Monday, February 22, 2016

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ጎንደር ውስጥ በህወሓት ከአቅሙ በላይ የታጠቀ ጥምር ኃይል ላይ ጥቃት ፈፅሞ ከባድ ጉዳት አደረሰ፡፡ ====================================================


የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ሰራዊት በጎንደር ታች አርማጭሆ ሳንጃ ዶጋው የተባለ ቦታ ውስጥ ይንቀሳቀስ በነበረው እና ከመከላከያ፣ ከልዩ ኃይል፣ ከፀረ-ሽምቅ እና ከሚሊሻ ጦር ተውጣጥቶ በልዩ ሁኔታ የተደራጀ የህወሓት ኃይል ላይ የካቲት 10 2008 ዓ.ም ከቀኑ 5 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት በከፈተው ድንገተኛ ጥቃት ከፍተኛ ድልን ተቀዳጅቷል፡፡

የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በጥምሩ የህወሓት ኃይል ላይ ድንገተኝነትን በማትረፍ ጠንካራ ምት አሳርፎ 35 ገድሎ 52 በማቁሰል እንዳልነበረ በማድረግ በታትኖታል፡፡

No comments:

Post a Comment