መቶ አለቃ አብዮት ማንጉዳይ ከባልደረባው መቶ አለቃ በኃይሉ ጋር በመሆን ሰኔ 2 1997 ዓ.ም ኤም.አይ 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር በመያዝ የህወሓትን አገዛዝ ተቃውሞ ጅቡቲ ገብቷል፡፡ በ1997 ዓ.ም የተካሄደውን ምርጫ ውጤት መጭበርበር በመቃወም ለሰልፍ አደባባይ የወጡ ኢትዮጵያዊያንን እንዲደበድብ ትዕዛዝ በመሰጠቱ ነበር ይህን እርምጃ የወሰደው፡፡ መቶ አለቃ አብዮት ከባልደረባው በኃይሉ ገብሬ ጋር በጅቡቲ መንግስት ነበር ለህወሓት ተላልፈው የተሰጡት፡፡ ከዚያም ለሦስት ዓመታት ያለምንም ፍርድ በስውር ቦታ ጨለማ ክፍል ውስጥ ታስረው ሰቆቃ እየተፈፀመባቸው ቆዩ... ቀጥሎም መቶ አለቃ አብዮት 15 ዓመት እና መቶ አለቃ በኃይሉ ደግሞ እድሜ ይፍታሽ እስር ተበየነባቸው፡፡
በመጨረሻም መቶ አለቃ አብዮት ማንጉዳይ አራቱን አመታት በዝዋይ እስር ቤት ሦስቱን ዓመታት ደግሞ በቃሊቲ ወህኒ ባጠቃላይ አስር የመከራ ጊዜያትን አሳልፎ ለመፈታት ቻለ፡፡ አብዮት እንደተፈታም ብዙ ሳይቆይ ወደ ኤርትራ በረሃ ወርዶ አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቅሏል፡፡ መቶ አለቃ አብዮት ማንጉዳይ ኤም.አይ 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር ይዘው እንዴት ወደ ጅቡቲ እንደሄዱና ለ10 ዓመታት በህወሓት የተፈፀመበትን ግፍ፣ ሰቆቃና መከራ /የመቶ አለቃ በኃይሉ ገብሬን ጭምር/ ለአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ በዝርዝር ተናግሯል፡፡ በዚህ ገፅ በፅሁፍ በተከታታይ እናቀርባለን፤ በድረ ገፃችንwww.patriotg7.org፣ በሳተላይት ደግሞ በቀጥታ ስርጭት የመቶ አለቃ አብዮት ማንጉዳይን እንዲያዳምጡ እንጋብዛለን፡፡
(ሳተላይት Arab SAt
Freguency 11564
sybol rate 27500
FEC 5/6
polarization Horizontal
No comments:
Post a Comment