Friday, February 26, 2016

Atse Menelik and Adwa, Poemአደዋ ደረሰ ጎጠኞች ከፋቸው ኢትዮጵያዊነት ሊተረክባቸው ። የአድዋ ድል ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የማንነታችን መሰረትና የህልውናችንም መገለጫ ነው፡፡ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ብቻም ሳይሆን ለመላው የጥቁር ህዝብ የነፃነት ተምሳሌትና የአርነት መስታዎትም ጭምር ነው፡፡ የሰው ልጅ በቆዳው ቀለም ምክንያት መዋረድም ሆነ ማነስ እንደሌለበት፣ ጥቁር ህዝብ በአፈጣጠሩም ሆነ በአስተሳሰቡ ‘ልዩና ድንቅ ነን’ ብለው ከሚኮፈሱት ነጮች ያላነሰ ማንነት እንዳለው፣ ካልነኩት ተንኮል የማይሸርብ ሲነካ ግን በማንነቱ ላይ የማይደራደር ድንቅ ፍጥረት መሆኑ የታየበት ድል ነው የአድዋ ድል፡፡ ዛሬ አለም አብዝታ ስለሰው ልጆች እኩልነት እየሰበከችና በዚህም ስም አያሌ መድረኮችን እያዘጋጀች ቢሆንም ገና ብዙ ያልተፈቱ ተያያዥ ችግሮች እያየን መሆኑ የሚካድ ሃቅ አይደለም፡፡ የአድዋ ድል ግን ገና ያኔ ስልጣኔ ባላደገበት፣ የሰው ልጅ አስተሳሰቡ ባልጎለመሰበት፣ እንኳን ነጮች ጥቁሮች ራሳቸው ባርነት የመፈጠራቸው ዕጣ ፈንታ፣ የአርባ ቀን እድላቸው እንደሆነ አስበው ባርነታቸውን ከእንባቸው ጋር እያጣጣሙ በነበሩበት በዚያ ዘመን… የጥቁርነት ትርጉሙን ፣ የሃገርና ህዝብን ሉአላዊ ክብርን ለመላው አለም በወሬ ሳይሆን በተግባር ያሳየ ዘመን አይሽሬ የመመኪያችን መድረክ ነው የአድዋ ድል፡፡ Atse Menelik and Adwa, Poem

No comments:

Post a Comment