Thursday, February 18, 2016

አሜሪካ፣ ኖርዌይና እንግሊዝ በኦሮምያ የጉዞ ማስጠንቀቂያ አወጡ


ኦሮምያ ውስጥ በምሥራቅ ሐረርጌና በምዕራብ አርሲ አካባቢዎች ሰሞኑን የታየው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ዛሬም ቀጥሎ በተለይ በምሥራቅ ሃረርጌ ጉራዋ ሕይወት መጥፋቱ ተሰምቷል።
ዋሽንግተን ዲሲ — 
ኦሮምያ ውስጥ በምሥራቅ ሐረርጌና በምዕራብ አርሲ አካባቢዎች ሰሞኑን የታየው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ዛሬም ቀጥሎ በተለይ በምሥራቅ ሃረርጌ ጉራዋ ሕይወት መጥፋቱ ተሰምቷል።

አርሲ ውስጥ አጄ አካባቢ ደግሞ ተጠልፈው ተወሰዱ የተባሉ የአሥራ አንድ ሰዎች ልብሶች መንገድ ላይ ተጥለው መገኘታቸውንና ሰዎቹ ያሉበት ግን እስከአሁን እንደማይታወቅ፤ ተማሪዎችም ትምህርት ቤት አለመግባታቸውን አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለቪኦኤ ገልፀዋል።
የዩናይትድ ሰቴትስ፣ የኖርዌይና የእንግሊዝ መንግሥታት ዜጎቻቸው ወደ ኦሮምያ የሚያደርጉትን ጉዞ ደጋግመው እንዲያስቡበት ወይም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ኃላፊ ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ትናንት ምሽት ላይ ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አርሲ ውስጥ የተፈጠረውን ግጭት አረጋግጠው የመንግሥቱ ኃይሎች ኦሮምያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን ተናግረዋል።
ለተጨማሪ ከተለያዩ ምንጮች የተገኙ መረጃዎችን ያካተተውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡
አሜሪካ፣ ኖርዌይና እንግሊዝ በኦሮምያ የጉዞ ማስጠንቀቂያ አወጡ (20:52)

No comments:

Post a Comment