካኔ እርምጃ መንፈራገጥ ካልሆነ ትግሉን የሚያቆም አይደለም ትግሉ የማይቀለበስበት ደረጃ ላይ ደርሷል...ትግሉ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በእኩልነት የሚተዳደሩበት ስርዓት መፍጠር ነው።ሁሉም ትግሉን ሊቀላቀል ይገባዋል... የአዲስ አበባ ወይም ፊኒፊኔ ጉዳይን እኛ የኦሮሚያ ክልል አካል ናት ብለን ነው የምናውቀው።የወያኔን ሕገ መንግስትንም ሆነ የወያኔን መግለጫዎች በጠቅላላ አንቀበልም።የፊንፊኔንም ሆነ የአዲስ አበባን ሁኔታ ወደፊት ሊወስን የሚችለው ሕዝቡ ነው።ሕዝቡ በፌዴሬሽን በኮንፌዴሬሽን ወይንም በተለያየ መንገድ አብሮ የመኖር ውሳኔ ካለው ፊንፊኔ በምን አይነት ሁኔታ ልትተዳደርና በምን አይነት ሁኔታ ልትኖር እንደምትችል ለወደፊት የሚታይ ነገር ነው።ለወደፊት የአገሪቷም ማዕከል የማትሆንበት ምክንያት የለም።ለሁሉም ይህንን ሊወስን የሚችለው ሕዝቡ ነው...> አቶ ኦዳ ጣሴ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር(ኦነግ) በውጭ የድርጅትና የፖለቲካ ጉዳይ ሀላፊ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
<…የየካቲት 12 ሰማዕታት ጉዳይ ሲነሳ በአብዛኛው የሚታወሱት ወይ ስማቸው የሚነሳው አብርሃም ደቦጭና ሞገስ አስገዶም ወጣቶቹ አርበኞች በግራዚያኒ ላይ የመግደል ሙከራ ያደረጉት ናቸው። ባለፈው ዓመት በዚህ ብሮግራም ቦንቡን በቤት ውስጥ ለወጣቶቹ የሰራላቸውን አባ አምዴን አንስተናል። ዘንድሮ ደግሞ በዕለቱ ታላቅ ተግባር የፈጸሙትን ወጣት አርበኞች እናስታውስ። እነዚህም…ታሪክን በታሪክነቱ መውሰድና መረዳት እንጂ ለፖለቲካ ዓላማ መጠቀሚያ ለማድረግ መሞከር አይገባም። አባቶቻችን በብሄር ተከፋፍለው ታሪክ አልሰሩም።መስዋዕትነታቸው በአንድ ላይ ተሪኩም የጋራ ታሪካቸው ነው።ወጣቶች ዛሬ የሚደረገውን ታሪክን የማዛባትም ሆነ የማጥፋት ለመከላከል እውነትን መመርመር የታሪክ መዛግብትን ማገላበት አለባቸው።ይህ ካልሆነ ግን…> ታሪክ ተራኪው ኤድዋርዶ ባይኖሮ የየካቲት 12 ሰማእታት አስመልክቶ ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ ( ሙሉውን ያዳምጡት)

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጎንደር ውስጥ በህወሓት ከአቅሙ በላይ የታጠቀ ጥምር ኃይል ላይ ጥቃት ፈፅሞ ከባድ ጉዳት አደረሰ፡፡ ====================================================


የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት በጎንደር ታች አርማጭሆ ሳንጃ ዶጋው የተባለ ቦታ ውስጥ ይንቀሳቀስ በነበረው እና ከመከላከያ፣ ከልዩ ኃይል፣ ከፀረ-ሽምቅ እና ከሚሊሻ ጦር ተውጣጥቶ በልዩ ሁኔታ የተደራጀ የህወሓት ኃይል ላይ የካቲት 10 2008 ዓ.ም ከቀኑ 5 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት በከፈተው ድንገተኛ ጥቃት ከፍተኛ ድልን ተቀዳጅቷል፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በጥምሩ የህወሓት ኃይል ላይ ድንገተኝነትን በማትረፍ ጠንካራ ምት አሳርፎ 35 ገድሎ 52 በማቁሰል እንዳልነበረ በማድረግ በታትኖታል፡፡

Sunday, February 21, 2016

የቆሰለው አውሬ አገራችንን ይበልጥ ሳያቆስል በጊዜ እንነሳ! February 20, 2016


def-thumb
የንቅናቄያችን ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ በቅርቡ በዋሽንግተን ዲሲ ተገኝተው ለኢትዮጵያውያን ባደረጉት ንግግር ወያኔ የቆሰለ አውሬ ሆኗል ብለው ነበር። ፕ/ር ብርሃኑ በንግግራቸው፣ የቆሰለ አውሬ በህይወት ለመቆየት ሲል ያለ የሌለውን ሃይል በመጠቀም ጥቃት በሰነዘረበት ግለሰብ ላይ የበቀል እርምጃ ከመውሰድ ወደ ሁዋላ የማይል በመሆኑ፣ ጥቃቱን ለመከላከል በቂ ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ አሳስበው ነበር። አውሬነት የጭካኔ ደረጃንና ሁዋላቀርነትን የሚያሳይ ገላጭ ቃል ነው፤ አውሬነት ወያኔ በህዝባችን ላይ ለሚፈጽመው ግፍ ጥሩ ወካይ ቃል ነው፤ ነገር ግን ወያኔ ከአውሬ አልፎ የቆሰለ አውሬ ሆኗል፤ አደገኛነቱም ጨምሯል።

ፕ/ር ብርሃኑ በትክክል እንዳሉት የወያኔ የጥቃት ኢላማዎች ወያኔን የሚታገሉት የነጻነት ሃይሎች ብቻ አይሆኑም። መላው የአገራችን ህዝብ በቆሰለው አውሬ ከመጎዳት አያመልጥም። በነፍስ ግቢና ውጪ መካከል የሚገኘው የቆሰለው አውሬ አፈር ልሶ ከቁስለቱ አገግሞ እንዳይነሳ ጥፋቱን እየተከላከሉ፣ ሞቱ የሚፋጠንበትን መንገድ መቀየስ ከእያንዳንዱ ዜጋ ይጠበቃል። የቆሰለ አውሬ ወዳጅ ጠላት መለየት የማይችል፣ ፊት ለፊት ባገኘው ላይ ሁሉ እርምጃ ለመወሰድ የሚንደፋደፍ በመሆኑ፣ ሁሉም ዜጋ የጥቃት ጥፎሮቹ እሱም ላይ እንደሚያርፉ በመገንዘብ አውሬውን ለማጥፋት መረባረብ ይኖርበታል።

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)


የፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አዛዦች በአዲስ አበባ ስብሰባ አካሄዱ፡፡ ስብሰባው ያለምንም ውጤት በግጭት ተቋጭቷል፡፡ 
የፌደራል ፖሊስ ከፍተኛ አዛዦች በአዲስ አበባ ከየካቲት 9 እስከ 12 2008 ዓ.ም የተሰበሰቡ ሲሆን የመልካም አስተዳደር ችግር፣ የፀጥታ ሁኔታ እና የአባላት መክዳት እያነሱ ከተወያዩባቸው አጀንዳዎች መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡ በስብሰባው ላይ የአማራና የኦሮሞ ተወላጅ አዛዦች "እኛ ከእናንተ የተሻለ የትምህርት ደረጃና ልምድ እያለን ሁሉንም ቦታ ጠቅልላችሁ ይዛችሁት ተገቢው ቦታ አልተሰጠንም..." በማለት ህወሓቶችን ልካቸውን ነግረዋቸዋል፡፡

ህወሓቶች በፌደራል ፖሊስ ተቋም ውስጥ ባሰፈኑት ዘረኝነት ምክንያት ሰራዊቱ በመፍረስ ላይ እንደሚገኝ ስብሰባው ላይ በተደጋጋሚ ተወስቷል፡፡ በውይይቱ ላይ ተቃውሟቸውን ያሰሙ የኦሮሞና አማራ ተወላጅ አመራሮች ከህወሓቶች "የእናስራችኋል" ማስፈራሪያ ደርሷቸዋል፡፡
በመጨረሻም ስብሰባው ወደ ለየለት ንትርክና አምባጓሮ በማምራቱ አብዛኞቹ አዛዦች እንዲበተኑ ተደርገው ውይይቱ በጥቂት ዋና፣ ዋና አመራሮች ለተጨማሪ ጊዜ ተካሂዷል፡፡ የፌደራል ፖሊስ አደረጃጀት ሊፈርስ እንደሚችልም ጭምር ጭምጭምታ ተሰምቷል፡፡
በተያያዘ ዜና የሚከዱ የፌደራል ፖሊስ አባላት ቁጥር አሁንም ከቀን ወደ ቀን እየናረ መምጣቱ እየተነገረ ነው፡፡ በጎንደር ብቻ ቢያንስ በቀን 3 የፌደራል ፖሊስ አባላት እንደሚከዱ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገልፀዋል፡፡

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) የ24ኛ ክፍለ ጦር አባላት በገፍ እየከዱ መሆናቸው ታወቀ፡፡



በሰሜን ምዕራብ የኢትዮጵያ ክፍል በሚንቀሳቀሱ የታጠቁ የነፃነት ድርጅቶች ለረጅም ዓመታት የዘለቀ የሽምቅ ውጊያ ጥቃት ሲደርስበት፣ እስከ ሬጅመንት ድረስ እየተደመሰሰ ሲፈርስና እንደገና በሰው ኃይልና በጦር መሳሪያ በተደጋጋሚ ሲገነባ የኖረው 24ኛ ክፍለ ጦር አባላት በውጊያ በእጅጉ ተሰላችተውና በስርዓቱ ተስፋ ቆርጠው በከፍተኛ ሁኔታ በመክዳት ላይ ናቸው፡፡
በተለይም ደግሞ የሽምቅ ውጊያ ጥቃቶች የመጀመሪያ ገፈት ቀማሽ የሆኑ በሁመራና አካባቢው ሰፍረው የቆዩ ሬጅመንቶች ውልቃቸውን በመቅረታቸው ከአዘዞ እና ጭልጋ ሌሎች ሬጅመንቶችን አንስቶ የመተካት እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡
የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ የነፃነት ድርጅቶች ክንድ እየፈረጠመ መምጣት እና ዕለት ከዕለት በሚያደርጓቸው የሽምቅ ውጊያ ጥቃቶች የሚያሳርፉት ዱላ እየበረታ መሄድ በዋነኝነት አርበኝነት በሚፋፋምበት አካባቢ የሚገኘውን 24ኛ ክፍለ ጦር አፍረክርኮታል፡፡

Saturday, February 20, 2016

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) ‪#‎የህወሓት‬ አገዛዝ የሱዳኑን ድንበር ጉዳይ ሙሉ በሙሉ በጦር ኃይሉ ቁጥጥር ስር እንዲሆን አደረገ፡፡ ===================================================


የወሓት አገዛዝ የሱዳን መንግስት በሽፍትነት ዘመኑ ለዋለለት ውለታ ምላሽና ብረት ያነሱ የነፃነት ድርጅቶች ጠረፍ ለጠረፍ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በመግታቱ ረገድ የሚደረግለትን ትብብር ለማፅናት ከሁመራ እስከ ቤንሻንጉል ጉሙዝ 1600 ኪሎ ሜትር ርዘማኔ ያለው፣ 30 ኪሎ ሜትር ደግሞ ወደ ውስጥ የሚገባ ሰፊና ለም መሬት ቆርሶ ሰጥቷል፡፡

መሬታቸው ተነጥቆ ለሱዳን በመሰጠቱ በ2002 ዓ.ም ብቻ 37 ባለሀብቶች ውልቃቸውን በመቅረት ተፈናቅለዋል፡፡
1. ነጋ ደስታ 21. ማማይ ሽፈራ
2. አስረሱ ደስታ 22. አጥናው አማረ 
3. ተፈሪ 23. ኃይሌ ተክሌ /ቢራ/
4. ጌታቸው 24. ሀጎስ
5. ሰረበ 25. ካሳ እንዳለው
6. ቻሌ ፈንቴ 26. ቻሉ ኑራይኔ
7. አዳነ ባብል 27. ደምለው ኑራይኔ
8. ብርሃኔ ጌታቸው 28. ብዙነህ ፀጋ
9. መለስ አስማማው 29. ግርማው ተዘራ
10. ታፍሮ 30. ገ/መድህን መንግስቴ
11. ጌታቸው ግደይ 31. ጌታቸው ሐጎስ
12. አብርሃም 32. አርአያ
13. ንጉሴ ገ/ሊባኖስ 33. አሰማራው መኮንን
14. ሲሳይ ሽሬ 34. ጌጡ ማለደ
15. አበባው 35. ግደይ አቡሃይ
16. ጌታሁን ሽባባው 36. አለልኝ አጣናው
17. ንጉሴ 37. ፈጠነ አዳነ
18. በያን
19. ደለለኝ መንግስቱ 
20. ስመኘው ብርሃኔ

ስለሆነም በአካባቢው ከፍተኛ ተቃውሞ በመነሳቱ ለረጅም ጊዜ የዘለቀ ግጭት፣ አለመረጋጋትና ውጥረት ሰፍኗል፡፡

Friday, February 19, 2016

ከሕይወት እምሻው .....................................................................# ከሰማኒያ አመታት በፊት ኢትዮጵያዊያን ዘማቾች አይተው የማያውቁትን የአውሮፕላን ድብደባ የገለፁበት ግጥም እንዲህ ይላል፡፡


ከሕይወት እምሻው
.....................................................................#
ከሰማኒያ አመታት በፊት ኢትዮጵያዊያን ዘማቾች አይተው የማያውቁትን የአውሮፕላን ድብደባ የገለፁበት ግጥም እንዲህ ይላል፡፡
.
‹‹በትግራይ ቢመጣ መቼ ይገባ ነበር፣
በጎንደር ቢመጣ መቼ ይገባ ነበር፣
በሸዋ ቢመጣ መቼ ይገባ ነበር፣
በጎጃም ቢመጣ መቼ ይገባ ነበር፣
በሰማይ ላይ መጣ በማናውቀው አገር….››
.
ጣልያኖች በማናውቀው ሀገር በሰማይ መጡብን፡፡
የአድዋን ሽንፈት ለመበቀል ጣልያኖች በአውሮፕላን እና በታንክ የመርዝ ጢስ ሰንቀው፣ ለቂም በቀል ድግስ መጡብን፡፡
.
.
ታንክ ሲያዩ ‹‹አሳማዋ መጣች›› የሚሉት ኢትዮጵያውያን፣
ቦምብን ለማጥፋት በእሳት አቀጣጥለው እንደ ማገዶ ይቆሰቁሱ የነበሩ ኢትዮጵያውያን፣
አውሮፕላንን እንደ ንብ ስለምትጮህ በሴት የሰየሙት ኢትዮጵያዊያን፣ ‹‹በሀገሬን አልቀማም›› ወኔ ብቻ
አመጣጡን ላላወቁት ጠላት በሕይወት
ከመምበርከክ ሞተው መውደቅን መረጡ፡፡
.
.
ፕሮፌሰር ባህሩ ዘውዴ እንዳሉት፤ በእርግጥም የኢትዮጵያውያን እና የጣልያኖችን የጦር አቋም የትዬለሌ ልዩነት ላየ የሚገርመው ነገር የኢትዮጵያውያን መሸነፍ
ሳይሆን ያን ያህል መዋጋታቸው ነው ፡፡ ግን ተዋጉ፡፡
.
.
ኢትዮጵያዊያን በማይገለፅ ጀግንነት ተዋጉ፡፡ ከዚያም አልፎ ለአምስት አመታት ሀገራቸውን በከፊል ቢነጠቁም ጠላት ሰላም አጥቶ፣ ሳይደላው እንዲቀመጥ ብዙ መስዋእትነት ከፍለዋል፡፡
.
.
አምስቱን አመት እፎይ ሳይል እና ሲቅበዘበዝ በየከተማውና በየካምፑ ተወሰኖ እንዲቀር ሺዎች ቆስለዋል፡፡
ሺዎች ደምተዋል፡፡
ሺዎች ሞተዋል፡፡
.
ከነጋ ጠባው ጦርነት ሌላ፤ በ1929 ዓ.ም. የሙሶሎኒን ቀኝ እጅ ግራዚያኒን ለመግደል የተደረገው ድፍርት ባስቆጣው የፋሺስት መንግስት የእብድውሻ ፍርድ የተነሳ የካቲት 12፣ 13 እና 14 …በሶሰት ቀናት ብቻ ሰላሳ ሺህ
ኢትዮጵያዊያን ተረሽነዋል፡፡ ተሰቅለዋል፡፡
.
.
አቤት ባይ በሌለበት በጎጇቸው ሳሉ በእሳት ተለብልበዋል፡፡ በግፍ ተገድለዋል፡፡
በሶስት ቀናት ብቻ ሰላሳ ሺህ ኢትዮጵያውያን ያለርህራሄ ለሞት ተሰጥተዋል፡፡
.
.
ቢሆንም…
የእነሱ አንገት ለገመድ በመሰጠቱ የእኛ አንገት ቀና ብሏል፣
.
በእነሱ በእሳት መለብለብ የእኛ የነፃነት ችቦ በርቷል፣
በእነሱ በግፍ መገደል እኛ በነፃነት ኖረናል እና …
የየካቲት 12፣
የየካቲት 13 እና
የየካቲት 14 ሰማዕታትን መቼም መቼም አንረሳቸውም!
የኦሮሚያ ክልል የጦርነት ቀጠና ሆናለች። እነ ጀነራል ሶሞራ በጭካኔና በግፍ ሕዝቡን በጥይት እያረገፊት ነው"" ባለፉት 3፣ 4 ቀናት ብቻ ቢያንስ ወደ መቶ የሚጠጉ ወገኖቻችን ተገድለዋል። "ቢያንስ" የሚለው ላይ አስመርበታለሁ። ለምን እጅግ በጣም ብዙ የቆሰሉ አሉ። የቆሰለ ሁሉም ይደናል ማለት አይደለም። ሃኩም ሄዶ መሞትም አለ።፡
በጣም ያሳዝናል.....በጣም ልብን ያደማል። አለም በሰለጠነችበት በዚህ 21ኛው አለም፣ እንደ ረሃብ፣ ድርቅ፣ ድህነት የመሳሰሉ የሁላችንም ትኩረት የሚያስፈልጋቸው ችግሮች እያሉን፣ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደሚባለው፣ በአጋዚዎች እጆች ላለፉት 25 አመታት እንደነበረው አሁን ዜጎች እየተገደሉ መሆናቸው በጣም ይሳዝናል።
በሜዳ ላይ ያለውን ሁኔታ እንደሚያሳየው ተቃዉሞው በጣም ተባብሷል። ከአዲስ አበባ ወደ ሃረር ፣ ከአዲስ አበባ ወደ ነቀምቴ ፣ ከነቀምቴ ወደ ጂማ፣ ከሻሸመኔ ወደ ባሌ ....የሚወስዱ መንገዶች ተዘግተዋል። በብዙ ቦታዎች የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኃይሎች በቀጥታ ከፌዴራሎች ጋርም ግብግብ የፈጠሩበት ሁኔታ ነው ያለው። ሰላማዊ የሆነው እንቅስቃሴ፣ ወያኔዎች የኃይል እርምጃ በወሰዱ ቁጥር ወደ አመጽ መሸጋገሩ አይቀርም። እየተሸጋገረም ነው።
አገሪቷ ትልቅ ችግር ላይ ናት !

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) ‪#‎ህወሓት‬ በሚቆጣጠረው አየር ኃይል ውስጥ ከፍተኛ አለመረጋጋትና ውጥረት ሰፍኗል፡፡ የሰባት ዓመት ኮንትራታቸውን የጨረሱ ቁጥር ስፍር የሌላቸው አብራሪዎች፣ ቴክኒሻኖች እና የስታፍ ሰራተኞች የስንብት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ የልምምድ በረራዎች በድሬ ደዋ እንዳይደረጉ ጥብቅ መመሪያ ወርዷል፡፡ ====================================================


ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ በለስ ቀንቶት በ1983 ዓ.ም አገሪቱን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ስር ካዋለ በኋላ በሁለት መንግስታት የተገነባውን፣ ገናና ስምና ዝና ያተረፈውን እና ጠንካራ ተክለ ቁመና የነበረውን የኢትዮጵያ አየር ኃይል በበቀል መንፈስ ተነሳስቶ ሙሉ በሙሉ አፈራርሶ ኦና አስቀርቶታል፡፡ የራሱን የደደቢት ድኩማኖች በውስጡ በመሰግሰግ እንደ አዲስ ሊያዋቅረው ሞክሮ ውጤቱ ፍሬቢስ ሲሆንበት ያለምንም የአገልግሎት ዋጋ ክፍያ በመጥረጊያ ጠራርጎ አውጥቶ የጣላቸውን የቀድሞው ጦር አባላትን በ1990 ዓ.ም ለመመለስና አዳዲስ ወጣቶችን ከዩኒቨርሲቲዎች ለመመልመል ሞክሯል፡፡
ሆኖም ግን በአየር ኃይሉ ውስጥ ስር በሰደደው ዘረኝነት፣ ኢ-ፍትሀዊ አስተዳደር፣ ከዘመኑ ጋር አብሮ የማይሄድ ኋላቀር የአሰለጣጠንና የትምህርት ስርዓት እንዲሁም በተጨማሪ አገዛዙ በህዝቡ ላይ በሚያደርሰው የማያቋርጥ ግፍና በደል ምክንያት በርካታ አብራሪዎች፣ ቴክኒሻኖችና የስታፍ ሰራተኞች ተዋጊ ሄሊኮፕተርና ጀት ጭምር በመያዝ ከአገር በመውጣት በበረሃ እየተደረገ የሚገኘውን የትጥቅ ትግል በመቀላቀል ላይ ይገኛሉ፡፡
አሁን ደግሞ በኦሮምያ ህዝባዊ አመፅ ከተቀሰቀሰ ወዲህ በአየር ኃይል በተለያዩ አየር ምድቦች ውስጥ ከፍተኛ አለመረጋጋት ተከስቷል፡፡ የኦሮምያ ተወላጅ የሆኑ አባላት ከፍተኛ ክትትል እየተደረገባቸው እንደሚገኝም ታውቋል፡፡ ስለዚህም በየቀኑ ከሚጠፉት ባሻገር የሰባት ዓመት ኮንትራት ጊዜያቸውን በመጨረሳቸው የስንብት ጥያቄ የሚያነሱ አብራሪዎች፣ ቴክኒሻኖችና የስታፍ ሰራተኞች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን በእጅጉ እየናረ መጥቷል፡፡ በተለይም ደግሞ በ1994፣ 95፣ 96 እና 97 ዓ.ም የተቀጠሩ አብዛኞቹ ቴክኒሻኖች ሰላማዊ ስንብት የማይደረግላቸው ከሆነ ሌሎቹ እንደሚያደርጉት ከመጥፋት የሚያግዳቸው ምንም ነገር እንደሌለ መናገራቸው ተሰምቷል፡፡
አገዛዙ በአየር ኃይል ውስጥ ተፈጥሮ የቆየውንና አሁን ደግሞ አየተባባሰ የመጣውን የአባላት መጥፋትና የስንብት ጥያቄ ማቅረብ ለማስታገስ የተለያዩ ማባበያዎችን ቢያደርግም ችግሩ ሊፈታ አልቻለም፡፡
በመሆኑም ድሬ ደዋ በሚገኘው ምስራቅ አየር ምድብ ምንም አይነት የበረራ ልምምድ እንዳይደረግ ጥብቅ መመሪያ ተላልፏል፡፡ የበረራ ልምምዱ ወደ ደብረ ዘይት ተዛውሯል፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት ድሬ ደዋ ለጎረቤት አገሮች ቅርብ በመሆኑ እና ለመክዳት አመችነት ስላለው ነው ተብሏል፡፡

Death toll rising in West Arsi, regime using American Humvees to crackdown on protesters, Zenawi’s portrait set ablaze ESAT News (February 18, 2016)


The protest in West Arsi, Oromia region of Ethiopia, continued today despite brutal crackdown by the regime that’s now rolling its American donated Humvees in the streets to boost up its operation against protesters who demanded political and economic rights.
ESAT’s sources in the region say at least 17 people were killed by the Agazi forces, the regime’s snipers, in the last five days of protest in the area that began on Friday when the forces decided to shot at a bus full of wedding goers for the trivial reason that the partiers refused to turn down a music playing on the radio, a favorite song among the protesters. Four were injured in that shooting. Protest against that brutal attack then engulfed Shashemene and the surrounding towns with the local militia responding to fires from the Agazi forces killing at least 7 of them.
Protesters effectively blocked roads in every town to fend off the Agazi forces from reaching their neck of the woods. Reports filed by the Oromo Media Network show regime's forces using helicopters and American Humvees to try to reach the localities.
In this strongest show of resistance against the dictatorial regime in Ethiopia by one of the largest ethnic groups in the country, the minority regime has lost control of the towns in the Oromia region where protesters effectively blocked roads fending off the forces coming to attack them. Protesters in Dodola took down the portrait of Meles Zenawi, Ethiopia’s late dictator, and set it ablaze, in a rare show strong rejection to the system and the minority rule.
“The regime has lost control and this protest is one among numerous manifestations that it has lost credibility; and whatever semblance of legitimacy has vanished,” a close observer of political developments in Ethiopia told ESAT today.
“The tyrannical regime uses not only it’s anti-terrorism law to crackdown on opponents, but also weapons it acquires under the name of fighting terrorists in Somalia, against peaceful protesters,” he added referring to the American Humvees being used to clear the blockages by the protesters.
(Photo: OMN)

Thursday, February 18, 2016

አሜሪካ፣ ኖርዌይና እንግሊዝ በኦሮምያ የጉዞ ማስጠንቀቂያ አወጡ


ኦሮምያ ውስጥ በምሥራቅ ሐረርጌና በምዕራብ አርሲ አካባቢዎች ሰሞኑን የታየው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ዛሬም ቀጥሎ በተለይ በምሥራቅ ሃረርጌ ጉራዋ ሕይወት መጥፋቱ ተሰምቷል።
ዋሽንግተን ዲሲ — 
ኦሮምያ ውስጥ በምሥራቅ ሐረርጌና በምዕራብ አርሲ አካባቢዎች ሰሞኑን የታየው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ዛሬም ቀጥሎ በተለይ በምሥራቅ ሃረርጌ ጉራዋ ሕይወት መጥፋቱ ተሰምቷል።

አርሲ ውስጥ አጄ አካባቢ ደግሞ ተጠልፈው ተወሰዱ የተባሉ የአሥራ አንድ ሰዎች ልብሶች መንገድ ላይ ተጥለው መገኘታቸውንና ሰዎቹ ያሉበት ግን እስከአሁን እንደማይታወቅ፤ ተማሪዎችም ትምህርት ቤት አለመግባታቸውን አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለቪኦኤ ገልፀዋል።
የዩናይትድ ሰቴትስ፣ የኖርዌይና የእንግሊዝ መንግሥታት ዜጎቻቸው ወደ ኦሮምያ የሚያደርጉትን ጉዞ ደጋግመው እንዲያስቡበት ወይም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ኃላፊ ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ትናንት ምሽት ላይ ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አርሲ ውስጥ የተፈጠረውን ግጭት አረጋግጠው የመንግሥቱ ኃይሎች ኦሮምያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን ተናግረዋል።
ለተጨማሪ ከተለያዩ ምንጮች የተገኙ መረጃዎችን ያካተተውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡
አሜሪካ፣ ኖርዌይና እንግሊዝ በኦሮምያ የጉዞ ማስጠንቀቂያ አወጡ (20:52)

Wednesday, February 17, 2016

ህወሓት በፈጠራቸው ድርጅቶች ውስጥ ተኩኖ ህወሓትን ማዳከም አርበኝነት ነው!



አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ ለኢህአዴግ እና አጋር ድርጅቶቹ አባላት የሚከተለው መልዕክት ማስተላለፍ  ይሻል።
def-thumb
ህወሓት ጥቂት አባላትና ደጋፊዎች ይዞ ታላቂቷን ኢትዮጵያ ለማንበርከክ እና ሀብቷን ለመመዝበር  እናንተን መጠቀሚያ ያደረጋችሁ መሆኑን የምታውቁት ነው። እናንተ አባል የሆናችሁባቸው ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴድ የተባሉ ድርጅቶች የራሳቸው ድርጅታዊ ነፃነት የሌላቸው የህወሓት አገልጋዮች መሆናቸው እነሱ ራሳቸው የሚነግሯችሁ ከመሆኑም በላይ እናንተም በዕለት ተዕለት ተግባራችሁ የምትታዘቡት ሀቅ ነው። እነዚህ ድርጅቶች ህወሓትን ለማስደሰት ሲሉ የራሳቸውን ሕዝብ የሚያስሩ፣ የሚገድሉ፣ የሚዘርፉ፣ ከቀየው የሚያፈናቅሉ፣ መኖሪያ ቤቱን የሚያስፈርሱ መሆናቸው እናንተም እየተሳተፋችሁበት ያለ ሥራ ነውና የምታውቁት ነው። “አጋር ድርጅቶች” የሚል ስያሜ የተሰጣችው  አብዴፓ፣ ቤጉህዴፓ፣ ጋህአዴን፣ ሀብሊ እና ኢሶዴፓ “አጋር” ሳይሆን የህወሓት ጀሌዎች መሆናቸው እናንተም እኛም የምናውቀው ነው። እናንተ አባል የሆናችሁባቸው ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደህዴድ፣ አብዴፓ፣ ቤጉህዴፓ፣ ጋህአዴን፣ ሀብሊና ኢሶዴፓ  የተባሉ አድርባይ ድርጅቶች ባይኖሩ ኖሮ ህወሓት ለ24 ዓመታት ኢትዮጵያዊያን እየገደለና እያሰረ፤ እየዘረፈ በውሸት ምርጫና በውሸት ዲሞክራሲ ስም ፍጹም የሆነ ዘረኛ፣ ከፋፋይ፣ አምባገነናዊ ሥርዓት በመላው ኢትዮጵያ ውስጥ ሊያሰፍን ባልቻለም ነበር። ህወሓት በኢትዮጵያዊያን አናት ላይ እንዲፈነጭ እናንተ አባል የሆናችሁባቸው ድርጅቶች አስተዋጽዖ  ከፍተኛ  ነው።