Friday, February 26, 2016

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) አዲስ አበባ ላይ ያልተሳካላቸው የህወሓት አገዛዝ ፌደራል ፖሊስ አዛዦች ባህር ዳር ላይ በድጋሚ ስብሰባ አካሂደው የባሰውን ተበጣበጡ፡፡


የፌደራል ፖሊስ አመራሮቹ ከእሁድ የካቲት 13 እስከ 16 2008 ዓ.ም ድረስ ነው በባህር ዳር ከተማ ምንም አይነት አዎንታዊ ውጤት ያላመጣ ውይይት ለማድረግ የሞከሩት፡፡ በስብሰባው ላይ “ባልተማሩ የህውሓት ታጋዮች አንመራም... ” የሚል ተቃውሞ ተነስቷል፡፡

በልዩ ልዩ የአገሪቱ ክፍሎች የተነሳውን የህዝብ ተቃውሞ የጠብመንጃ ጉልበት ተጠቅሞ ፀጥ የማስኘትን የአገዛዙን የፀና አቋም በሚመለከት ደግሞ በአዛዦች መካከል እስከ አምባጓሮ የዘለቀ አለመግባባት ተከስቶ ነበር፡፡ “ወደ ህዝባችን እንዲተኮስ ትእዛዝ አንሰጥም...“ በማለት በግልፅ ተቃውሟቸውን ያሰሙ በርካታ የፈዴራል ፖሊስ አመራሮች ነበሩ፡፡
በመጨረሻም ስብሰባው እንደተለመደው ያለምንም ውጤት ተበትኗል፡፡ ከስብሰባው በኋላ 4 የፌደራል ፖሊስ አመራሮች ስርአቱን ከድተዋል፡፡ ከአራቱ መካከል አንዱ ኢንስፔክተር ፀጉ ይሰኛል፡፡ አራቱም መኮንኖች እስካሁን የት እንደደረሱ የታወቀ ነገር የለም፡፡

No comments:

Post a Comment