Saturday, February 27, 2016

መነበብ ያለበት የጊሼይ ገጠመኝና ግርምታ – በፍራንክፈርት ኤርፖርት ያገኘው ግለሰብ በዋሽንግተን ዲሲ የህውሃት ጄነራል

                        ግርምታመነበብ ያለበት የጊሼይ ገጠመኝና ግርምታ – በፍራንክፈርት ኤርፖርት ያገኘው ግለሰብ በዋሽንግተን ዲሲ የህውሃት ጄነራል

 June 19, 2015
የዛሬ ኣመት ተኩል በቤተሰብ ችግር ምክንያት ሃገር ቤት ሄጄ ስመለስ ፍራንክፉርት ላይ በቺካጎ በኩል ወደ ካሊፎርንያ ግዛቴ የሚወስደኝን ኮኔክሽን ለማግኘት ስጣደፍ በተርሚናሉ ውስጥ አንድ ግራ የገባው የሚመስል ኢትዮጵያዊ አየሁና ሰላም ካልኩት በሁዋላ ወደ ኣሜሪካ ሲጕዋዝ የመጀመሪያው መሆኑን እሱም በቺካጎ በኩል ወደ ሂውስተን የሚሄድ መሆኑን ስለነገረኝ የውጭው ኣለም የመጀመሪያው ለሆነው ኢትዮጵያዊ ወገኔ መርዳት ግዴታየም ኣድርጌ ካረጋጋሁትና ሁለታችንም ኮኔክሽናችንን ካገኘን በሁዋላ በተርሚናሉ ውስጥ ካለው ኣግዳሚ ወንበር ኣረፍ ብለን ጨዋታ ጀመርን። ኢትዮጵያዊው ወንድሜ ስሙን ሲያስተዋውቀኝ የትግራይ ተወላጅ ለመሆኑ ብገነዝብም እስካረጋግጥ ኣልደመደምኩም። ለማረጋገጥ ደግሞ ትግሬ ነህ ወይም ኦሮሞ ነህ ብየ የማይጠይቅ ሰብእና ያለኝ ነኝና ይልቁንም ባስተሳሰረን ኢትዮጵያዊነትና ለሱም እንድራራለት ያስገደደኝን ሰውነት ወይም ሰው መሆኑ ብቻ ላይ አትኩሬ በሰውነቱ ላይ የሚታየው ጠባሳ ( በኣደጋ ይሁን በበሽታ ባላውቅም)የተበላሸ ፊቱና ቆዳውን እያየሁ በሃዘን ስሜት ወደጨዋታ ገባሁ። ወደ ውጭ ሲወጡ አንኩዋን ለመጀመሪያ ጊዜ ለሆናቸውና ለሚደጋጉትም የሚያስቸግሩ ብዙ ነገሮች መኖራቸውን ከተነጋገርን በሁዋላ በቀጥታ እሱና ኢትዮጵያ ኣሁን የተሳሰሩበትን ገመድ መምዘዝ ጀመርኩ ፥ ለዚህም በውጭ የምኖር መሆኔን ሃገር ቤት በቤተሰብ ችግር ደርሼ እየተመለስኩ መሆኑን ከነገርኩት በሁዋላ እሱም ኑሮው ሃገር ቤት አንደሆነ ኣሁን የሚሔደውም ለ ፩ ኣመት ትምህርት አንደሆነ ነገረኝ።

በእድሜ እበልጠዋለሁ ብየ ሰላሰብኩኝ ኣንተ ማለቱን ቀጥያለሁ ። ፩ ኣምት ከሆነ ምንድነው የምታጠናው ብዬ ጠየቅኩት ሚሊታሪ ሳይንስ ነው ሲለኝ ያኔ ወንድሜን ከኢትዮጵያዊ ሰንሰለቶች ወጣ ብየ በፖለቲካ ሰንሰለቶች ውስጥ ማየት የጀመርኩት። ሚሊታሪ ነህ ? ኣዎ::
የሰወነቱ ቆዳዎች ላየ ያየሁት ቃጠሎ ወይም በሃገራችን (ለምጥ የሚባለው)የሚመስል ፊቱን ያበላሽው በጦር ሜዳ ሊሆን ይችላል ወደሚል ግምት ውስጥ ገባሁ። በርስ በርስ ጦርነት ያለቁት ኣካለ ስንኩል የሆኑት ወገኖቼ ሁሉ ታወሱኝ። በእንዲህ ላይ እያለሁ እሱ ወዲያው የፈተና ጥያቀ መግቢያ ኣቀረበልኝ። ኣገር ቤት እንዴት ኣየህው የሚል። ሲናገር ያው እነደ ኣንዳንድ የትግራየ ተወላጆች የኣማርኛ ፊድሎች የራሳቸው ኣገላለጽ ቢኖራቸውም መናገር የሚፈልገወን በኮንፊደንስ የሚናገር ለመሆኑ ተገንዝቤኣለሁ። ይህ ጥያቀው ደግሞ በዲኣስፖራ የሚገኑት ኢትዮጵያውያን ሃገር ቤት ደርሰው ለሚመጡ ኢትዮጵያውያን የሚቀርብ የመጀመሪያ የፖለቲካ ፈተና ጭምር መሆኑን ስለምረዳና ቀጣይነት ያለው ጥያቀም ስለሆነ የራሴን ቅድመ ዝግጅት ያደረግኩበት በመሆኑ ለመልሱ ኣልተችገርኩም። መልሴን የሚያዳምተኝ ማነው ለሚለውም ኣልተጨነኩም። በፖለቲካው ኣለም ብዙ ስለቆየሁበትም ለዚህ ጥያቄም ሆነ በሌላ ሃገራዊ ነክ ጥያቀዎ ላይ ከኣቶ መለስ ዘናዊ ጀምሮ ሌሎች የስራቱ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ጋር በተለያየ ኣጋጣሚ የመወያየት የመጠየቅ እድል ስለነበረኝ መልሴ ምን ያስከትልብኛል ብዬ ኣልሰጋሁም ። ይልቁንም የተስማኝን ከዚህ የስራቱ ኣካል ከሆነው የመከላከያ ሰራዊት ኣባል ጋር መወያየት የበለጠ ኣመለካከቴን ያሰፋልኛል ቢዬ ስላመንኩ ያየሁትን በጎም ሆነ መጠፎ ነገር በተለዪም በቀጥታ ከስራቱ ጋር የማልስማማባቸውን ነገሮች ማንሳት ፈለግኩ። ለመንደርደሪያም ተዘዋውሬ ባየህዋውቸ ኣካባብዎች ኣንዳንድ ያየሁዋቸው የተሰሩ የልማት ስራዎች ማነም ይስራው ማንም ለሃገር ጠቃሚ መሆናችወን : ተደጋግሞ በስራቱ ተቃዋሚዎ ች የሚነሳው የተሰራው የልማት ስራና የህዝቡ የሂይወት ለውጥ ላይ የማዪታይ መሆኑን ተቀጠረው የሚሰሩ ሰራተኞች እንኳን ባ ለው የኑሮ ውድነት ገቢያቸው ስለማይበቃቸ ው ምግብ መግዛት ተስኖኣ ቸው በየለቅሶ ቤት በራቸፍ ላይ ትርፍራፊ የሚለምኑ መሆናቸወን ከራሰ ገጠመኝ በመነሳት ላስረዳው ሞከርኩ ። በገጠርም ሆነ በከተማ ያነጋገርኳ ቸው ኢትዮጵያወያን በዘር መድሎ በፖለትካ ኣስተሳሰብ ልዩነት የሚደርስባቸው መሆኑንና የፍርሃት ድባብ ያጠላበት መሆኑን ለማሳየት ሞከርኩ (ኣያውቀውም በሚል ኣስተሳሰብ ኣይደለም )በቅን የጠየቀኝ ስለምሰለኝ በቅነነት መመለስ ስላለብኝ ነው። ያላግባብ የታሰሩ ኤትዮጵያውያን ጉዳዪም ኣንዱ የፖለቲካው መጥፎ ገጽታ መሆኑን ጠቃቀስኩና ኢሃዴግና በትግሉ የተስውት የትግራይ ልጆች መስዋአትነት ዋጋ ለጥቂቶች ስልጣን መጠበቂያ መሆኑ የሚያሳዝን አንደሆነ ጠቀስኩ። በጽሞና ያዳመጠኝ ተጉዋዥ ጉዋደኛየ ግልጽነቴን የወደደው ዪሁን ኣልያም ከዚህ ቀደም በውጭ የሚገኙ በዲያስፖራ ተቃዋሚነት ስም የሚቀርቡትን የጠቃውሞ ሃሳቦች ኣቀራረብ ችግር በሚያገናዝብ መልኩ ያቀረብኩዋቸውን ሃስባች ኣንዳንዱን በሚስማማ መልኩ ሲቀበለው ኣልፎ ኣልፎም ፊቱን ቀጨም አያደርገ አዳምጦኝ በኣንድ ኣረፍተ ነገር መልስ ቁዋጨብኝ ። ኣዎ ብዙ ች ግሮች ኣሉ ነገር ጊን በሂደት የምንፈታቸውና ኣንዳንዳንዶቹ ም በጥላች ላይ የተመሰረቱ የፖለቲካ ኣካሄዶች መሆናቸወን ሊያስረዳኘ ሞከረ። የበረራ ሰኣታችን ሁለት ሰኣት ስለሚቀረው ቡና ልጋብዘው ብጠይቀው በቅርቡ አንደጠጣ ስለነገረኝ ኣልገፋሁበትም።ጨዋታችንን ቀጠልን ኣሁንም በጥያቀ መልክ ኣስተያየቴን ከሁሉም በላይ ብዙዎቻችን ስሌኢትዮጵያ መከላከያ ሲነሳ የሃገር መከላከያና የስርዓት መከላከያን በወያኔ ኢሃደግ የመከላከያ ሰራዊት ትርጉም እየተርጎምነው ወያኔ የደርግ ሰራዊት ብሎ ለዘመናት የተገነባውን የመከላከያ እሴት ስሩን ነቅሎ ለመተካት ያደረገወን ታላቅ ወንጀል ለመድገም ኣንዳንዶች ኣሁን በሚጣደፉበት ወቅት በመከላከያ ውስጥ ያለውን ስልጣን የማላውቀውን ይህንን ወንድሜን ጠንከር ያለ ጥያቄ ደፍሬ ጠየቁት፧ የኣብዛኛዎች አትዮጵያወያን ስለ ኣሁኑ የመከላከያ ሰራዊት ያላቸው ቅሬታ ከሃያ ኣመት በሁዋላ የሰራዊቱ መሪዎች ለምን የኣንድ ብሄረሰብ ሰዎች ሆኑ የሚለውን ነበር ፤ በርግጥም ለኣንዳንዶቻችን በኣንድ ሰኣት ውይይት እንዴት ይህን የመሰለ ጥያቄ ስልጣኑን ለማላውቀው ሰው እንዳቀረብኩ ሳይገርማችሁ ኣይቀርም። በወቅቱ የነበረኝ ግምት ለትምህርት የሚሄደውን ጎልማሳ እነመንግስቱ ሃይለማርያም መቶኣለቃ ወይም ሻምበል ሆነው ለትምህርት ወደ ኣሜሪካ መላካቸውንና ያም በኣስተሳሰባቸው ላይ ለለውጥ ካነሳሳቸው ምክንያቶች ይጠቅስ ስለነበረ ዪሀንንም ወንድም መቸም ሰው ነወና ጥያቀዬን የቤት ስራ ለማድረግም ነበር ። ታዲያ ኣሁንም ይህ ወንድም በጠያቀዬ ምንም ኣልተደነቀም ። ኣዎ ትክክል ነው ብሎ ጀመረልኝ። ይህ ጥያቀ በሰርዊታችን ውስጥ የሚነሳ ጥያቀ ነው ። በተለይም የህዋሃት ሚናና የተከፈለውን መስዋእትነት ከጦር ሜዳ ውሎዎችና ተሳትፎዎች ኣኩዋያ ዪህ መሆኑ ኣያስደንቅም ። የኣመራር ሚና የብሄረሰቦችን ተሳትፎ ባሳደገ መልኩ መሆን እንዳለበት ኣምናለሁ ለዚህም በርካታ የተለያዩ ብሄረሰብ ኣባሎች ወደኣመራር ሊመጡ የሚችሉበት ሁኔታ እየተመቻቸ ነው የሚል ልክ ኢሃዴግ ለዲሞክራሲ ጥያቄውም የሚሰጠውን በሂደት ላይ ነን የሚለውን መልስ ሰጠኝ። በኣጥቃላይም ስረኣቱን በሚገባ የመከላከል ሃሳብ ቢመስልም በሰውነቱ ውስጥ ግን የሚጋራኝ ችግሮች እንዳሉ ተገነዝብኩ። ወዲያውም ብዙ ሳንቆይ ሁለታችንንም ወደ ቺካጎ የሚበረው ኣውሮጵላን ተሳፈሩ ሲባል አሱም የሱን አውነታ እኔም የራሴን ዪዤ ወደ ኣውሮጵላናችን ገባን ።
ግርምታየ ዋናው ነገር ዘሃበሻ ድህረ ገጽ ኣንድ ዘገባ ላይ የህዋሃት ኢሃዴግ ጀነራሎች ተጋለጡ በሚል ርእስ በቪዲዮ ኣስድግፎ ያወጣውን ስመለከት የህዋሃት ጄኔራሎችን ያማሁለት የፍራንክፈርቱ ኣብሮ ተጉዋዤና የሁለት ሰኣት ጉዋደኛዬ የመከላከያ ሰራዊት ኣባል ለህወሃት ምስረታ በኣል የክብር ተናጋሪ ሆኖ ጄኔራል ማረጉን ገጥግጦ ሳየው በጣም ደስ ኣለኝ ። ከሁሉም በላይ ከኣምስተኛ ክፍል የመጣሁ ኣይደለሁም ብሎ ንጝሩን ሲጀምር ሳቅኩኝ። እውነት ከልቡ ይሆን ያን ያህል ስለሰራቱ ብልሹ ጎኖች ስናገር በጥሞና ያዳመጠኝ ? እውነት የጄኔራል ማረጉን ሳይለብስ ከሌሎች ሃገር ቤት ካሉ ኢትዮጵያውያን ጋር ከኔ ጋር እንዳደረገው በነጻ ያወያይ ይሆን ? እውነት እንዳለው የመከላከያ ሰራዊቱ የሃገር ሰራዊትና ዘብ አንጂ የጥቂት ቡድኖች ጥቅም ኣስጠባቂ ኣለመሆኑ ላይ ወታደራዊ ቁርጠኝነት ይኖረው ይሆን ? ለመሆኑ ከየትም ብሄረስብ ይወለድ ግን ሳየው ሚስኪን ተራ ዜጋ የመሰለኝንና ልቤም የራራችለት በኢትዮጵያዊነቱ መሆኑን የሱም ልብ እንደኔ ኣስቦት ይሆን ? ክቡር ጄኔራልን ዛሬም ባገኘው በጀኔራለነቱ ሳይሆን ያኔ በቀረብኩት መንገድ እንደምቀርበው ኣልጠራጠርም። ለዚህም ነው ምንም ያህል ብንጠላላ የህዝብን ጥቅም ቅድሚያ ከሰጠን ፺ ሚሊዮን ለሚሆነው ህዝባችን መፍትሄ ብሄራዊ መግባባት ያስፈልገናል ። ዪህ ከሆነ ደግሞ መፍትሄም ይገኛል የምንለው ። ቪዲዮውን ከታች ይመልከቱ ።http://www.ethiopanorama.com/?p=8092

No comments:

Post a Comment