Thursday, February 11, 2016

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)




በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም አካባቢዎች እየተካሄደ የሚገኘው ህዝባዊ ትግል የድርጅታችን አርበኝነት አካል እንደሆነና ካለፈው ጥር ወር ጀምሮ ወደ ኤርትራ በረሃዎች እየጎረፈ ትግሉን የሚቀላቀለው ወጣት ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እንደናረ የአርበኞች ግንቦት 7 ፖለቲካ መምሪያ ሃላፊ አርበኛ ታጋይ ዘመነ ካሴ እና የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝባዊ እምቢተኝነት መምሪያ ሃላፊ አርበኛ ታጋይ መንግስቱ ወ/ስላሴ ገለፁ።
የአርበኞች ግንቦት 7 ለአነድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ፖለቲካ መምሪያ ሃላፊ አርበኛ ታጋይ ዘመነ ካሴ የኢትዮጵያ ህዝብ እያደረገው የሚገኘው አመፅ አካባቢው ይለያይ እንጂ አንድ አይነት ነው ብለዋል። በአሁኑ ወቅት ወደ በረሃ ወርዶ የትጥቅ ትግሉን የሚቀላቀለው ወጣት ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨመረና ኤርትራ ውስጥ የምናደርገው የትግል እንቅስቃሴ በተለይም የሰው ሃይላችንን የማጠናከሩ ተግባር ባንዴ የሚተው እንዳልሆነ ወጣቱ ኤርትራ መምጣት ማቆም እንደሌለበት አክለው ገልፀዋል።

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአነድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ህዝባዊ እምቢተኝነት መምሪያ ሃላፊ አርበኛ ታጋይ መንግስቱ ወ/ስላሴ ደግሞ በዚህ ወር ብቻ በህዝባዊ እምቢተኝነት ተደራጅተው የነበሩ ከስልሳ(60) በላይ ወጣቶች ወደ ኤርትራ በረሃ መጥተው ትግሉን እንደተቀላቀሉና ህዝቡን በእምቢተኝነት የማደራጀቱ ተግባር ያልደረሰበት የኢትዮጵያ ክፍል እንደሌለ ተናግረዋል።

No comments:

Post a Comment