Friday, February 26, 2016

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) የህወሓት አገዛዝ የህዝቡን ትኩረት ለማስቀየር የጦር ኃይሉን ኤርትራ ድንበር አካባቢ ከወዲያ ወዲህ በማተራመስ ጦርነት የሚከፍት በመምሰል የተለመደ የማስመሰል ተግባሩን በማከናወን ላይ ነው፡፡


በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በተለይም በኦሮምያ በህዝባዊ አመፅ እየተናጠ እና በበረሃ በአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት የሽምቅ ውጊያ ጥቃት እየተፈፀመበት የሚገኘው የህወሓት አገዛዝ ከኤርትራ ድንበር ሰፍሮ የቆየውን ጦር ወደ ኋላ፣ በደጀን የነበረውን ደግሞ ወደፊት እንዲሁም በአንድ ግንባር የነበረውን ወደ ሌላ ግንባር የመቀያየር ሲጨንቀው የሚያደርገውን የተለመደ የውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ስራውን እየከለሰው ይገኛል፡፡

ህወሓት ይህን መከላከያ ሰራዊቱን በእጅጉ ያሰለቸና ያማረረ ወዲያ ወዲህ የማተረማመስ በጭንቅ ሲያዝ እያማጠ ደጋግሞ ሲወልደው የኖረውን የተለመደ ተግባሩን አሁን ደግሞ ከሰሞኑ ከበፊቱ በተለየ መልኩ የተያያዘው በኤርትራ ድንበር አጠገብ "የትግራይ ወጣቶች ማንነታቸው ባልታወቀ የታጠቁ ኃይሎች ታፍነው ወደ ኤርትራ ተወስደዋል..." የሚለው ዜና ከተሰራጨ በኋላ ከውስጥ ከራሱ ሰዎች በገጠመው ተቃውሞ የሰፈነውን ውጥረት ለማርገብም ጭምር ነው፡፡
በቅጥፈት የተካነው የሽፍቶች ቡድን ህወሓት እንዲህ የጦር ኃይሉን በኤርትራ ድንበርና አካባቢው እየወሰደ እያመጣ ካተራመሰ በኋላ ተጠለፉ ለተባሉት የትግራይ ወጣቶች "ተመጣጣኝ የሆነ የአፀፋ እርምጃ ወስጃለሁ..." ብሎ በመገናኛ ብዙኃን ለማስነገር ማቀዱን ለአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ከውስጥ ምንጮች የተላከው መረጃ ይጠቁማል፡፡

No comments:

Post a Comment