Thursday, February 4, 2016

እረ ለመሆኑ ደመቀ መኮነን ማን ነው? እዉን አማራ ነውን? – ሰርካለም ጌታሁን


Demeke
ደመቀ መኮነን
ደመቀ መኮነን ሀሰን የተወለደው ላኮመልዛ ውስጥ ነው። አባቱ አቶ መኮንን ሀሰን በሽመና እና ግብርና ሙያ የሚተዳደሩ የነበሩ ሲሆን ችግርና መከራ ከቤታቸው ተሰውሮ እንደማያቅ የሚአውቁአቸው ይመሰክራሉ። ለብአዴን አባልነት ሲመለመል የሞላው ቅፅ እንደሚአመለክተው በናቱ በኩል የኦሮሞ ተወላጅ ነው። ደርግ ምስጋና ይግባውና በረሀብና በችግር ሲጠበስ የነበረውን የነአቶ መኮንን ሀሰን ቤተሰብን በመንደር ምስረታ ፕሮግራሙ ከላኮመልዛ አንስቶ ጎጃም ቻግኒ ውስጥ አምጥተው አሰፈሮአቸው።
አቶ መኮንንም የሽመና ሙያውን ወደጎን ትተው ግብርናው ላይ በመበርታት በልቶ ለማደር ብቻ ሳይሆን ልጆቻቸውንም አስተምሮ ለወግ ለማረግ ለማድረስ በቁ። ደመቀም በአዲስ አበባ ዬንቨርስቲ የሳይንስ ፋኩልቲ ውስጥ ገብቶም በባዮሎጅ የመጀመሪያ ድግሪ ያዘ። በዚህ ግዜ ነው እንግዲህ ማሩ ከበደ የተባለ ግለሰብ የተዋወቀው። ማሩ ተወልዶ ያደገው ጎንደር ውስጥ ጠዳ የሚባል ቦታ ነው። እንደ ደመቀ የመጀመሪያ ድግሪውን በባዮሎጅ ይዞ ነበር። የደመቀ የዮንቨርሲቲ ጒደኛ ማሩ ዛሪ በሂወት የለም። ከነባለቤቱ ኤድስ የሚባል ቀሳፊ ከቀሰፋቸው ሰነበተ። ማሩ ከደመቀ ቀድሞ በመወየኑ ከፍ ያለ ስልጣን ነበረው። ሚስቱም ለተወሰነ ጊዜ በርሀ ስለነበረች ለሱአም ውለታ ተብሎ ማሩ የብአዴን ምሁራን ምልመላና ማደራጃ መምሪያ ዎና ተጠሪ ነበር። ትልቅ ስልጣን ነው። ማሩ ድጋፍ ካልሰጠ ማንም የአማራ ምሁር ሹመት አይሰጠውም ነበር። ወደ ማሩና ደመቀ ግንኙነት እመለሳለው።
ደመቀም ጎጃም ቡሪ አስተማሪ ሆነ። እዛ እያስተማረ እያለ ለአቅም አዳም ያልደረሰች ተማሪ ማርክ እጨምርልሻለው ብሎ በማታለል ደፈራት። የልጅቱ ቤተሰቦች እጅግ አበዱ ደመቀንም እንገላለን ብለው መግቢያ መውጫ አሳጡት። ሽማግሌ ገባና ” በቃ ተውት ምን ይደረጋል” ብሎ ሸመገለና ደመቀ ይቅርታ ጠይቆ ልጅቱን እንዲአገባት ተደረገ። እርሱአም የዛሪ ባለቤቱ እና የሶስት ልጆች እናት ወይዘሮ አለሚቱ ካሳየ ናት።
ይህ ከሆነ በሁዋለ ደመቀ በዪኒቨርስቲ ጉአደኛው ማሩ ተመልምሎ ብአዴንን ተቀላቀለ። ማሩ በሰጠው የምስክርነት ቃልም ወደ ውጭ ለትምህርት ተላከ ተመልሶም ይህው አልጋ ባልጋ ተረማምዶ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ተባለ። ደመቀ ጫት ይወዳል። ያለጫት አይንቀሳቀስም። በባህሪውም እጅግ አድርባይና የራሱ የሆነ አቁዋም የሌለው ግለሰብ ነው። አያሌው ጎበዜ አንድ ጊዜ “የበረከት ተላላኪ” ብሎ ሰድቦት በሂስ ይቅርታ ጠይቆ ታልፎአል። መለስም ለበረከት በተደጋጋሚ “ይህን ልጅ አላምነውም። ቀዥቃዣ ነገር ነው” ሲል ስለ ደመቀ ያለውን አመለካከት ተናግሯል ። ደመቀ የኢትዮጵያ መሪት ለሱዳን እንዲሰጥ ከመለስ ቀጥሎ ፌርማ ያስቀመጠ ግለሰብ መሆኑም የአደባባይ ሚስጥር።
አበቃሁ። ከዚህ በላይ በአንድ በማይረባ እቃ በሆነ ሰው ላይ ግዜ ማጥፋት ያለብኝ አይመስለኝም። ለፍርድ ሲቀርብ እመለስበታለሁ ።Demeke

No comments:

Post a Comment