Friday, February 5, 2016

በኢትዮጵያ ውስጥ ህዝቡ ፔፕሲ እንዳይጠጣ ተጠየቀ

 በኢትዮጵያ ውስጥ አላግባብ የሕዝብን ሃብት ከሕወሓት መንግስት ጋር በመተባበር ዘርፈዋል እየተባሉ በሰፊው ተቃውሞ የሚቀርብባቸው ሼህ መሀመድ አላሙዲ ንብረት የሆነውን ፔፕሲን እና የፔፕሲ ምርቶችን ሕዝቡ ያለመጠጣት ተአቅቦ እንዲደረግ እንቅስቃሴ ተጀመረ::
በሶሻል ሚድያዎች እና በስልክ መል ዕክቶች በሃገሪቱ በሰፊው እየተካሄደ ባለው በዚህ ቅስቅሳ ‘ቦይኮት ፔፕሲ’ የሚል ጽሁፍ ያለበት እና ከአጠገቡም የአላሙዲን ምስል ያለበት ነው:: የዚህ ቅስቀሳ አስተባበሪዎች በአሁኑ ወቅት የኦሮሞ ሕዝብን እንቅስቃሴ እያካሄደ ያለው ሕዝብ መሆኑ ታውቋል::
በአማራ ክልል ከዚህ ቀደም አቶ አለምነው መኮንን የአማራውን ሕዝብ በስብሰባ ላይ ክብሩን በሚነካ መንገድ ከተሳደቡ በኋላ ሕዝቡ የብ አዴን ንብረት የሆነውን ዳሸን ቢራን አንጠጣም በሚል ቦይኮት መጥራቱ ይታወሳል:: አሁን አላሙዲ በኦሮሚያ የወርቅ ማዕድኑን ሳይቀር መውሰዳቸውን ተከትሎ በተጠራው ሕዝባዊ የአላሙዲንን ምርቶች የመጠቀም እቀባ በሌሎችም ላይ እንደሚቀጥል ይጠበቃል ተብሏል::
በሶሻል ሚድያዎች እና በኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች ሕዝቡ ፔፕሲ እንዳይጠጣ/ መጠጣት እንዲያቆም የሚጠይቀው በራሪ ወረቀትን ከላይ ለግንዛቤ አቅርበነዋል::
በምርቶች ላይ ያለመጠቀም ተአቅቦ (ቦይኮት) የሰላማዊ ትግል አንዱ አካል መሆኑን ፖለቲከኞች ያሰምሩበታል::12654111_767726366661154_1300336201884149680_n

No comments:

Post a Comment