Sunday, February 28, 2016

ዳግማዊ ምንሊክ እና የአድዋ ድል ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የማንነታችን መሰረትና የህልውናችን መገለጫ ... አደዋ ደረሰ! ጎጠኞች ከፋቸው! ኢትዮጵያዊነት ሊተረክባቸው!!

ከባንዳ ሁሉ የበለጠ የሚዶክከኝ ከባንዳ አያቶቹ የክህደት ታሪክ እራሱን አርቆ የራሱን የጀግንነት ታሪክ በመጻፍ ፋንታ የምንተ እፍረቱን የባንዳ አያቶቹን ቅሌት ሊሸፋፍን እና ሊያወድስ የሚቀባጥር ባንዳ ነው። ጀግንነትም ሆነ ክህደት በደም ይወረሳል የሚል እምነ የለኝም። የጀግና ልጅ እንዳባቱ ጀግና ካልሆነ ሙገሳ፣ የባንዳም ልጅ እንዳባቱ ባንዳ ሆኖ ካልተገኘ ወቀሳ ይገባቸዋል ብዬ አላምንም። ሁላችንም በግዜያችን ባለን አቋም እና ስራ መለካት ይኖርብናል-ፍትሃዊ የሆነ አመለካከት ነው ብዬ አምናለሁ።

የሚያሳዝነው እውነታ ግን የአድዋ ድል አንድ ቀን እየቀረበ በመጣ ቁጥር ሃፍረተ ቢስ የባንዳ የልጅ ልጆች በደም ስራቸው የሚተራመሰው የሃፍረት ውርስ የባሰውኑ በባንድነት እና ክህደት ያጦዛቸው መሄዱ ነው።ምን ጀግና እና ታላቅ ቢሆንም ማንም መሪ ከህዝ ትችት በላይ ሊሆን አይችልም። በሚገባው ቦታ እና ሊተች ሊወቀስ በሚችልበ ነገር ይተቻል ይወቀሳ ። ነገር በጥቁር ህዝብ ታሪክ ለዘላለም አንጸባራቂ የድል ኮከብ ሆኖ የሚኖረው የአድዋን ድል የመሩትን አጼ ምኒልክን ከአድዋ ጦርነት እና ከዛጋር በተያያዘ ለመውቀስ መሞከር ለውይይት የሚያበቃ የታሪክ ግንዛቤ ከጎደለው መሃይም ወይንም ባንዳ አያቱ እግር ስር ተቀምጦ የቤተሰቡን የክህደት ታሪክ እየሰማ በቅናት ሲጠበስ ከኖረ ግልገል ባንዳ እንጂ ከማንም ሌላ ዜጋ አይጠበቅም።

ምንም እንኳን በታሪክ አጋጣሚ በግዜው እምየ ምኒልክ የኢትዩጵያ ሃገራችን ንጉስ ሆነው በአድዋን ድል በመሪነት ቢሳተፉበት እና ስማቸው ቢጠራም፡ ተከትሏቸው ዘምቶ በአድዋ ገደል እና ሜዳ ወድቀው የቀሩት ኢትዩጵያውያን አርበኞች ያንድ ብሄር ልጆች ሳይሆኑ ከኤርትራ ሳይቀር ከእያንዳንዱ የሃገራችን ክፍል የተሰባሰቡ ልበ ሙሉ ሃገር ወዳድ ኢትዩጵያውያን እንደሆኑ አይካድም። ይህን የጋራ የድል ታሪካችን በጋራ እንደማክበር የተወሰኑ ባንዶች ዛሬም እንደ አያቶቻቸው ከETV እስከ ፌስቡክ እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋዕማት ተሰግስገው ሁኔታወችን ባላገናዘበ ተራ ዘረኝነት እና ቅናት አጼ ምኒልክ ለምን ዘልቀው ወደ ኤርትራ ምድር ገብተው ጣልያንን ከመረብ ምላሽ አላስወጡም ብለው መክሰስ ብቻ ሳይሆን የአድዋን ድልም ለማኮሰስ እና ግማሽ ድል ብለው ለመውቀስ ይዳዳቸዋል። ይሄን ጥያቄ ከግል ጥላቻ እና የባንዳነት ዝንባሌ ተነስተው የሚያነሱ (በተለይ የህወሃት ጀሌ እና ካድሬወች)መልሱ ቋቅ ሊላቸው ቢችልም የሚከተሉትን ጥያቄወች እንዲያላምጡ እንጋብዛቸዋለን፡

1)ምኒልክ ከመሃል ሃገር ወራት ገስግሰው የረባ መሳሪያ እና በቂ ስንቅ ያልያዘውን የገበሬ ጦር መርተው አድዋ እስኪደርሱ የእናንተ አያቶች (ትልቁ ምሳሌ የመለስ ዜናዊ አያት) የተወለዱባትን አድዋን ትተው በጣልያን እጅ ከነበረችው መረብ ምላሽ ምን ሊሰሩ ከተሙ? ምነው ይሄ ለትችት የሚቸኩል ምላሳችሁ እንደ አሉላ አባነጋ የትግራይን ገበሬ አስተባብረው እና አበረታትተው ወራሪን ለመመከት ማዘጋጀታቸው ትተው ህዝባቸው ባደባባይ ያለ መሪ እና ሰብሳቢ ትተው ለጣልያን ያገበደዱት መኳንንት እና መሳፍንት አያቶቻችሁ ላይ ሲደርስ ዶለዶመ። ስም እየጠራን እንዘርዝር እንዴ ከሃዲ መሳፍንት አያቶቻችሁን?

2) በወቅቱ የአለም ሚድያወች የአድዋ ድል ማመን ያልቻሉበት እና ጉድ ያሰኛቸው ብዙ ምክንያቶች ነበሩ። ከእነዚህም ውስጥ ቀዳሚው ምክንያት በግዜው የፋሽስት ጣልያን በነበረው የቴክኖሎጂ የበላይነት እና የወታደራዊ ዝግጅት እንኳን እንደ ኢትዩጵያ ያለ መደበኛ ሰራዊት የሌለውን፣ ከጦር ጎራዴ ያላለፈ ጥንታዊ መሳሪያ የያዘ ገበሬ ወታደር ይቅርና እስከ ጥግ ድረስ በዘመናዊ መሳሪያ እና ወታደራዊ ስልት የበሰሉትን የወቅቱን ሃያል ሃገሮችም ቢሆን የሚያስፈራ እና ገናና ስለነበረ ነው። መትረየስ እንዴት በጋሻ ይመከታል ?እናም ይሄን እስከ ጥርሱ የታጠቀን ሃይል በመለስ ዜና የትውልድ መንደር አድዋ መክቶ ለማቆም በሺ የሚቆጠር የመሃል ሃገር ገበሬ ደረት እና ግንባር ነበረ የጥይት ማብረጃ ሆኖ የመከተው። በእርሃብ እና በበሽታ የተጎሳቆለ ይሄ የገበሬ ሰራዊት አድዋ ላይ በሰራው ታዕምር (እደግመዋለሁ አንጸባራቂ ታዕምር) ማድነቅ እና ማመስገን ቢቀር ለምን የሚሸሸውን የጣልያንን ጦር ለአመታት ከመሽገበት እና ከሃገሬው ከብቻ ከሰማንያ ሺ በላይ አስካሪስ መልምሎ ግምብ ሰርቶ የሚጠብቅበት መረብ ምላሽ ድረስ ተከትሎ አልገባም ማለት እብደት እንጂ ሌላ ምንም ትርጉም የለውም።

እንዴት ነው በአድዋ ጦርነት ዋዜማ ሰራዊቱ በጣልያን ጥይት እንደ ቅጠል እረግፎ፣ ስንቁ ተሟጦ ቁስለኛው ተሸካሚ እና ውሃ አቅራቢ እያጣ በየሜዳው የሚሞትበት የተመናመነ እና የተዳከመው የምኒልክ ሰራዊት ጣልያንን ቀፎው መረብ ምላሽ ድረስ ሄዶ ድል ያደርግ ተብሎ የሚጠበቀው? ወይንስ ይሄ ጭልጥ ያለ ለምን ተረፉ ከሚል የጥላቻ ስሜት የመነጨ ምክር ነው?

ይሁን እንበል እና ምኒልክ የሚሸሸውን የጣልያን ጦር ተከታትለው መረብምላሽ ቢገቡ እና የጣልያን ሰራዊት ከኋላ ድጋፍ ሰራዊት፣ ስንቅ እና ትጥቅ አግኝቶ የተሳካ የመልሶ ማጥቃት እርምጃ ቢወስድ፡ ጣልያን እዛው መረብ ምላሽ ይቀር ነበረ እንዴ? ጣልያኖቹን በእልህ እና ከአለም መሳለቂያነት ለመዳን ወደ ኋላ ገፍተው እንደገና አድዋን እና ሌላውን የተቀረውን የኢትዩጵያ ግዛት ዘልቀው ለመግባት የሚያግዳቸው ምን ሃይል ነበረ? የአድዋ ታሪስ ምን ተብሎ ይጻፍ ነበረ?

እናም እናንተ የአስረስ ተሰማ የልጅ ልጆች እነ መለስ ዜናዊወች ሆይ-- ሌላው ቢቀር ስማችሁ “መለስ ዜናዊ” መሆኑ ቀርቶ “Malisimo Gra-Zenawi" ከመባል የተረፈው በምኒልክ እና ምኒልክ በመራው ዛሬ እንደጠላት ታሪኩን ጭቃ ለመቀባት በምትረባረቡበ ታላቅ የኢትዩጵያ ገበሬ አርበኛ መስዋዕትነት መሆኑን አትዘንጉ። አንዘነጋም የብዙወቻችሁ አያቶቻች በጣሊያን ተባርከው ማርዮ እና ሉቺያኖ ተብለው በባርነት ታሪክ የሚኮሩ የመረብ ምላሽ ፓስታ ጎታቶች ነበሩ። ምርጫችሁ ያ ከሆነ ዛሬም ማጎብደድ እና ለነጭ ሎሌ ከመሆን የሚከለክላችሁ የለም። ለእኛ በታሪካችን ለምንኮራ በምኒልክ የተመሩ ገበሬ አያቶቻችን በባዶ እግራቸው አድዋ ላይ ባስመዘገቡት ታዕምረኛ እና ታሪካዊ ድል ለምንኮራ ኢትዩጵያውያን ግን ሃፍረት የለሽ የታሪክ ስረዛ ብረዛችሁን ባታገሱብን መልካም ነው። እንደ ወናፍ ታናፋላችሁ እንጂ አያቶቻችን የኖሩትን አባቶቻች መዝግበው ያቆዩንን እኛም በደም ስራችን ሰርጾ በክብር የሚያኖረንን ታሪካችንን በእናንተ ፕሮፓጋንዳ አንለውጠው ።http://mereja.com/forum/viewtopic.php?f=2&t=73398&start=10


አምና አድዋ! ዘንድሮ አድዋ! ከርሞም አድዋ ! ክብራችን ነው!!
ምን ግዜም ክብር ለእምዬ ምኒልክ እና ለአርበኛ አያቶቻችን !!

No comments:

Post a Comment