Friday, February 5, 2016

በጋምቤላ ውጥረቱ አይሏል * እናት እና ህፃን ልጇ ተገደሉ * ፍኙሩ ከተማ የጦር አውድማ መስላለች (ፎቶዎች ስላሉ ከ18 ዓመት በታች ያሉ እንዳያነቡት)

 Gambela 2የፌደራል መንግስት የኑዌር እና የአኝዋክ ብሄረሰቦችን ለማስታረቅ ከጋምቤላ በስተደቡብ 105 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ፍኙሩ ከተማ ላይ ስብሰባ ጠርቶ ስብሰባው እየተካሄደ ባለበት ወቅት የኑዌር ብሄረሰብ አባላት ድንገት በወሰዱት እርምጃ እናት እና የ2 ዓመት ህፃን ልጇ ዛሬ መገደላቸውን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከስፍራው አስታወቁ::
ዘ-ሐበሻ በስልክ ያነጋገረቻቸው የዓይን እማኞች እንደሚገልጹት ፍኙሩ ከተማ የደቡብ ሱዳን አማጽያን የሪክ ማቻር ወታደሮች የሚኖሩባትና የስደተኞች ካምፕ የሚገኝበት ቦታ እንደሆነ ገልጸው ድንገት ስብሰባው እየተደረገ እርምጃውን የወሰዱት እነዚሁ የሪክ ማቻር ወታደሮች የሆኑ የኑዌር ብሄረሰብ አባላት ናቸው ብለዋል::
የአይን እማኞቹ በፎቶ ግራፍ አስደግፈው በላኩት መረጃ የከ እናት እና ልጅ በተጨማሪ ሌላም አንድ ሰው ሕይወቱ ማለፉን እና በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን ገልጸዋል:: የፌደራል መንግስት ሁለቱን ብሄረሰቦች ለማስማማት ስብሰባ ጠርቶ ኑዌሮች ድንገት እርምጃ ሲወስዱ የፌደራል ወታደሮች ግጭቱን ከማብረድ ይልቅ ዳር ቆመው ይመለከቱ ነበር ሲሉ እነዚሁ የአይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::
በሌላም በኩል በጋምቤላ ኦሚንጋ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር ከ2 ቀናት የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት በጠሩት ስብሰባ ላይ ሕዝቡን ወክሎ በስብሰባ ላይ ሲናገር የነበረውና በቅጽል ስሙ ሶኒ ተብሎ የሚታወቀው ወጣት ዛሬ ባልታወቁ ሰዎች ወገቡን ተምትቶ በጋምቤላ ሆስፒታል ህክምና ላይ እንደሚገኝ ከስፍራው ያገኘነው መረጃ አመልክቷል::
በጋምቤላ በተለይም ከፓንጋ ወደ ፍኙሩ የሪክ ማቻር ስደተኛ ወታደሮች በከፍተኛ ሁኔታ የጦር መሳሪያዎችን እያመላለሱ እንደሚገኝም ለዘ-ሐበሻ የመጣውGambela መረጃ ጨምሮ ገልጿል::

No comments:

Post a Comment