Saturday, December 31, 2016

አቶ አለበል አማረ በጲላጦስ ወንበር ይቀመጡ ይሆን ?! አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ እንዳይሆን…

አባይ ሚዲያ
አቶ አለበል አማረ በጲላጦስ ወንበር ይቀመጡ ይሆን ?!
አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ እንዳይሆን…
(መስቀሉ አየለ)

ሰው በስነፍትረት አንድ ብሎ እንደ ማህበረሰብ በህገ ልቦና ሲኖር እንዲሆን የታዘዘው ትንፋሹ እስካለ ድረስ ለቃል ኪዳን ሚስቱ ታማኝ ሆኖ እንዲኖር ነበር። ነገር ግን ግዜው የወንዶች የበላይነት የገነነበት፣ ስርአተ አልበኝንት ልክ ያጣበት፣ የሰው ህይወት ተክለሃይሞኖት አጠገብ አውራ ጎዳና የጣለውን አሮጌ የካርታሜ በርሚል ያህል እንኳን ለአይን የማይቆረቁር ተራ ነገር በሆነበት በዚያ የጨለማ ዘመን፤ ያለዝሙት ምክንያት ሚስቱን የፈታ የሚል ህግ እንቅፋት ይሆንባቸው ነበረና ባሎች ሚስቶቻቸውን ሊፈቱ ሲፈልጉ ማድረግ የሚጠበቅባቸው አንድ ነገር ብቻ ነው፤ ሶስት የሃሰት ምስክር ፈልጎ ዝሙት ስ ትፈጽም አገኘናት ብሎ መክሰስ፤ በቃ፤ የሙሴ ህግ ለድርድር የሚቀርብ አልነበረምና እራሱዋን በማትከላከልበት ሁኔታ ባልገባት ነገር ተጠርንፋ በህግ ስም የሰዎችን ክፉ ምኞት ለመሙላት ሲባል ብቻ በዲንጋይ ተወግራ ትሞታለች። ሙሴ የልባችሁን ጥንካሬ አይቶ “ባይሆን ስለ በድሉዋ የፍችዋን ወረቀት ስጡዋት” ብሎ ኢፍትሃዊነትን ለማስታርቅ ስለሄደበት የመንገድ እርቀት ክርስቶስ በመዋእለ ስጋዌ ሳለ ገልጦባቸው ነበረና።

Friday, December 30, 2016

የትንሳዔ ሬድዮ የዕለተ አርብ ፕሮግራም፣ ወቅታዊ ዜና፣ ሌሎችም መደበኛ ፕሮግራሞች ትንሳዔ ለኢትዮጵያ!!Tensae Radio Dec 30 2016

እኔ ለነጻንቴ! ዓለም አቀፍ “የአንድነትና የዴሞክራሲ ትግል ድጋፍ” ዝግጅት

December 30, 2016
30+ ከተሞች በአንድ ላይ ቅዳሜና እሁድ ፌብሯሪ 11 እና 12 2017 ዓ.ም.

በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ለአንድነትና ለዴሞክርሲ የሚደረገው ትግል ወደ ወሳኝ ም ዕራፍ እየተሸጋገረ ይገኛል። ይህንን ትግል ወደ ወሳኝ ም ዕራፍ በመግባቱ ምክንያት ከመቴው ጊዜ ይልቅ የሚያስፈልገው ዋጋ እየጨመረ መጥቷል። በእየለቱ በርካታ ታጋዮች የወያኔ ዘረኛ አምባገነን ቡድንን አስወግዶ …..

Thursday, December 29, 2016

በቁማችን ተሸጠን እያለቅን ነው | ሊነበብ የሚገባው ጥብቅ መረጃ


‘ባህርዳር’ ተብላ የምትጠራው የካርጎ መርከብ
ለኢሃድግ ጽህፈት ቤት ለፓርላማ አባላት ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ለሚመለከታቸው ሁሉ
የዛሬ 7 ዓመት ገደማ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ እንደተለመደው አንድ አገርን ለውጪ ሰው የመሸጥ ወንጀል ፈጽመዋል። ይኸውም የባህረኛ ማሰልጠኛ ተቋም በኢትዮጵያ ባህርዳር እንዲገነባ በሚፈቀድበት ጊዜ ለ30 ዓመታት የዚህ ዓይነት ትምህርት ቤት በአገሪቱ ሌላ ማንም እንዳይገነባና ይህ ኩባንያ ብቻ እንዲሆን አገሪቱን ግዴታ ማስገባታቸው ነው።
ጉዳዩ የሚመለከታቸው የበታች አካላት ይህንን ቢቃወሙም ማስፈራሪያ እየደረሳቸው የ30 ዓመቱ ጊዜ ወደ 15 ዝቅ እንዲል አስደርገዋል። ይህ ኩባንያ ይህ ብቻ ሳይሆን በአገሪቱ ለፖሊስ እንኳን የማይፈቀድ እንደ ውሸት መመርመሪያ መሳሪያ እንዲያስገባ፣ የአገሪቱ ቀረጥ ከፋይ ያስገነባቸውን ትምህርት ቤቶችና ምርጥ ተማሪዎችን በመመልመልና ወደ ውጪ በመላክ ከፍተኛ የሆነ ጥቅም ከማጋባሱም በላይ፣ እነዚህን ልጆች በአብዛኛው በኢትዮጵያ ህዝብ ሃብት ለማሰልጠን አንድ ሚሊዮን ብር የሚያህል እዳ በማስፈረም በመሰረቱ ባሪያ ሆነው እንዲሰሩ ያስገድዳቸዋል።

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በሽብርተኝነት ወንጀል ሊከሰሱ ነው። ታኅሣሥ ፳ (ሃያ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-

Bilderesultat for መራራ ጉዲናባለፈው ወር በብራሰልስ አውሮፓ ህብረት ፓርላማ ለስብሰባ መጥተው ሲመለሱ ለእስር የተዳረጉት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በሽብርተኝነት ሊከሰሱ መሆናቸውን  ምንጮች ገልጸዋል።
ፕሮፌሰር መረራ  ከሁለት ሳምንታት በፊት ፍርድ ቤት ቀርበው የ28 ቀን ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ወደ ማእከላዊ የተመለሱ ሲሆን፤ መርማሪዎች የኢሜይልና የፌስቡክ አካውንታቸውን አስገድደው በመውሰድ  በሽብርተኝነት ሊያስከሣቸው ይችላሉ ብለው የሚያሥቧቸውን መረጃዎች እያሰባሰቡ ይገኛሉ። እንደ ኢሳት የውስጥ ምንጮች ዘገባ፤ የፕሮፌሰር መረራን ጉዳይ በዋነኝነት የያዘው  የፌዴራል ፖሊስ አባል የሆነው የሽብር ምርመራ ዳይሬክተሩ ኮማንደ ተክላይ ነው።
የፕሮፌሰር መረራ ምክትል የሆኑት የኦሮሞ ፌዴራሊስ ኮንግረስ ምክትል ሰብሳቢ አቶ በቀለ ገርባ በተመሣሳይ ወደ አሜሪካ ለስብሰባ አቅንተው ሲመለሱ በሽብርተኝነት ተከሰው መታሰራቸው ይታወቃል።
በፕሮፌሰር መረራ እስር ጉዳይ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ፕሬዚዳንት በቀጥታ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ደብዳቤ ቢጽፉም፤ አገዛዙ  ይባስ ብሎ ፕሮፌሰሩን በሽብርተኝነት ለመክሰስ መዘጋጀቱ ፤በህብረቱና በህወኃት- ኢህአዴግ መንግስት መካከል ያለውንና ቀዝቀዝ እያለ የመጣውን ግንኙነት ይበልጥ ያሻክረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

“ኢትዮጵያን አፈራርሰን ኦሮሚያን እንገነጥላለን” – በበታችነት ሕመም የተጠቁ አሳዛኝ ፍጡሮች ባዶ ጩኸት!

ከሸግዬ ነብሮ (ኢጆሌ ባሌ)
“ሀገር አጥፊው አረም በሀገሬ ሲስፋፋ፣
ሁሉም ተዳከመ የሚያርመው ጠፋ፣
የጊዜ ጉዳይ ነው እኔ አለቆርጥም ተስፋ፣
ሀገሬ ነው የሚል ኢትዮጵያዊ ሁሉ፣
ጥቃቱ ይሰማው ሲቆረስ አካሉ።”

ከሊቀ ማዕመራን አበባው ይግዛው “ወይ ሀገሬ” ከሚለው ግጥም የተወሰደ።
የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች አፍሪካን እንደ ቅርጫ ሥጋ ለመቀራመት በተነሱበት ወቅት በተለያዩ ሀገሮች እገራቸውን ያስገቡት በሀይማኖት አስተማሪነት ሰም የቄስ ካባ አልብሰው የመረጃ (ሰላይ) ሰዎቻቸውን በመላክ ነው።
London Oromo Conference
ማርቲን ሉተር የተባለው የተባለው የጀርመን የሀይማኖት ሊቅ እ.ኢ.አ. በ1517 የፕሮቴስታንት ሃይማኖት መሻሻል አለበት በሚል ያቀረበው ፅንሰ ሃሳብ ተቀባይነት አግኝቶ ዛሬ ሉተራን የሚባል የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ዋናው ቅርንጫፍ እንዲፈጠር አድርጓል። እዚህ ላይ የሉተራን ቤተ ክርስቲያን፣ የጀርመንና የኦሮሞ የሉተራን ቤተክርስቲያን ተከታዮችን ቁርኝት ማስተዋሉ በኋላ ለምንመጣበት ዋናው ጉዳያችን ይጠቅማል።
ጀርመን ምሥራቅ አፍሪካን የራሷ ለማድረግ ዓይኗን በጣለችበት ወቅት ሃይማኖት የለሽ (ፓጋን) ወይም ባህላዊ ዕምነት ይከተሉ የነበሩትን የደቡብ ኢትዮጵያ ወገኖቻችንን የሉተራን ሃይማኖት ተከታይ ለማድረግና ከሕዝቡ ጋር በሃይማኖት ሽፋን ወዳጅነት ፈጥሮ አስፈላጊውን ቅድመ ቅኝ ግዛት ዝግጅት ለማጠናከር የቄስ ካባ አልብሳ የላከቺው ዮሐን ሉድዊግ ክራፍ የተባለ የመረጃ መኮንኗን ንው።
ዮሐን ብሩህ አዕምሮ፣ ተመራማሪ፣ የሃይማኖትና የሥነ – ቋንቋ ከፍተኛ ችሎታ ያለው ግለስብ ሲሆን፣ እ.አ.አ. ከ1837 እስከ 1842 ኢትዮጵያ ውስጥ በቆየበት ወቅት አማርኛ፣ ኦሮሞኛና ግዕዝ አጥንቶ የመጀመሪያውን የዮሐንስና የማቴዎስ ወንጌል በኦሮሞኛ ተርጉሞ ለንባብ አብቅቷል። ሆኖም ጥንታዊ የሆነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት በብዙ መላዕክቶች በማመን ላይ ያተኩራል እያለ ይተች ስለነበረና የሉተራን ሃይማኖትንም ለማስፋፋት ያለመው ግብ እንደተጠበቀው ስላልተሳካለት ወይም ለሌላ ተልዕኮ ፊቱን ወደ ኬንያና ታንዛኒያ አዙሯል። ቢሆንም ዮሐን የኦሮሞ ተወላጆችን ሞምባሳ ላይ እየተገናኘ የሃይማኖት ስብከቱንና የተደበቀ የስለላ ተግባሩን ከማከናዎን አልተቆጠበም። በሀገሩ በጀርመንና በእንግሊዝ ሀገር ቆይታ ካደረገ በኋላም እ.አ.አ. ብ1867/68 አፄ ቴዎድሮስን ሊዎጋ ከመጣው በጄኔራል ሮበርት ናፒዬር ከሚመራው የታላቋ ብሪታኒያ ጦር ጋር አብሮ በመዝመት አፄ ቴዎድሮስ መስዋዕት ከሆኑባት መቅደላ ድረስ ተጉዟል።
ኬንያ/ናይሮቢ የሚገኘው የጀርመን ኤምባሲ ሕንፃ በእርሱ ስም Ludwig Krapf House ተብሎ ይጠራል። አዎ! ለእኛ መርዝ ተከለ፤ ለእርሱ ግን በመታሰቢያንት ሕንፃ ተገነባለት።
ዮሐን ክራፍ ለሀገሩ መንግሥት ባደረገው የመረጃ ጥናቶች ውስጥ የሚከተሉት በአንኳርነት የሚጠቀሱ ናቸው፦
  1. የምሥራቅ አፍሪካንና የመካከለኛው ምሥራቅን ከዚያ በመነሳት መቆጣጠር ይቻላል፤
  2. የእስልምና ሃይማኖት፣ በአረብ ሀገሮችና በአፍሪካ የሚያደርገውን መስፋፋት መግታት ይቻላል፤
  3. የምሥራቅ አፍሪካ ነዋሪዎችን በክርስትና ሃይማኖት በማጥመቅ የጀርመን ወዳጅ አድርጎ የጀርመንን የበላይነት ማስፈን ይቻላል፤
  4. ከላይ የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ለማሳካት በየቦታው ተራርቆ የሠፈረውን የኦሮሞ ብሔረሰብ በካርታ ከልሎ ከኢትዮጵያ ነጥሎ ማውጣት የሚል ግምገማ ነው ያቀረብው።
ግንጠላውንም ለማካሄድ ብሔረሰቡን ከታሪክ ለማራራቅና ከሌሎቹ በሔረሰቦች ጋር ቅራኔ እንዲፈጥር ለማድረግ ጋላ የሚለው ቃል በሐበሾች ለአረቦች የተሰጠና ትርጉሙም ስደተኛ ማለት ነው ሲል ሰብኳል። የጊዜው አክራሪ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ጋላ የሚለው ስያሜ የኦሮሞን ሕዝብ ለማንቋሸሽ በአማሮች የተሰጠ ነው ቢሉም፣ ቃሉ ስደብ እንዳልሆነ ከዚህ መረዳት ይቻላል። የኦሮሞን ታሪክ ያጠኑ ተመራማሪዎች ጋላ ማለት በሱማልኛ እስላም ወይም ክርስቲያን ያልሆነ ማለት ነው። አሁንም ከዚሁ የሱማልኛ ቋንቋ ሳንዎጣ በሱማልኛ “ጋል” ማለት ግመል ማለት ሲሆን፣ ጋላ የሚለው ሰምም ከዚሁ ጋል ከሚለው  ስም የወጣና “ባለግመሎቹ” እንደማለት ነው የሚሉም አሉ። ከኦሮሞኛ ቋንቋ “ገላ” ከሚለው ግሥ የወጣና ትርጉሙም ቤታችን ሄድን ወይም ገባን ማለት ነው የሚሉም ሲኖሩ፣ በየትም ቦታ በስድብነት አልተመዘገበም።
ዮሐን ባቀረብው ሃሳብ መሠረት የብሔሩ መጠሪያ ኦርማኒያ እንዲሆን በ1860 ዓ.ም. የተወሰነ ሲሆን፣ ኦሮሞ እና ኦሮሚያ የሚሉት ስሞች የመጡት ከዚሁ ነው። ትርጉሙንም ኦርማ ወይም ኦሮማ ማለት ጎበዝ ማለት ነው ሲል ተንትኗል።  በምሥራቅ ኬንያ በታችኛው ጣና ወንዝ የሚኖሩ ዘላኖች ኦርማ ይባላሉ። የኦሮሞ ነገድ ወደ ኢትዮጵያ ፈልሶ ከመግባቱ በፊት መነሻው ከዚህ ሊሆን ይችላል የሚሉም አሉ።
ከላይ ለማሳየት እንደተሞከረው ኦሮሞ፣ ኦሮሚያ፣ የኦሮሚያ ካርታና ኦሮሚያ ራሷን የቻለች ሀገር መሆን አለባት የሚሉት ጠንሳሽ በጀርመን መንግሥት ተልኮ አካባቢውን በቅኝ ግዛት እንዴት መያዝ እንደሚቻል ያጠናው የጀርመኑ ሰላይ ዮሐን ሉድዊግ ክራፍ ነው።
ጀርመኖች የብሔረሰብ መጠሪያ ስም ሰጡ፤ የኦሮሚያ ግዛት ብለው ካርታ ሠሩ፤ በመጨረሻም ኦሮሚያ መገንጠል አለባት አሉ። የጀርመን ሉተራን ቤተክርስቲያን ብዙ ልጆችን (የአሁኑ አዛውንቶችን) በሀገር ውስጥም ሆነ ሀገራቸው ወስደው በማስተማርና በግንጠላ መርዝ በመበከል ኦሮሚያ በኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ሥር ነች የሚል አስተሳሰብ በአንዳንድ የኦሮሚያ ተወላጆች ጭንቅላት ውስጥ አስርፀዋል። ለዚህ አስተሳሰብ የተንበረከኩ ጥቂት የኦሮሞ ልጆች ከአክራሪ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ጋር በመሆን ከ50 ዓመታት ላላነሰ ጊዜ ተንቀሳቅሰው እነርሱ በአሜሪካና በአውሮፓ በድሎት እየኖሩ ብዙ የኢትዮጵያ ልጆችን እርስ በእርስ አባልተው ከፍተኛ የሕይዎት መስዋዕትነትና የንብረት ውድመት እንዲደርስ አድርገዋል። ለዚህ እኩይ ተግባራቸውም እንደ ሀሰል ብላት ያሉና የጀርመን የሐሰት ቄሶች በሃይማኖት ስም የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የሎጂስቲክ ድጋፍ ያደርጉላቸዋል።
ኢትዮጵያ ከምትታወቅባቸው አንዱ በቅኝ አለመገዛቷና የራሷ የሆኑ ቋንቋዎችን መጻፍ የሚያስችል ባለፊደል ሀገር መሆኗ ነው። ማንኛውም የሀገሪቱ ብሔረሰብ ቋንቋ በሀገሪቱ በነፃነት ይነገራል፤ በግዕዝ ፊደልም ሊጻፍ ይችላል። በራስ ከመኩራት ይልቅ በባርነት ወይም በቅኝ ግዛት ከተያዙ ሀገሮች ደረጃ ዝቅ ማለትን የመረጡ ለኦሮሞ ሕዝብ ቆመንለታል ያሉ ፈረንጅ አምላኪዎች የኢትዮጵያ ጠላት ከሆነው ወያኔ ጋር በመሆን ክ1991 ጀምሮ ኦሮሞኛ የሚጻፍው በላቲን ፊደል ሆኗል።
ቋንቋ እንደ ዛፍ የተተከለ፣ ካልቆረጡት የማይነቃነቅ ደረቅ አይደለም። ያድጋል፣ ይዳብራል፣ የሰው ልጅ መጠቀሚያ እስከሆነ ድረስ ፈሩን ሳይለቅ ይሻሻላል። ያሉት የግዕዝ ፊደላት ኦሮሞኛን ሙሉ በሙሉ ለመጻፍም ሆነ ለማናበብ አይበቁም እንኳን ቢባል፣ በግዕዝ ፊደላት ላይ ፊደሎችንና አናባቢዎችን ጨምሮ መጠቅም ሲቻል፣ የላቲን ፊደል ነው ለአፋን ኦሮሞ የሚመቸው በሚል ኢትዮጵያዊነትን ለማፍረስ ሰንካላ ምክንያት በማቅረብ በፈረንጆች ቅኝ ሳይገዙ በግድ ጌቶቻችን ናችሁ በማለት እጅ መስጠት ታምኖበታል። በግዕዝ “ጨ” እና “ሸ”ን የመሳሰሉ ፊደላት አልነበሩም። የአማርኛ ቋንቋን ሙሉዕ ለማድረግ ሲባል ግን ተፈጥረው እንጠቀምባቸዋለን።
በቅርቡ ቪዥን ኢትዮጵያ በተባለው ስብሰባ ላይ ስለ ቁቤ ተነስቶ ፕ/ር እዝቅኤል ጋቢሣ ኦሮሚኛን በላቲን ፊደል መጠቀም የተጀመረው ከ1840ዎቹ ጀምሮ ነው ብለዋል። ይህ መረጃ የሚያመለክተው የኦሮሞ ሊሂቃን እንደሚሉት በእነርሱ ጥናት ተደርጎበትና የኦሮሞ ሕዝብ ተዎያይቶ አምኖበት የተቀበለው ሣይሆን ቁቤ ኦሮሞ፣ ኦሮሚያ የሚለውን ባወጣው በጀርመናዊው ዮሐን ክራፍ የተሰጠ መሆኑን ነው። ከትልቅነት ትንሺነትን መምረጥ ይሉታል ይህ ነው።
ወያኔ የአማራን መሬት ከጎንደርና ወሎ ወስዶ ሕዝቡን በግዴታ ትግሬ ነህ ብሎታል። የሕዝብ ቆጠራ ብሎ በሠራው ማጭበርበር የአማራውን ቁጥር ቀንሶ ለማቅረብ ያደረገው ሙከራ ስለተነቃበት የሕዝብ ቆጠራው ተቀባይነት አጥቷል።  በመሆኑም በወያኔ ዘመን በኢትዮጵያ ትክክለኛ ይሕዝብ ቆጠራ ስላልተካሄደ የኢትዮጵያ በሔረሰቦች፣ ባጠቃላይም የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህን ያህል ነው ብሎ መናገር አይቻልም። አንድን ቋንቋ መናገር የዚያን ብሔረሰብ አባላትነትን አያቀዳጅም። (ዝርዝሩን በኋላ እንመጣበታለን።)
ኦሮሚያ ውስጥ ሳይወዱ በግድ ኦሮሞ ናችሁ ተብለው የተፈረጁ ኦሮምኛ የሚናገሩ የሌላ ብሔረሰብ አባላት እንደሚገኙ ሊሠመርበት ይገባል። ስለሆነም ኢትዮጵያ ውስጥ የኦሮሞ ብሔረሰብ ቁጥር ይህን ያህል ነው፣ ከሁሉም ብሔረሰብ ይበልጣል ብሎ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም። የአፋን ኦሮሞ ተናጋሪዎች ቁጥር ግን ከፍተኛ ስለሆነ አፋን ኦሮሞ ሁለተኛ በሔራዊ ቋንቋ እንዲሆንና ከሁለተኛ ደረጃ ጀምሮ ካሪኩለም ውስጥ ገብቶ እንደ አማራጭ ትምህርት እንዲሰጥበት መጠየቅና መታገል የኦሮሞ ሊሂቃን ተግባር መሆን ሲገባው፣ ዮሐን ክራፍ ያዘጋጀውን የኦሮሚያ ካርታ ይዘው አትላንታና ሚኒሶታ በመሯሯጥ ጊዜያቸውን ሲያባክኑ ይታያሉ።
ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛትነት ያልተያዘች ለረጅም ዘመን ነፃነቷንና ሉዐላዊነቷን ባሏት በርካታ ብሔረሰቦችና ማኅበረሰቦች አስጠብቃ የኖረችና የምትኖር ሀገር ናት። “History is more than the path left by the past, it influences the present and can shape the future” Malcolm X.
የኢትዮጵያን የረጅም ዘመን ታሪክ ለማጥላላት የሚሞክሩ ከሃዲዎች እንድሚሉት ከሰሜን በመጡ መኳንንት የተመሠረተች ሳትሆን ሕዝቦቿ ልዩነት እንኳን ቢኖራቸውም አንድነታቸውን የሚፈታተን ሁኔታ ሲፈጠር አንድ ላይ በመቆም ኢትዮጵያ የምትባለውን ሀገር በደማቸው ዋጅተው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው አቆይተዋታል። በየትኛውም ሀገር በፊውዳል ሥርዓት የመሳፍንት ፍትጊያ እንደነበረ ሁሉ፣ በኢትዮጵያም የተከሰተ ሁኔታ ነው። ይህን ግን እንደ ኢትዮጵያ የታሪክ መሠረት አድርጎ የጥንታዊት ኢትዮጵያን የረጅም ዘመን ሕልውና ለመናድ የሚጠቀሙብት የእናት ጡት ነካሾች ብቻ ናቸው። የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ብዙ ወጣውረዶችን ያዬች፣ በተለያዩ ጦርነቶች ልጆቿ የተሰውባት፣ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ አንዳንድ ጎሣዎቿ የጠፉባት ሀገር ናት።
በ1517 አህመድ ኢብን ኢብራሂም (በተለምዶ ግራኝ መሐመድ) የወረራ ጦርነት የጀመረው በምዕራብ ሐረርጌ ሲሆን፣ ዘንተራ ሰሜን ጎንደር ጣና ሃይቅ አካባቢ በአፄ ገላውዲዎስ ጦር እስከተገደለበት 1535 ዓ.ም. ድረስ ለ19 ዓመታት ከፍተኛ ጥፋት ፈጽሟል።
ግራኝ አህመድን በመከተል ከ1530 ዓ.ም. ጀምሮ በቦረና በኩል ነው የመጡት የሚባሉ የኦሮሞ ወራሪዎች (የኦሮሞ ልሂቃን ፍልሰት ይሉታል) እግረመንገዳችወን ያገኟቸውን የሌላ ብሔረሰብ አባላትን በመደፍጠጥ እስከ ትግራይ ዘልቀዋል። በዚህ ሂደት የጋፋት ነገድ ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል፤ ወይም በኦሮሞው የሞጋሣ ሥርዐት ሳይወዱ ተገድደው ኦሮሞ ሆኗል። የሚያ ነገድ ተወላጆችም ተመናምነው በዝዋይ ሐይቅ ደሴት ላይ እንዲወሰኑ እንደተደረጉ ቢነገርም መኖራቸው የተረጋገጠ አይደለም። ሃዲያዎችና ከምባታዎች ከግዛታቸው ከባሌና ከአርሲ ተፈናቅለው በደቡብ ምዕራብ ሸዋ በስደተኝነት አነስተኛ ቦታ ይዘው እንዲኖሩ ተደርገዋል። አርጎባዎች፣ ቀቤናዎች፣ ወርጅዎች፣ አላባዎች፣ ሲዳማዎች፣ የኦሮሞ ወረራ ሰለባ ሆነው ሳይወዱ በግድ ኦሮሞ እንዲሆኑ ወይም እንዲሰደዱ ሆነዋል። የዳውሮና የገሙ ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቅለው ግዛታቸው በኦሮሞዎች ተወስዶባቸዋል።
በዘመናችን ኦሮሚያ ተብሎ የተከለለው ቦታ የተለያዩ የብሔር ብሔረሰቦች ጥንቅር ውጤት ነው። የኦሮሞ ወራሪዎች የሌሎች ብሔረሰቦችን ግዛት ሲይዙ ነዋሪዎችን ኦሮሞ ከማድረግ ጀምሮ የቦታዎችን መጠሪያ ስም ቀይረዋል። ፈጠጋር = አርሲ፣ ግራሪያ = ሰላሌ.፣ ገንዝ = ጅባትና ሜጫ፣ ኢሊባቡር = እናሪያ፣ ሌቃ (ምሥራቅ ወለጋ) = ዳሞት፣ ቢዛሞ = ቄለም (ምዕራብ ወለጋ) ወ.ዘ.ተ.
የቅኝ ገዥ ሀገራት ባህሪን ስናይ አንዱን ሉዐላዊ ሀገር ከሌላ ቦታ መጥቶ በጉልበት ነጥቆ ማስተዳደርንና የተፈጥሮ ሀብትን መዝረፍን ያመለክታል። ቅኝ ገዥዎች ለመግዛት እንዲያመቻቸው የራሳቸውን ቋንቋ፣ ሀይማኖት፣ ባህልና አኗኗር በሚገዙዋቸው ሀገሮች ላይ በግድም ሆነ በውድ ተጭነው ያሰፍናሉ። ኦሮሚያ ተብሎ በሚጠራው ክልል የነበሩ ብሔረሰቦች ነገዳቸው ጠፍቶ ባህላቸው ተረስቶ ማንነታቸው ተቀይሮ እንዲኖሩ ተደርገዋል። የገዳ ሥርዓትን በግድ እንዲቀበሉ ተደርገዋል። በመሀሉም ባህሌን፣ ወጌን፣ በማለታቸው የደረሰባቸው ጉዳት ይህ ነው ኣይባልም። ከዚህ የበለጠ ከቅኝ ገዥነትና ተገዥነት በምሳሌነት የሚጠቀስ አይኖርም። ከላይ በዝርዝር ለማሳየት እንደተሞከረውም በዓለም ላይ እራሷን የቻለች ኦሮሚያ የተባለች ሀገር አትታወቅም። ኦሮሚያም ኦሮሞዎች በታሪክ አጋጣሚ የሚኖሩባት ሀገር ናት እንጅ የኦሮሞዎች ብቻ አይደለችም።
የ16ኛውንና የ17ኛውን ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያን ታሪክ ስንመለከት የኦሮሞን ብሔረሰብ መስፋፋት እናጤናለን። በአሁኑ ጊዜ የኦሮሞ ብሔረሰብ የሚገኝበት መሬት ወይም ኦሮሚያ ተብሎ የሚጠራው የኩሽ ቤተሰብ ብቻ ሳይሆን፣ የሴማውያንም እንደነበረ ነው በታሪክ የሚታወቀው። የዎራሪዎቹ ዘመናት የሚታወቁት በተነሱት የኦሮሞ የጦር አለቆች ወይም መኳንንቶች መጠሪያ ነው።፡ የዘመን አቆጣጠሮቹ እንድ አውሮፓውያን አቆጣጠር ናቸው። መልባ 1522 – 1530፣ ሙደና 1530 – 1538፣ ኪሎሌ 1538 – 1546፣ ቢፎሌ 1546 – 1554፣ መሰሌ 1554 – 1562።
የኦሮሞ መስፋፋት እስከ ራያ አዘቦ ድረስ የዘለቀበት ሁኔታ ነበረ። የየጁ ኦሮሞ ባላባቶች የአማራውን፣ የትግሬውንና የአገውን ግዛት ተቆጣጥረዋል። ከአፄ ቴዎድሮስ በፊት የየጁ ኦሮሞ ዳይናስቲ አባ ሴሩ ጉዋንጉል፣ ቀዳማዊ ራስ አሊ፣ ራስ አሊጋዝ፣ ራስ ጉግሣ መርሶ፣ ራስ ይማም፣ ራስ ማርየ፣ ራስ ዶሪ፣ ዳግማዊ ራስ አሊ፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ገዥዎች ነበሩ። በአንድ ወቅት የጎንደር ቤተመንግሥት ቋንቋ ኦሮሞኛ ነበር። የአፄ ቴዎድሮስ ባለቤት ተዋች አሊ፣ የአፄ ምኒልክ ባለቤት እቴጌ ጣይቱ ብጡል፣ የራስ መንገሻ ባለቤት ከፋይ ወሌ፣ የንግሥት ዘውዲቱ ባለቤት ባለቤት ራስ ጉግሣ ወሌ፣ የትግራይና የባህረነጋሽ ገዥ የነበሩት ራስ ውቤ የየጁው የራስ ጉግሣ መርሶ ዘር ናቸው።
በምኒልክ ዘመነ መንግሥት የሰው ልጅ የደረሰበት የዕድገት ደረጃ ፊውዳሊዝም ነው። በየትኛውም ሀገር የተስፋፊነት ጦርነቶች ተካሂደዋል። የሚኒልክ አካሄድ የሚለይበት ግን የኢትዮጵያን ግዛት አንድ ላይ አጠቃሎ አሀዳዊ መንግሥት መሥርቶ በዘመናዊ ሥርዐት ማስተዳደር ነበር።፡ በጊዜው ዲሞክራሲ ምርጫ የሚባል የሚታሰብ አልነበረም። ባለጡንቻ እየተዋጋ፣ እያስገበረ፣ የጎሣ መሪዎችን እየጣለ የራሱን አስተዳደር ይመሠርታል። በምኒልከም የተደረገው ኦሮሞዎች በጡንቻ እየደፈጠጡ የመጡትን ሕዝብ ማስመለስና አንድ አድርጎ ማስተዳደር ነው። በመሀሉ መገዳደል፣ መማረክ፣ መታሠር የሚጠበቅ ነው። በወያኔ የተጨመረው የጡት ቆረጣ የቆርጦ ቀጥል ታሪክ ነው። ጡት ቆረጣና የወንድን ብልት መስለብ የሃይማኖት የለሽ (የባህላዊ ዕምነት ተከታዮች) ባህል ነው። የወንድ ብልት ተቆርጦ ልጃገረድ ለማግባት እንደግዳይ የሚቀርብበት ቦታ የት እንደሆነ ሁሉም የሚያውቀው ነው። ሚኒሊክ ሀገር በመክዳት ለጣሊያን አድረው የኢትዮጵያ አርበኞችን የወጉ ትግሬዎችን ግራ እግርና ቀኝ እጅ (የተንበረከከበትን ግራ እግርና ምላጭ የሳበበትን ቀኝ እጅ) እንዲቆረጥ ማድረጋቸው በፎቶ የተደገፈ ማስረጃ የሚቀርብበት ንው። የወያኔ መንግሥት የአያቶቹን አሳፋሪ ተግባር ስለሚያውቅ ለተቆረጠው እጅና እግር ሀውልት ልትከል ሳይል የአማራና የኦሮሞን ብሔረሰቦች ለማለያየት በተቆረጠ እጅ ላይ ጡት አስቀምጦ በአርሲ ዞን ሂጦሳ ወረዳ በኦሮሞና በአማራ ሕዝብ ላይ ሰቆቃ በፈፀሙ የኦፒዴኦ መሪዎች በነጁነዲን ሳዶ አማካኝነት የአኖሌን ሀውልት ተከለ። የዋሆችም ተደሰቱ፤ ጣታቸውንም በሌላ ብሔረሰብ ላይ ላይ ቀሰሩ። ወያኔም እንደባለውለታ ተቆጥሮ የኦሮሚያን መሬት ለአረቦችና ሕንዶች ሲቸበችብ ዝም ተባለ።
ምኒልክ ወደ ደቡብ በዘመቱበት ወቅት የአንድ ብሔር ወታደሮችን ብቻ ይዘው አልዘመቱም። ከጦር አዛዥ እስከ ተራ ተዋጊነት የሁሉም ብሔረሰቦች ተሳታፊነት አለበት። የጅማው አባ ጅፋር 30 ሺህ ጦር ይዘው እንደዘመቱ፣ ራስ ጎበና ዳጨና ባልቻ … ወ.ዘ.ተ. የጦር አዝማቾች እንደሆኑ ነው የሚታወቀው። የነፍጠኛ አስተዳደር አሰፈኑ ለሚባለው ነፍጥ መሣሪያ፣ ነፍጠኛ መሣሪያ ለታጠቀ የሚሰጥ ስያሜ ነው። ነፍጠኛ የሚለው ቃል ጎሣን ወይም ብሔርን አያመለክትም፤ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የትግሬ፣ የጋሞ፣ የወላይታ፣ የአፋር ወዘተ ነፍጠኛ አለ። በ1938 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ዘመናዊ የመከላካያ ኃይል እስከሚመሠረትበት ጊዜ ድረስ መሣሪያ ታጥቆ ዳር ድንበር የሚጠብቀው ሁሉ ነፍጠኛ ነበር የሚባለው።
የተለያየ ስም የተሰጠው የአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት የፈጠረው አስገባሪ፣ ጢሰኝንት ወዘተ. ባጠቃላይ ፊውዳሊዝም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ የካቲት 25 ቀን 1967 ዓ.ም. የወጣው የመሬት ላራሹ አዋጅ ለመጨረሻ ጊዜ ያንኮታኮተው መሆኑ እየታወቀ ከሌላ ባላጋራ ወይም ወያኔ ጋር ከመፋለም ይልቅ ስለፊውዳሊዝም ማላዘኑ ጥቅሙ ምን እንደሆነ አይታወቅም።
Inferiority complex ወይም የበታችነት ስሜት መጠናዎት በራስ ካለመተማመን የሚመጣ የአዕምሮ መታዎክ ነው። ሕመሙ ልጅ አዋቂ፣ ወንድ፣ ሴት፣ የተማረ፣ ያልተማረ ሳይለይ በየትኛውም ሰው ላይ ይከሰታል። የህክምና ባለሙያ ሳያማክሩ በራስ ለመወጣት የሚደረግ ትንቅንቅ ለሌሎች የጥላቻና የአውሬነትን (aggressive) ባሕሪን የማሳየት ሁኔታ ይፈጥራል።
በውጭ የሚኖሩ የተማሩም ሆኑ ያልተማሩ አንዳንድ የኦሮሞ የፖለቲካ አክቲቪስቶች ባሕሪ በዚህ ይገለጣል። (“I am Oromo first” የሚለው የጃዋር መሐመድ አዲስ መፈክር ከዚሁ የመነጨ ነው። አንገቷ ላይ የዋርካ ምስል ተነቅሳና የሱን መፈክር ከሥሩ አስጽፋ አንድነትን የሚደግፉ ኢትዮጵያወያንን ስትዘልፍ የምትውለውን ጀርምን የምትገኘው አደገኛ ቦዘኔ ሁኔታ የህመሙን ከፍተኛ ደረጃነት ያሳያል።)
በቅርቡ ለንደን ላይ በተደረገው የኦሮሞ የሕግ ባለሙያዎች ስብሰባ ላይ በጥቂት ግለሰቦች የተንፀባረቀውም ይህ ባሕሪ ነው። አማራውን ከሌላው ብሔረሰብ ከሚገባው በላይ አግዝፍው በማየት የራሳችውን ብሔረሰብ በማሳነስ ርቀው በመሄድ ከፊታችን ልጆቻችንን በመፍጀት ላይ ያለውን የጭራቆች መንግሥት (ወያኔን) በጋራ ተባብሮ ከመጣል ይልቅ “የእኛ ዓላማ ኢትዮጵያን አፈራርሶ ኦሮሚያን መገንጠል ነው” ይላሉ። ኢትዮጵያን በማግሥቱ ሄደው እንደ ቦረና ሣር ቤት እንደሚያፈራርሷት ሁሉ። ኢትዮጵያ ማለት አማራ፤ አማራ ማለት ኢትዮጵያ እንደሆነች በአዕምሮአቸው የሠረፀው የትንሽነት ሕመም ስለሚነግራቸው ኢትዮጵያ ከ80 በላይ ብሔረሰቦች ሀገር መሆኗን ይረሱታል። በእነሱ አስተሳሰብ ሰሜኑ የትግሬና የአማራ፣ ደቡቡ የኦሮሞ ነው። ሌላው ብሔረሰብ አይነሳም። ኢትዮጵያ ባቀፈቻቸው ብሔረሰቦች አጥንትና ደም የተገነባች በማንም ህመምተኛ ጩኸት የማትነቃነቅ መሆኗን ሊረዱ የሚችሉት የህክምና ባለሙያ ዘንድ ሄደው በመታከም በራሣቸው መተማመን ሲችሉ ብቻ ንው። እነኚህ የዞረባችው ሀገር አጥፊዎች የወያኔው የኦሆዲድ አባላት “de-Amharicization” የሚል አዲስ ቃል ፈጥረው ኦሮሚያን ከአማራው ጋር ከሚያገናኙ ባህላዊ ትሥሥሮች እናለያያለን በማለት ውጥን መያዛችውን ለማዎቅ ተችሏል። በእነርሱ አባባል የአማራ ዶሮ ወጥ መብላትና የዶርዜ ጥበብ መልበስ በኦሮሞው ላይ አማራው ያሳደረው የባህል ተፅዕኖ ነው። እነርሱ በእንግሊዝ ሱፍና በአሜሪካ ጂንስ ተከሽነው ሲወጡ ግን የፈረንጆቹ የአለባበስ ባህል ተገዢ ነን አይሉም። ይህ ሁሉ ዝግጅት ኦሮሚያን ገንጥሎ ሥልጣን ላይ ለመቀመጥና አዲስ አበባን ከያዙ በኋላ የወያኔ ጄኔራሎች ዘርፈው የገነቡትን ሕንፃ እንወርሳለን በሚል ቅዠት ውስጥ ስለሚዋኙ ነው።
እጄ ጠባብ፣ ኩታና የጥበብ ቀሚስ የአማራው ብቻ ሳይሆኑ፣ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ተመራጭ የዓመት በዓል የክት ልብሶች ናቸው። ሥራው የዶርዜ ሲሆን፣ ዘሩን የማይናገር መዋቢያና መታዎቂያችን ሆኖ ሳለ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የተነሳው ወያኔ በኦሎምፒክ ሜዳ የየሀገሩ ስፖርተኞች የሀገራችውን የባህል ልብስ ለብሰው ሲያልፉ የእኛዎቹ ግን በስፖርት ቱታ እንዲሰለፉ አድርጓል። የሚሰጠውም ምክንያት የኢትዮጵያ የባህል ልብስ የአማራ የባህል ልብስ ነው የሚል ነው።
የኦሕዴድ አባላት፣ የአሁኖቹ የወያኔ ተቃዋሚ የኦሮሞ ሊሂቃን ነን ባዮች አቋም ጌቶቻቸው በአዕምሮዎቻቸው ላይ የሠሩት የአዕምሮ አጠባ (Brain wash) ውጤት ነው።
ባለፈው ጊዜ በዩናይትድ ኪንግደም ለንደን ከተማ የኦሮሞ የሕግ ባለሙያዎች ማህበር የጠራው የሁለት ቀን ጉባኤ ተካሂዷል። በስብሰባው ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ወየሳና በጸሐፊው በአቶ ሁንዴ ዱጋሣ አባባል የስብሰባው ዓላማ በኦሮሞ ድርጅቶች መካከል ያለውን ሀሳብ ለማቀራረብ ከዚያም ወደፊት ከሌሎች የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ጋር ተቀራርቦ አንድ ላይ ለመሥራት ነው። ቀጣዩም ስብሰባ በአትላንታ እንደሚካሄድ አስታውቀው ነበር። የአትላንታው ስብሰባም ተካሂዶ ነበር።ሆኖም ግን ሾልክው የሚወጡ መረጃዎች የሚያመለክቱት ቀደም ሲል የተባልውን አይደለም። የስብሰባው ዓላማ የተቀደሰ ቢሆንም ሁለት የድርጅት መሪዎች ነን በሚሉና በጃዋር መሀመድ የተሰጡ አስተያየቶች አሉታን ፈጥረዋል። በተለይ የተሰጡት አፍራሽ አስተያየቶች በታዳሚው የሞቀ ጭብጨባ መታጀብ በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ጥያቄዎችን ጭሯል። የአንዳንዶቹንም የሕይወት ታሪክ ወደኋላ መለስ ብሎ ለማየት አስገድዷል።
“ያሳደግነው ጥጃ የምንጭ ውሃ ግተን፣ ከጨሌው አግጠን፣
ያሳደግነው ጥጃ ወትተ አጠጥተን፣ ለምለም ሣር አግጠን፣

ፈርገጥ ፈርገጥ አለ እኛኑ ሊረግጠን።” ፈተነኝ ከሚለው ዜማ የተውሰደ።
የመድርክ አዝጋጁ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታይ ነኝ ባዩ የመቶ አለቃ ተሻለ አበራ በደርግ ዘመነ መንግሥት ከፖሊስ ኮሌጅ በመኮንነት ተመርቆ ወደ ቀድሞዋ ሶቪየት ሕብረት ለትምህርት ተልኳል። በጊዜው በሥራ ላይ የነበሩ ወደሶቪየት ሕብረት ለትምህርት የሚላኩ የኢሠፓ አባላትና ካድሬዎች ናቸው። ወያኔ ሥልጣን እንደያዘም በተለያዩ የሥራ መደቦች ሲያገለግል ክቆየ በኋላ እስከ ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትነት ደርሷል። አሁንም የኦሕዴድ አባል ሳይኮን እዚህ ደረጃ ላይ እንደማይደርስ ፀሐይ የሞቀው ሐቅ ነው። መቶ አለቃ ተሻለ በወያኔ ለትምሀርት ወደ እንግሊዝ ሀገር ሂድ ሲባል ሚስትና ልጁን አስቀድሞ ወደ ዑጋንዳ በመላክ ለተሻለ ኑሮ በዚያው ቀርቷል። ባለወለታ ወይም ትግሬ ላልሆነ የዚህ ዓይነት ዕድል የማይታሰብ ነው። እንግሊዝ ሀገር እንደሄደም ዘመድም ሆነ ወዳጅ ስላልነበረው የቀረበው ወያኔን በመቃወም የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት (Downing Street) ደጃፍ ላይ የነበሩ ኢትዮጰያውያንን ነው። እነርሱም ወገናችን ነው በሚል ችግሩን ተረድተው አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ አድርገው የመኖሪያ ፈቃድ እስከሚያገኝና ጉዳዩ ፈር እስከሚይዝለት ድረስ ሲንከባከቡት ቆይተዋል። ዓመልና ጅራት ከወደኋላ እንደሚባለው ሁሉ የመቶ አለቃ ተሻለ ሀገር ከለመደና የስደተኝነት ጉዳዩ ካለቀለት በኋላ የዘር ክሩን መዝዞ ወደ ኦሮሞ ተቃዋሚዎች በመሄድ ውለታ ካደረጉለት ኢትዮጵያውያን ተደብቆ ይኖራል። ተሻለ ኢትዮጵያ ፈራርሳ  የኦሮሚያ መንግሥት ይመሠረታል ብሎ የሚያስብ ፀረ የሀገራችን አንድነትና የኢትዮጵያዊነት ጥላቻ እንዳለው በተለያዩ ሁኔታዎች አቋሙን በማንፀባረቅ ላይ ይገኛል። ውሎው ኦሮሚያንና ኦጋዴንን እንገነጥላለን ከሚሉ የኦሮሞ ተወላጆችና የሱማሌ ዜጎች ጋር ሲሆን፤ ይህንንም ለማሳካት የሰብዓዊ መብት ታጋይ ድርጅቶችንና የእንግሊዝ ባለሥልጣናትን በመቅረብ መርዙን ሲረጭ ይውላል።
ዓላማችን ኢትዮጵያን አፈራርሰን ኦሮሚያን መገንጠል ነው ያለው የወያኔ ጄኔራል ሆኖ ሲያገለግል ቆይቶ ወደ ኤርትራ በመግባት ከሌቻ ወለቡማ የተባለ ድርጅት ያቋቋመውና አሁን በዑጋንዳ የሚገኘው የጄኔራል ከማል ገልቹ ተጠሪ ሊበን ዋቆ ነው። ድርጅቱ ከፋላ በመባል የሚታወቀው የሶማሌ አቦ ተቀፅላ እንደሆነ ይነገራል። ሊበን የሚታወቀው ጥቅም ባግኝበት የሚያድር በመሆኑ ንው። በደርግ ዘመነ መንግሥት በኢ.ሕ.አ.ፓ. አባልነት ተመልምሎ ብዙ ወጣቶችን በማጋለጥ ሕይዎታቸው እንዲያልፍ አድርጓል። በአንድ ወቅትም የኦነግ አባል ነኝ ብሎ በመጠጋት በኢሓፓ ላይ ያደረገውን እኩይ ተግባር ደግሞታል። በተለያዩ ጊዜያት  የመንግሥትን ተቃዋሚዎች በማጋለጥና በማስመታት ላደረገው አስተዋፅዖ በሻምቡና በቦረና አውራጃ አስተዳዳሪነት ሊሾም በቅቷል። የደርግ መንግሥት ከወደቀም በኋላ በወያኔ እግር ሥር ሲልከሰከስ እንደነበረ የሚያውቁት ይናገራሉ።
ጉዲሣ ሙለታ (United Liberation Front) ኡልፎ መሪ የኦሮሞ ትግል ዓላማ እየፈረሰች ያለች ኢትዮጵያን መደገፍ ሳይሆን የጊዜውን አጋጣሚ ተጠቅሞ ኦሮሚያን ነፃ ማውጣት ነው ብሏል። ጉዲሣ ሙለታ ይህን ሲል ወያኔ በተባበረ ክንድ ሊወድቅ በተንገዳገደብት ወቅት ምርኩዝ እያቀበለ እንደሆነ አልተረዳውም። የፖለቲካ መሀይምነት ይሉታል ይህ ነው። ጉዲሣ ብዙም ተከታይ የሌለው፣ አትላንታ ላይ በተደረገው ስብሰባ አማራውንና የኢትዮጵያ አንድነት ደጋፊዎችን በፌስ ቡክ በመዝለፍ የምትታወቀውን የጀርመን ነዋሪ ቦዘኔ ከኋላ ኋላ እየተከተለ “አድናቂሽ ነኝ” እያለ ሲያሞካሻት መታየቱ ምን ያህል የወደቀ ሰው መሆኑን ያሳያል።
ሜንጫ በአረብኛው ሜንቻ ከተባለው የስለት መሣሪያ የተወሰደ ነው። አክራሪ እስላሞች የሌላውን ሃይማኖት ተከታዮች አንገት የሚቆርጡብት መሣሪያ ማለት ነው። በአሜሪካ   ያደረገውን እውንተኛ ዓላማውን የሚገልፀውን አክራሪ የእስልምና ሃይማኖትን ለማስፈን የተጠቀመበትን ንግግር ለማዳመጥ   የሚቅጠለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ። https://www.youtube.com/watch?v=RMLLmAMWdG8  የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን ሰብስቦ ባደረገው ንግግር ጃዋር መሐመድ እኛ ዘንድ የሌላውን አንገት በሜንጫ ነው የምንቆርጠው ሲል ታዳሚው “አላህ ወ አክበር!” ብሎ አጨብጭቦለታል። ጃዋር ከሼሪያ ሕግ ተከታይ ጂሃዲስቶችና ከአይሲስ የሚለየው በምንድን ነው? ይህ ሰው ነው እንግዲህ በውጭ በሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች የኦሮሞ ታጋይ ተብሎ የሚወሰደው።
ጃዋር OMN በሚል ያቋቋመው መገናኛ ብዙሓን ከአንዳንድ የአረብ ሀገሮች የገንዘብ ድጎማ እንደሚያገኝና በየሀገሩ የሚገኙ አንዳንድ ወጣቶችንና ቦዘኔዎች እየከፈለ እርሱ በዜና ማሰራጫው ሊል የማይችለውን እነሱ በሶሻል ሚዲያዎች እንዲሉለት እንደሚያደርግ ይነገራል። የአንዳንዶቹም እንቅስቃሴ  ማስረጃ እየተሰበሰበና ለሕግ ለማቅረብ ዝግጅት እየተደረገብት ስለሆነ ወደዝርዝሩ አልገባም።
ከጥቂቶች በስተቀር የጃዋር መሐመድ ተከታዮች እስልምና ሀይማኖት ተከታዮችና ከፋላ በመባል የሚታወቁት የሶማሌ አቦ ወይም ኦሮሞኛ ተናጋሪ የምዕራብ ሶማሊያ ነፃ አውጪ ጀሌዎች እንደሆኑ ነው የሚነገረው። ከአልሽባብ ጋርም ግንኙነት አላቸው ይባላል።
አንዳንድ ከፋፋዮች ለማራገብ እንደሚሞክሩት ሳይሆን ሰፊው የኦሮሞ ሕዝብ አያት ቅድመ አያቶቹ የተዋደቁላት ኢትዮጵያ አንድነቷ ተጠብቆ፣ ደሞክራሲ ሰፍኖ፣ ሁሉም በእኩልነት የሚኖሩባት ሀገር ነው የሚፈልጉት። የኦሮሞ ሕዝብ በኢትዮጵያ ላይ የአንበሣ ድርሻ ያለው፣ ብሔረሰቡ የሰፈረበት ቦታ ለም ቢሆንም ጫንቃው ላይ የተቀመጡ ደም መጣቾች ለጊዜው የበይ ተመልካች ቢያደርጉትም ከሌሎች ወገኖቹ ጋር አብሮ ታግሎ መብቱን ማስከበር እንጅ አኩርፎ ልገንጠል የሚል ሕዝብ አይደለም።
አማራ በቂ የሰው ኃይል፣ የተፈጥሮ ሀብት፣ አባይን የመሰለ እንኳን ኢትዮጵያን ለሱዳንና ግብፅ ሕይዎት የሚዘራ የውሃ ሀብት ያለው ነው። ሀገር በቀልም ሆኑ የውጭ ሀገር ጠላቶች የሚረባረቡበትና የሚፈሩት የፀና የኢትዮጵያ ፍቅር ስላለው ብቻ ነው። አንድነትን የሚሰብከውና የሚፈልገው ብቻውን መቆም አቅቶት ሳይሆን ከሌላው ሕዝብ ጋር ተባብሮ ጠንካራ የጋራ ሀገር ለመመሥርት ሲል ብቻ ነው።
ኢትዮጵያዊነት ተጭኖብኛል፤ ማንነቴን አይገልፀውም፤ ኢትዮጵያዊነት የሚባል መታወቂያነት ወይም identity የለም የሚለው ጃዋር ስለ ብሔረሰብ እንጅ ስለ ኢትዮጵያዊነት ተናግሮ አያውቅም። አማራ ኢትዮጵያዊነቱን ከረሳ ኦሮሞ የመገንጠል ህልሙ እውን ይሆናል በሚል እሳቤ ይመስላል ከአትላንታ ስብሰባ በኋላ የአማራውን መበደልና በአማራነት የመደራጀትን አስፈላጊነት አፅንዖት ሰጥቶ ሲናገር እየተሰማ ነው። የማንነት ጥያቄ ያነሳው አማራው ኢትዮጵያዊነትን ማቀንቀኑ እንደጎዳውና ይህንንም ትቶ እርሱና ጀሌዎቹ “I am Oromo First” እንደሚሉት አማራውም የእነርሱን መንገድ በመከተል ላይ እንደሆነ ለማሳመን ጥረት ሲያደርጉ ይስተዋላል። እነ ጃዋር ያልተረዱት አማርው ኢትዮጵያዊነቱን ብሎም በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ያለውን የፀና አቋሙን እንደያዘ የሚደርስበትን ጥቃት ለመከላከል በአጭር ጊዜ ውስጥ በመደራጀትና ተደራጅቶም በጠላቱ ላይ ጥቃት በመሠንዘር ላይ መሆኑን ነው።
ጊዜው የግሎባላይዜሽንና በአንድነት የመሰባሰብ ዘመን እንጅ የተበጣጠቁ ደሴቶችን የመፍጠሪያ ጊዜ አይደለም። እንደ ወያኔ በ21ኛው ክፍለ ዘመን በዘር ተደራጅቶ ስልጣን የመያዣም አይደለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ በፖለቲካ ከነቃ ሰንብቷል አንዱ ዘር ሌላውን ረግጦ የሚገዛበት አይደለም። ይህን ዓይንት አስተሳሰብ የሚያራምድ ካለ አሁን በሥልጣን ላይ ካለው ወያኔ የማይሻል ነው። ጊዜው እራስን በዕውቀት አሳድጎ ለገበያ መውጣትን የሚጠይቅ ነው። ኢትዮጵያ የብሔረሰቦቿ ድምር ውጤት ስለሆነች ለአንዱ እናት ለሌላው የእንጀራ እናት የምትሆንበት ጊዜ ማብቂያው እሩቅ አይደለም፤ በአንድነት ተባብረን ከታገልን።
ከ120 ዓመት በፊት ተደረገ ለተባለው ዝባዝንኬ ጆሮአችንን ሰጥተንና የወያኔን የቤት ሥራ ተቀብለን የምናላዝን ካለን እስከ ህልፈታችን ሀዘን ከመቀመጥ ውጪ የምናተርፈው የለም። በዳዮችም ሆኑ ተበዳዮች እንኳን ነፍሳቸው አጥንታቸውም ስለማይገኝ ይቅርታ ጠያቂም ሆነ ተጠያቂ አይኖሮም። ይህን ምዕራፍ ዘግተን አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመመሥረት በሕብረት እንታገል። የውደቁትን ልጆቻችንና ቤተሰቦቻችንን መስዋዕትነት ዋጋ አናሳጣው።
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሣት) ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ በወያኔ ለታፈነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዓይንና ጆሮ ሆኖ የሚያደርገው አስተዋፅዖ ከፍተኛ ነው። በመሆኑም ወያኔና ደጋፊዎቹን ጨምሮ በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፍተኛ ተደማጪነት አትርፏል። ኢሣት ከሚያቀርባቸው ዝግጅቶች ውስጥ መነጋገሪያ የሆኑ ፕሮግራሞች አልጠፉም።
ፀረ – የኢትዮጵያ አንድነት፣ ፀረ – ክርስቲያንና ፀረ – አማራ የሆነው ጃዋር መሐመድ በፖለቲካ ተንታኝነት በተደጋጋሚ በኢሣት ቀርቧል። ጃዋርን ከተደበቀበት ጉድጓድ አውጥቶ ለታዋቂነት ያበቃው ኢሣት ነው። ጃዋር በአንድ ጉዳይ ላይ በአማርኛ፣ በኦሮሞኛና በእንግሊዝኛ የተለያዩ መግለጫዎችን የሚሰጥና የሚያምታታ ግለሰብ ነው። የፖለቲካ ብስለት የሌለውን በተልይ በወያኔ ዘመን የሕወሓትን የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ እየተጋተ ያደገውን ወጣት ከነመለስ ባልተናነሰ ግራ በማጋባት አንዱን ብሔረሰብ ከሌላው ብሔረሰብ ጋር በማጋጨት ጊዜውን የሚያጠፋ ነው። በመሆኑም ይህ ፀረ – ሠላምና ፀረ – አንድነት አቋም ያለው ሰው በተደጋጋሚ በኢሣት መቅረቡ ከድርጅቱ ዋና ዓላማ ጋር የሚቃረን ስለሚሆን ቢስተካከል መልካም ነው።
ጁነዲን ሳዶ ከጋዜጠኛ ሲሣይ አጌና ጋር ቃል ምልልስ አድርጓል። በእርሱ ዘመን እሥር ቤት ስላጎራቸው የኦሮሞ ልጆች፣ ሰለገደላቸውና ወደ ስድት ሲሄዱ ሜዲቴሪያኒያን ባሕር ውስጥ ስላለቁት የኦሮሞ ተወላጆች፣ በአጠቃላይ ስለ ኢትዮጵያ ልጆች ሰቆቃ ገን ትንፍሽ አላለም። ወያኔ በሙስሊሙ የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ከሊባኖስ አልሐባሽ የተባለ  ሃይማኖት አምጥቶ ለመጫን ሲሞክር ጁነዲን ሣዶና ሚስቱ ደግሞ በሳዑዲ አረቢያ ተገዝተው የ14ኛው ክፍለዘመን የሻእሪያ ሕግንና ዋሀቢዝም የተባለውን የእስልምና እምነት ዘርፍ ኢትዮጵያ ላይ ለማስፈን ሲሯሯጡና ሚስቱ አዲስ አበባ ከሚገኘው የሳዑዲ ኤምባሲ ገንዘብ ተቀብላ ስትወጣ ስትያዝ፣ እርሱ ፈርጥጦ ከሀገር ወጥቷል። መልኩና ሥራው የእባብ የሆነው ይህ በኦሮሚያ ብዙ አማሮች ላይ ዘግናኝ ሰቆቃዎችን የፈፀመው የመለስ ዜናዊ ቀኝ እጅ የኦሕዴድ አመራር አባል የሠራቸው ወንጀሎች ማስረጃዎች ተሰብስበው ለዓለም – አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መቅረብ ሲገባው በኢሣት መስኮት ብቅ ብሎ በአፄ ሚኒሊክ ጊዜ ተፈፀመ የሚለውን የፍብረካ ወንጀል ማብራራት ነበረበት ወይ? ሁሉም ሰው ከሚያውቀው ወያኔ ሲነዛው ከኖረው የጥላቻና የሐሰት ፕሮፓጋንዳ የተለዬ ከእርሱ የተገኘ መረጃ አለ ወይ?
የቀድሞ የኦሕዴድ አባልና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት መቶ አለቃ ተሻለ አበራ በለንደን ስቱዲዮ ቃለ – መጠይቆች ሰጥቷል። ተሻለ የሚሰጣቸው መልሶች በሙሉ በጥንቃቄ የተሞሉ ኦሮሚያ የኢትዮጵያ አካል እንደሆነች የማያመልክቱ፣ የእርሱም እጅ ስላለብት በኦሕዴድ ሰልተፈፀሙት ከፍተኛ በደሎች በማድበስበስ የታለፉ ነበሩ። መቶ አለቃ ተሻለ ኢትዮጵያ እየፈራረሰች ነው ብሎ የሚያስብ ለኦሮሞ ወያኔ የተሻለ ነው ብሎ የሚያምን ፅንፈኛ፣ ፀረ – የኢትዮጵያ አንድነት አቋም ያለው ሰው እንደሆነ የሚያመለክቱ መረጃዎችን የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ ወደፊት የሚያቀርበው ይሆናል። ኢሣትን ተጠቅሞ የለንደኑና የአትላንታውን የኦሮሞ ድርጅቶችን ስብሰባ አስተዋውቆበታል።
ኢሣት የኢትዮጵያ አንድነት ኃይሎች ንብረትና መጠቀሚያ እስከሆነ ድረስ ግለሰቦችን ለቃለ – መጠይቅ ከማቅረቡ በፊት ማንነታቸውንና አቋማቸውን ከየአቅጣጫው ማጣራት ይኖርበታል። ይህ ካልተቻለ ፕሮግራሙን አርሞ ማቅረብ ወይም እንዳለ አለማቅረቡ ይመረጣል።
“የምጽፈው ሁሉ ባይተች ኖሮ፣ መጻፌን አቆም ነበር”
ቭላድሚር ኤሊች ሌኒን።
ጽሑፌ ለትችት ክፍት ነው።
shegyen@gmail.co

ህሊና ራድዮ ከአቶ ቃሲም አባ ነሻ ጋር - የምንታገለው ህዝባችን እጣ ፋንታውን በሬፈረንደም እንዲወስን ነው!

ሰበር ዜና. 19/04/2009

Bilderesultat for የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትን
በሱዳን በኩል ከአልቀዳሪፍ ለማጥቃት የተንቀሳቀሰው የህወሀት አንድ ሽምበል ኮማንድ ፓስት ተደመሰሰ::
አዘናግቶና አድብቶ ከጀርባ በመምታት የነፃነት ሐይሎችን ለመደምሰስ ከአል-ቀዳሪፍ ወደ ሁመራ እና አካባቢው የተነቃነቀው 400 የሚጠጋ የህወሀት ቅጥረኛ ሰራዊት መሽገው ከነበሩ የነፃነት ሀይሎች ጋር የገጠመውን ድንገተኛ ውርጅብኝ ለመመከት ባደረገው ማፈግፈግ ከሌላኛው የህወሀት የጦር ቀጠና በመግባቱ ሙሉ በሙሉ መደምሰሱ ከ 24 ተኛ ክ/ጦር የውስጥ አርበኞች የደርሰን መረጃ አመለከተ::

Ethiopia: External debt major set back to economy

ESAT News (December 28, 2016)
The problem of foreign debt has been a major and persistent set back for the African Economy, despite being one of the fastest growing economy in the entire globe.
According to a report by the website Answer Africa, the economic setback is mainly a result of foreign debt.
The report ranked Ethiopia the 7th, with foreign debt of 22 billion dollars with the first being South africa with an estimated debt of 143 billion dollars.
The report said in the case of Ethiopia, public enterprises have continued to borrow heavily to fund their investment. The financing needs by the public enterprises increased to 7.4 percent of the GDP.
The report revealed the public and publicly guaranteed debt reached n estimated 50 per cent of the GDP.

ESAT Gabaasa Walgahii Sochii Biyyoolessaa Ethiyophiyaa Siwiidiinitti Gag...

የአሜሪካን መንግስት ልኡክ የኢትዮጵያ መንግስት ላይ ከተቃውሞው ጋር በተያያዘ የታሰሩ እስረኞችን እንዲፈታ ማስገደዱ ታወቀ።

የአሜሪካን መንግስት ልኡክ የኢትዮጵያ መንግስት ላይ ከተቃውሞው ጋር በተያያዘ የታሰሩ እስረኞችን እንዲፈታ ማስገደዱታወቀ።
 በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ የሄደው የኦባማ አስተዳደር ሉእክ ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ውይይት ካደረገ በሆላተከትሎ እሰረኞቹ እንዲፈቱ አድርገዋል። 
 ወደ 20 በላይ የሚጠጉ ዜጎች በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ካለው አመፅ ጋር ተያይዞ የታሰሩ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 9የሚጠጉ እስረኞ ባለፈው ሳምንት መለቀቃቸው የታወቀ ሲሆን ይህንንም በኢትዮጵያ መንግስት ቴሌቪዥን “አይደገመንምየሚል ቲሸርት ለብሰው የሚያሳይ ዘገባ መስራቱ ይታወሳል። 
በአሜሪካን የተባበሩት መንግስት አምባሳደር ሰማንታ ፓወር የእስረኞችን መፈታት ተከትሎ መልካም ጅምር ሲሉገልፀውታል። 
 የአባይ ሚዲያ ዘጋቢ እንዳረጋገጠው የአሜሪካን ልኡክ ጠንከር ያለ ግፊት ማድረጋቸውን ተከትሎ ጉዳዩ በአዲሱ የአሜሪካንምክርቤት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ እርዳታና ማእቀብ መጣልን የሚጨምር ውይይት ሊደረግ እንደሚችል አክለውአስጠንቅቀዋል።
 ይህ በንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ከእስር የአይደገመንም ቲሸርት ለብሰው ከተለቀቁ ዜጎች መካከልባደረገው ቃለምልልስ ይህ በግዳጅ እንዲለብሱ የተደረገው “አይደገመንም” ቲሸርት እስረኞችን እንደማይገልፅና እንደማይወክልትግሉን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በቃለምልልሱ አረጋግጠዋል።

Ethiopia: Prosecutors file terrorism charges against Col. Demeke et al

ESAT News (December 28, 2016)

The 19th bench of the federal high court in Addis Ababa on Tuesday presided over the case of Colonel Demeke Zewdu and et al, who are leaders and members of a committee that spearheads the demands of the people of Wolkait, Tsegede and Telemt.
The defendants lead the demand by the people of north Gondar to reclaim their land that was illegally incorporated into Tigray region when the Tigrayan-led regime took power 25 years ago.
The prosecutor accused the defendants of taking missions from Patriotic Ginbot 7 to destabilize the country. They were also accused of killing and abduction of local officials in Gondar and Tigray.
Colonel Demeke Zewdu was accused of killing 11 regime security forces and injuring 7 police officers.

Wednesday, December 28, 2016

የህወሓት ባለስልጣናት ኮማንድ ፕስት አፍኖ ያሰራቸውን ንፁሃን ዜጎች በቅርቡ የተወሰኑትን እጅግ በወረደና በዘቀጠ የስነልቦና ጫና መፍጠሪያ “አይደገምም” የሚል ቲሸርት በማልበስ ፈተሁ ባለበት ማግስት በመላ ኢትዩጲያ አዲስ ዙር እስርና ግድያ እያካሄደ ይገኛል ።

imageimageየህወሓት ባለስልጣናት ኮማንድ ፕስት አፍኖ ያሰራቸውን ንፁሃን ዜጎች በቅርቡ የተወሰኑትን እጅግ በወረደና በዘቀጠ የስነልቦና ጫና መፍጠሪያ “አይደገምም” የሚል ቲሸርት በማልበስ ፈተሁ ባለበት ማግስት በመላ ኢትዩጲያ አዲስ ዙር እስርና ግድያ እያካሄደ ይገኛል ።
• በበህርዳር ከተማ የህወሓት-ብአዴን በሚጠራቸው አስገዳጂ የይስሙላ ስብሰባወች ላይ ጥሬ ሃቆችን ሲናገሩ የነበሩ ሰወች በድብቅ እየተገደሉ እየተገኙ ነው ።
* ከሳምንት በፊት ነዋሪነቱ ባህርዳር ቀበሌ 02 የሆነ ወጣት ተገድሎ በቀበሌ 04 ትልቁ መስጊድ አካባቢ ተጥሎ ተገኝቷል ።
* ከትናንት በስቲያ ነዋሪነቱ ባህርዳር በቀበሌ 14 የሆነ የመንግስት ሰራተኛ ተገሎ ጣና ሃይቅ ውስጥ ተጥሎ ተገኝቷል ። እነዚህ ሁሉ ስለእውነት ፤በህዝብ ላይ ስለሚደርስው ግፍ ፊት ለፊት መናገራቸው ለህወሓት እረጂምና ስውር እጆች ሰለባ ሁነዋል።
* ዛሬም ታኅሳስ 19 /2009 ዓ.ም የታላቁ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል በሚከበርበት በባህርዳር አባይ ማዶ ገብርኤልና ጎርደማ ገብርኤል ቤተክርስቲያናት ላይ የተሰባሰቡ ንፁሃን ወጣቶች በኮማንድ ፕስቱ እንደተያዙ ታውቋል ። በግፍ የታሰሩት ወጣቶች በእምነታቸው መሰረት አመታዊ በዓሉን ተሰባስበው በማክበር ላይ እንዳሉ ነው ። እጅግ ብዙ ወጣቶች በየቀበሌው በሚገኙ ኩሊወች ጠቋሚነት ታስረዋል ፥እየታሰሩም ይገኛል ።
እስካሁንም ያሉበት ሁኔታ አድራሻቸው የማይታወቅ ብዙ ወጣቶች ይገኛሉ ።
•በየቀበሌው ማጎሪያ ጣቢያወች የታጎሩ ንፁሀን ወንድሞቻችን ወደ ብርሸለቆ ወታደራዊ ካምፕና ማሰቃያ ስፍራ ሊወሰዱ እንደሆነ ልጆቻቸውን ሊጠይቁ የሄዱ እናቶች ይናገራሉ።

ናትናኤል መኮንን

ሀገርን የማዳን የመጨረሻ ጥሪ! — ምሕረት ዘገዬ (ከአዲስ አበባ)

ምሕረት ዘገዬ (ከአዲስ አበባ) ብዙ የምለው የለም፡፡ ከዚህ በታች ያለው በየድረገፆች ተለጥፎ የሚገኘው የሕወሓት አስገዳጅ ደብዳቤ በግልጽ ከሚናገረው የተለዬ እምብዝም የተለዬ ነገር መናገር አይቻልም፡፡ ደብዳቤው በራሱ ከበቂ በላይ የሆነ የሀገር ዘረፋ መግለጫ ነው፡TPLF letter to ANDM፡ ሀገር በደብዳቤ እየተዘረፈች ማለቋ ነው፡፡ በህግ ሽፋን የሚደረግ የለዬለት ሀገርን ራቁት የማስቀረት ዘረፋ እየተካሄደ ነው! ባንክን መዝረፍ፣ ግምጃ ቤትን መዝረፍ፣ ቋሚና ተንቀሳቃሽ የሀገርና የሕዝብ ንብረትን መዝረፍ፣ መሬትን መዝረፍ… ዜጎችን ማሰር… ማሰቃየት… መግደል… ደብዛ ማጥፋት… ማስራብ… ማጋዝ… ማሳደድና ማሰደድ… መቼም በማይረካ የዘረፋና የግድያ ሱስ ተጠምደው ሀገርን ማፍረስ የወያኔዎች ልዩ ባሕርይ እንደሆነ ወደዕድሜያቸው ጫፍ ደረሱ፡፡ እኛም እነሱም ስናሳዝን! የደብዳቤው ኦሪጂናል ቅጅ በደንብ የሚነበብ ቢሆንም ከፎቶው ላውጣውና በግልጽ ላስነብባችሁ፡- ጉዳዩ፡- በቋሚ ኤግዚቢሽን የሚቀመጡ ቅርሶችን አሰባስቦ መላክን ይመለከታል፡፡ የአብክመ [የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት] ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በትግራይ ክልል አዲገዛኢ በሚባል አካባቢ የአገራችንን ብሔር ብሔረሰቦች መገለጫ የሆኑ ቅርሶችን በአንድ አካባቢ አሰባስቦ ማስጎብኘት ይቻል ዘንድ አገር አቀፍ ሙዜም አስገንብቶ ፍጻሜ ላይ ማድረሱን በመግለጽ በዞናችን የህብረተሰቡን ማንነት ገላጭ የሆኑ ቅርፆችን በማሰባሰብ እስከ ታህሳስ 15/2009 ዓ.ም ድረስ ለክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እንድናስረክብ በቁጥር ባ/ቱ 322/09 በቀን 23/3/2009 ኣ.ም (ዓ.ም) በተጻፈ ደብዳቤ አሳውቆናል፡፡

Tuesday, December 27, 2016

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በዝዋይ እስር ቤት ውስጥ በጽኑ ታሞ ባቱ ሆስፒታል ገባ

የሶስት ዓመት እስራት ተፈርዶበት በዝዋይ እስር ቤት በእስር ላይ የሚገኘው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ታህሳስ18 ቀን 2009 ዓ.ም በፀና ታሞ በአንፑላንስ ተጭኖ ዝዋይ በሚገኘው ባቱ አጠቃላይ ሆስፒታል መግባቱ ታውቋል።
በተደጋጋሚ ጊዜያት ከቤተሰቦቹ እና ሕጋዊ ጠበቃው ጋር እንዳይገናኝ ሲደረግ የነበረው ጋዜጠኛ ተመስጌን ደሳለኝ የእስር ቤቱ ወታደሮች ወደ ሆስፒታል ይዘውት በሚገቡበት ወቅት በአቅራቢያው የሚገኙትን ሰዎች እንዲርቁ አድርገዋል። በዚህም ምክንያት የተመስገን የሕመም ደረጃ ምን ያህል እና በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ እንዳልተቻለ ቤተሰቦቹ ስጋታቸውን ገልፀዋል። ይህን ዜና እስካጠናከርንበት እስካሁኗ ሰዓት ድረስ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በቃሬዛ ተጭኖ ከገባበት ዝዋይ ባቱ ሆስፒታል ያልወጣ ሲሆን የሕመሙን ዓይነት ቤተሰቡ እንዲያውቁት አልተደረገም።

የአስቸኳይ ጊዜ የዉጭ ምንዛሬ ማዕቀብ አዋጅ!

ውድ ኢትዮጵያዊያን፣
ሁላችንም በሚገባ እንደምናውቀው፤
  • ሀገራችን ኢትዮጵያ በሕወሓት መራሹ ዘረኛ የግፍ አገዛዝ ሥር ሆና ዜጎች እንደ እንስሳ እየተገደሉ ባሉበት በዚህ ፈታኝ ወቅት፣ አስከፊውን ስርዓት ከስሩ ነቅለን ሕዝባችንን እና ሀገራችንን ለመታደግ ዛሬ ነገ የማይባልበት አጣዳፊ ጊዜ ላይ የደረስን በመሆኑ፤
  • ጠላት ሌት ተቀን ሥልጣኑን ለማራዘም በሽዎች እያሰረ፣ እያሰቃየና እየገደለ ባለበት ወቅት፣ ዝም ብለን በመቀመጥ ወይንም ወያኔ በሚፈፅመው ግፍ በማዘን እና በመቆጨት ብቻ ተጠምደን እያንዳንዳችን የቻልነውን ያህል ጠጠር ከመወርወር ከተቆጠብን ፣ “ነገ ሀገር እና ሕዝብ የሚባል ይኖረናል ወይ?” ብለን የምንጠይቅበት ደረጃ ላይ የደረስን በመሆኑ፣
  • በሀገር ቤት ያሉ ወገኖቻችን የእለት ጉሮሯቸውን ዘግተው እየተራቡ እና እየተጠሙ በሕዝባዊ እምቢተኝነቱ ዐውድ የሚያደርጉትን የሞት ሽረት ትግል፤ በውጭ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ወገን የበኩሉን እርምጃ በመውሰድ  አጋርነቱን ማሳየቱ ትግሉን እንደሚያጎለብት የታመነበት በመሆኑ፣
  • ሀገራችን ኢትዮጵያን ለ25 ዓመታት በግፍ እንዲገዛ የኢኮኖሚው ጀርባ አጥንት ሆኖ ያገለገለው ከውጭ ሀገራት በተለያዬ መንገድ እና ምክንያት የሚገባው የውጭ ምንዛሬ በመሆኑና ከዚህም ዉስጥ በዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ለግንባታ፣ ለንግድ እና ለዘመዶቻቸዉ በባንክ በኩል የሚልኩት ህዋላ (remittance) ከፍተኛ ድርሻ ያለዉ በመሆኑ፣
  • በህዝባዊ እምቢተኝነቱ መቀጣጠል ምክንያት ወያኔ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ የገባ በመሆኑ እና ወደ ሀገር ቤት በተለያዬ ምክንያት በሚላከው የውጭ ምንዛሬ ላይ ውጤታማ ተአቅቦ ከተደረገ ሕወሓት መራሹን ዘረኛና ወንበዴያዊ አገዛዝ ውድቀት በእጅጉ የሚያፋጥነው በመሆኑ፣

Monday, December 26, 2016

አዲስ አበባ በእሳት አደጋ ታመሰች 8 መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል በሚሊዮኖች ብር ንብረት በ24 ሰአታት ተቃጥሏል

አባይ ሚዲያ ዜና
ዘርይሁን ሹመቴ
አዲስ አበባ ከወትሮ ለየት ባለ ሁኔታ በበተለያዩ ስፍራዎች 24ሰአት በልሞላ ሰአት ውስጥ አስተናግዳለች። የእሳት አደጋው በንብረት ላይ ከፍተኛ ጎዳት አድርሷል። ከመረጃዎች መረዳት እንደሚቻለው በአብዛኛው የንግድ ሱቆች በእሳት አደጋው ወድመዋል።
የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ መከላከያና መቆጣጠሪያ ባለስልጣን የኮምንኬሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ ንጋቱ ማሞ እንደገለጹት አደጋው የተከሰተው በዋናው ፖስታ ቤት በአራዳና በጉለሊ ክፍለ ከተማ እንደሆነ መረዳት ተችሏል።
የዋናው ፖስታ ቤት ንብረት የሆኑት ሱቆች በእሳት በመንደዳቸው በግምት ከ500 ሺህ ብር በላይ ንብረት ጠፍቷል። ይህም በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከሌሊቱ ሰአት እንደሆነ ከኮምንኬሽኑ ገለጻ መረዳት ተችሏል።

የ21ኛው ክፍለ – ዘመን የአማራ ይሁዲ (ማተቤ መለሰ ተሰማ)

(ማተቤ መለሰ ተሰማ)
በ20ኛው ክፍለ ዘመን የአርያንን ዘር በዓለም ላይ ማንገስን ሰነቆ የተነሳው የጀርመኑ ናዚ በይሁዲያዊያን ላይ የፈጸመው የዘር ማጥፋት ሰቆቃ ዛሪ ድረስ የዓለምን ህዝብ ሲያሳዝን ይገኛል። አሁን በ21ኛው ክፍለዘመን ደግሞ ወያኔ አማራንና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታይ የሆነውን ኢትዮጵያውያን ከምድረገጽ ለማስወገድ ከጀርመኑ ናዚ ሺህ ጊዜ የከፋና በዚህ ዘመን ሰው ያደርገዋል ተብሎ የማይታስብ ዘግናኝ ድርጊት በመፈጸም ላይ ነው።

Sunday, December 25, 2016

የአፈናውና ሰቆቃው መጠናከር ለነጻነታችን ከምናደርገው ትግል አይገታንም።

Image may contain: one or more people, people standing, child and outdoorህወሃት ህዝባችን ለነጸነቱ የሚያካሂደውን ትግል ለመቀልበስ የፈለገውን ያህል ጉልበት ለመጠቀም ቢፍጨረጨር ፤ እስር ግድያና የማሳደድ ተግባሩን አጠናክሮ ቢቀጥል ከህዝባችን ልብ የበለጠ እየራቀ፤ የጥላቻና የበቀል እርምጃ የሚቀሰቅስ ወኔ ለምናካሄደው ትግል ይፈጥር እንደሆነ እንጂ ከጀመርነው የነጻነት ትግል ወደ ኋላ እንደማይገታን አርበኞች ግንቦት 7 በጽናት ያምናል።

የአፈናውና ሰቆቃው መጠናከር ለነጻነታችን ከምናደርገው ትግል አይገታንም። December 24, 2016

የመንግሥትን በትረ ሥልጣን በጠመንጃ ሃይል ተቆጣጥረው ያሉት የህወሃት ከፍተኛ አመራሮች ላለፉት 25 አመታት በህዝባችን ላይ ተንሰራፍተው  የዘረፉት የአገር ሃብት ፤ በአገር ውስጥና ከአገር ውጪ  በየባንኩ ያከማቹት ጥሬ ገንዘብና በዘመድ አዝማዶቻቸው ሥም እዚህና እዚያ የዘረጉዋቸው የንግድ ድርጅቶች ብዛት እንዲሁም ያለዕውቀታቸውና ልምዳቸው ለሩብ አመታት ሲሿሿሙበት የኖሩት ሹመትና ማዕረግ  አሁንም ቢሆን በቃኝ ከሚሉበት ደረጃ እንዳላደረሳቸው ሥልጣንን በሰላማዊ መንገድ እንዲያስረክቡ የተቃውሞ ድምጻቸውን በሚያሰሙ ወገኖቻችን ላይ እየወሰዱት ካለው ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ መረዳት ይቻላል።

Friday, December 23, 2016

የትንሳዔ ሬድዮ የዕለተ አርብ ፕሮግራም፣ ወቅታዊ ዜና፣ ሌሎችም መደበኛ ፕሮግራሞች ትንሳዔ ለኢትዮጵያ!! Tinsae Radio Dec 23 2016

The West has Emboldened the Ethiopian Regime to Continue with Its Repressive Rule!! =========================== Patriotic Ginbot 7


No automatic alt text available.The brutal and inhuman treatment of Ethiopians by the ruling clique, the TPLF/EPRDF over the last 25 years has been met by little challenges or any serious question by the donor governments of the West who provide the regime with lavish aid. The West in general and the United States government in particular chose to ignore the widespread human rights violations by the regime.

The West has Emboldened the Ethiopian Regime to Continue with Its Repressive Rule!! (Patriotic Ginbot 7)

Patriotic Ginbot 7
The brutal and inhuman treatment of Ethiopians by the ruling clique, the TPLF/EPRDF over the last 25 years has been met by little challenges or any serious question by the donor governments of the West who provide the regime with lavish aid. The West in general and the United States government in particular chose to ignore the widespread human rights violations by the regime. The Ethiopian ruling clique rode the international antiterrorism bandwagon and is effectively using it to shield itself from questions and accountability for the terrorism it commits against the people it rules. Ethiopia continues to become the destination of the largest Western aid in sub-Sahara Africa in spite of continuous reports by human rights organizations about widespread violations of human rights. In all its annual country reports, the US State Department human rights section has also reported grave violations of human rights in the country. The only reactions to note from the West, particularly the US, are the numerous and repeated expressions of “concern” over incidents of human rights violations. There has never been any practical and meaningful action taken to pressure the government to change its coursebehavior. The sad result of these consistent appeasement has been the emboldening of the regime to continue with its grave violations of human rights that in many instances included genocidal massacres of citizens.
The much talked about recent visit by the US Assistant Secretary of State for Democracy, Human Rights, and Labor Affairs, Mr. Tom Malinowski, to Ethiopia is reported to have raised some of the concerns of the US government regarding human rights violations that the regime executes using the current state of emergency as a cover. Sadly, Ethiopians expect that this visit and the talks with regime officials would not be any different from the previous ones and think that it would bring no significant changes to the deteriorating and dangerous conditions in the country. The West has completely failed to understand that the regime has made a final decision on using force as the only choice to stay in power. Any observer of conditions in Ethiopia clearly notes a growing pattern of repression, use of force and closure of political space for the opposition after the 2005 election where the ruling clique lost and recovered its power by repression and force. From these experiences the regime learnt that democracy and free and fair elections, freedom of expression, independent media, and civil society are its enemies. The regime decreed its antiterrorism law with the objective of accusing and eliminating peacefully working leaders of the opposition and journalists as well as potential political leaders. There have been numerous human rights reports that can be cited to show that the antiterrorism law has been extensively used to quell opposition activities. By so doing the regime has succeeded in closing all political space so much that, during the last national election in 2015, it succeeded in “winning” all the seats in the national parliament.
From their repeated agonizing experiences, the Ethiopian people too have learnt their lessons. They have concluded that the West has almost become an accomplice of the regime in their suffering. They are tired of the lip service given by Westerners about democracy and human rights. Ethiopians, particularly young people, are increasingly leaving the peaceful political discourse in droves and choosing the use of force as the only option left for them to change the government and their dire circumstances. More and more young people are raising arms and organizing protests that sometimes turn out violent. Meanwhile the repression by the regime intensifies and feeds this general public resolve.
Understandably the west does this appeasement for its objective of building its antiterrorism block. While this may be useful to the West temporarily, the gradual deterioration of the human conditions in Ethiopia is heading to the collapse of the system leading to a dangerous destabilization that could pose serious danger, not only to the country, but to the entire region. Patriotic Ginbot 7 movement for unity and democracy would like to We warn the West that the Ethiopia policy it currently pursues and the toothless talks with the regime are leading the country to a dangerous end. The only way the West can avoid a dangerous situation Ethiopia is currently facing we believe, is by resorting to using meaningful and coercive tools to change the behavior of the regime and force it to introduce fundamental changes in the country without further delay.
Ethiopia shall prevail

Patriotic Ginbot 7 Public relation

የዶ/ር መረራ መታሰር ሰላማዊው ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል የተደረገ ጥሪ ነው!!! – መላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን)

ላ ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን)Bilderesultat for መራራ ጉዲና
መረራ ጉዲና ገና ከለጋ ወጣትነት ህይወቱ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ባልተቋረጠ ወኔና ጥራት ለአንዲት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ ሲታገል የኖረ ዜጋ ነው፡፡ በዚህ ያልተቋረጠ ተጋድሎው በንገሱ ዘመን አምቦ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ ሆኖ በተማሪው ንቅናቄ በነበረው ንቁ ተሳትፎ ለአጭር ጊዜም ቢሆን እስር ቤት ተወርውሯል፡፡ በደርጉ ዘመን ደግሞ በመኢሶን ታጋይነቱ ለሰባት አመታት በእስር ተንገላቷል፡፡ ለአለፉት 25 አመታት ደግሞ የወያኔ ኢህአዴግን ግፈኛ አገዛዝ በመቃወም በሰላማዊና ህጋዊ የትግል ስልት ተሰማርቶ ከነዚህ የጥፋት ሃይሎች አንጻር እነሱ ከፋፍለህ ግዛን ሲያራመዱ የህዝቦች ወንድማማችነትን እየሰበከ፣ እነሱ ለስልጣናቸው ሲሉ በለየለት የአፋኝና የአመጽ ጎዳና ሲሰማሩ ዴሞክራሲን፣ ሰላምንና ህጋዊነትን እያነገበ ሲሞግታቸውና ሲታገላቸው በህዝባችን ፊት ተአማኒነትንና ተወዳጅነትን ያተረፈ ብርቅየ የኢትዮጵያ ልጅ ነው፡፡

ሰበር ዜና 'ማርሽ ቀያሪው' በሚል መጠሪያ የሚታወቀው አትሌት ምሩጽ ይፍጠር ማምሻውን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። በካናዳ ቶሮንቶ በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ህይወቱ ማለፉን ለማወቅ ተችሏል። Two-time Olympic champion Miruts Yifter passed away at 72

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ



በሰሜን ጎንደር የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄን ተከትሎ እስራትና ግድያው ተጠናክሮ እንደቀጠለ ሲሆን የማንነት ጥያቄ አቅራቢውም ህዝብ ትጥቁን እያጠባበቀ ወደ ጫካ እየከተተ መሆኑ ታውቋል ፡፡No automatic alt text available.
ባለፈው ታህሳስ 9 ቀን 2009 ዓ.ም. የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አባላት የሆኑት አቶ ዘውዱ ገ/እግዚያብሄርና አቶ ሙላው ከበደ በመተማ ወረዳ ልዩ ስሙ ስናር በተባለው አካባቢ በወያኔ መከላከያ ሰራዊት ተከበው የነበረ ሲሆን ከዚህ ከበባ ለመውጣት ከስርዓቱ ታጣቂ ሃይሎች ጋር ውጊያ በማድረግ አቶ ዘውዱ ገ/እግዚያብሄር 5 የወያኔ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ገድሎ እርሱም በክብር ተሰውቷል ፡፡ ወያኔም እነዚህን ሁለት ሰዎች አስከሬን አይቀበርም ብሎ በጠራራ ፀሃይ መሬት ላይ አስጥቶ እንዲውሉ ቢያደርግም የአካባቢው ህዝብ ባደረገው ጫና ምክንያት ህዝቡ ቃፍታ ወስዶ ቀብሯቸዋል ፡፡

Thursday, December 22, 2016

በአምቦ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ከተማዋ ለሁለተኛ ቀን ውጥረት ሰፍኖባት ዋለ ታኅሣሥ ፲፫ (አሥራ ሦስት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-

 የአምቦ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ትናንት ትምህርት በማቆም በእስር ላይ የሚገኙ ተማሪዎች እንዲፈቱ እንዲሁም በተማሪዎች ላይ ጉዳት ያደረሱት ለፍርድ እንዲቀርቡ ሲጠይቁ ከዋሉ በሁዋላ፣ የአጋዚ ወታደሮች ወደ ግቢው በመግባት በተማሪዎች ላይ ከፍተኛ ድብደባ ፈጽመዋል። በርካታ ተማሪዎችንም ይዘው አስረዋል።Image may contain: one or more people, people standing, people walking and crowd

ዛሬ ሃሙስ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የአጋዚ ወታደር ወደ ከተማዋ በማምራት ሁሉንም ትምህርት ቤቶች ከቦ ያረፈደ ሲሆን፣ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ከትምህርት ቤት እንዳይወጡ እና የወጡትም እንዳይገቡ ታድርጓል። ተማሪዎቹ ዶ/ር መረራ ጉዲና ፣ አቶ በቀለ ገርባና ሌሎችም በእስር ላይ የሚገኙ ጓደኞቻቸው እንዲፈቱ ጠይቀዋል። ባለፈው ተቃውሞ ወቅት በድብደባ ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበት የነበረውና አሁንም ድረስ የአልጋ ቁራኛ የሆነውና በሞት እና ህይወት መካካል የሚገኘው  የተማሪ ወሊሶ ደብዳቢዎች ለፍርድ እንዲቀርቡም ተማሪዎች ጠይቀዋል።
ተማሪዎቹ የህወሃት ድርጅት የሆነውን የትራንስ ኢትዮጵያ ተሳቢ የጭነት ተሽካሪዎች ላይ ድንጋይ በመወርወር መስታውቶችን አርግፈዋል። ስለአካባቢው ሁኔታ ጥያቄ ያቀረብንለት የከተማው ነዋሪ፣ ከተማዋ በወታደሮች መወረሩዋን ተናግሯል ። ገዢው ፓርቲ ከ9 ሺ በላይ ሰዎችን መልቀቁን እያስታወቀ ባለበት ሰአት አሁንም በኦሮምያ የተለያዩ ቦታዎች ወጣቶችን ይዞ እያሰረ ነው።
በሌላ በኩል አላጌ እስር ቤት ውስጥ የነበሩት በሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞች ተፈትተው ወደ መኖሪያ አካባቢያቸው ሲመለሱ፣ ህዝቡ መንገድ ላይ ወጥቶ እጁን እያጣመረ ለወጣቶች ያለውን ድጋፍና በአገዛዙ ላይ ያለውን ተቃውሞ ገልጿል። አንድ ዛሬ ሃሙስ የተለቀቀ ወጣት፣ ህዝቡ መሃል መንገድ ላይ እየገባ ድጋፉን በመግለጽ ለመጓዝ  ሁሉ ተቸግረን ነበር ብሎአል። የሻሸመኔ፣ ቡልቡልና ነገሌ  ከተሞች ወጣቶች ባሳዩዋቸው  ድጋፍ ልቡ መነካቱንም ገልጿል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናንት ታህሳስ 12፣ በቡሌ ሆራ ትልቁ ገበያ በሚውልበት ቀን አንድ መኪና ኮንትሮባንድ ጭኖ አልፏል በሚል ወታደሮች በተኮሱት ጥይት የአንድ ወጣት ህይወት አልፏል። የከተማው ነዋሪዎች እንደሚሉት ወጣቱ ሆን ተብሎ ተገድሏል።

የጎንደር ሁኔታ የሀገሪቱ "መርዛም" ፖለቲካ ማሳያ ነው፦ዘጋርዲያን ጋዜጣ።/አዋዜ አፕ 1ን ይጫኑ/ The predicament of Gondar is the creation of "toxic"poletics in the coun...

በጐንደር ክፍለ ሀገር ከወልቃይት ጠገዴና ጠለምት የአማራ ማንነት አስተባባሪ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ!!

በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ሕዝብ ላይ ወራሪውና ደም ጠጭው የህወሃት ፀረ-ሕዝብ ቡድን ጀግኖችን እያሳደዱ መግደል ማሰደድና ሀብታቸውን መዝረፍ የጀመረው ከዛሬ 40 ዓመት በፊት ቢሆንም የሚፈፀምባቸውን ግፍ በልባቸው አምቀው በመያዝ ጊዜና የሕግ የበላይነት ሲሰፍን በሕግ እንፋረዳለን ብለው ዝምታን የመረጡ ቢሆንም ተስፋፊው የሕወሃት ቡድን ማንኛውንም ጉዳይ ለማስፈፀምም ሆነ ለመማር በትግርኛ ነው እናንተም ትግሬዎች ናችሁ ትግሬ አይደለንም የምትሉ አባይን ተሻግራችሁ ትሄዳላችሁ እንጅ አማራዎች ነን እያላችሁ በትግራይ ክልል መኖር አትችሉም በማለት አካባቢውን ያቀኑትን ተወላጆች አሳዶ ከአካባቢው እንዲጠፉ ማድረጉ ይታወቃል። በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ እንዲሉ ሀብት ንብረታቸውን ተዘርፈው ተወልደው ያደጉበትን አጥቢያቸውን ለቀው ሄደው ተሰደው ከሚኖሩበት የጐረቤት አካባቢ ሰላዮችን በመላክና አፋኞችን አሠማርቶ የግድያ ወንጀል ላይ ተሰማርቷል። በዚህ ባሳለፍናቸው ሁለት ቀናት ውስጥም ሮጠው ያልጠገቡ የጐልማሳነት ዘመናቸውን ተደብቀው ለማሳለፍ ወደ አርማጭሆ ሄደው ከሚኖሩበት ገዳይ ኃይል በማሠማራት አካባቢው በተማረ የሰው ኃይልም እንዲደኸይ ለማድረግ ባለው እቅድ መሠረት ሁለት ቀምበጥ የወልቃይ ወጣቶችን ገድሏል።

Wednesday, December 21, 2016

በሰሜን ጎንደር የነጻነት ሃይሎች፣ አርሶአደሮችና የታጠቁ ሃይሎች በገዢው ፓርቲ ወታደሮች ላይ የሚያደርሱት ጥቃት መጨመሩን ተከትሎ፣ አገዛዙ ሰራባ ላይ 46ኛ ክፍለ ጦር ለማቋቋምና ሰራባን የጦር መሳልጠኛ ለማድረግ ማሰቡንም ምንጮች ገልጸዋል።


ታኅሣሥ ፲፪ (አሥራ ሁለት)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :Bilderesultat for ethiopian mekelakeya serawit


ሰራባ የሚገነባው ክፍለጦር፣ አዘዞ ሎዛ ማሪያም ላይ ያለው 24ኛው ክፍለ ጦር ፈርሶ ይሁን ወይም ተጨማሪ አልታወቀም። በዞኑ ወታደራዊ ፍተሻው ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፣ ፍተሻው በአዘዞ ፣ ሰራባ፣ ነጋዴ ባህርና ሸህዲ ላይ ይካሄዳል። የአገዛዙ ወታደራዊ አዛዦች፣ በአሁኑ ሰአት ራሳቸውን የሰወሩትን የነጻነት ሃይሎች ያሉበትን ቦታ ለማወቅ በሽምግልና ስም እንቅስቃሴ ጀምረዋል። አዲሱ በሽምግልና ስም የሚካሄደው እንቅስቃሴ በአንድ በኩል ከተሳካ በሽምግልና ስም አግባብቶ በምህረት እጅ በማሰጠት ታጋዮችን ለመያዝ፣ ካልተሳካ ደግሞ ሽማግሌዎች የታጋዮቹ አመራሮች ያሉበትን ቦታ እንዲጠቁሙ ለማድረግ መሆኑን ምንጮች ይገልጻሉ። በቅርቡ ተደርገው በነበሩት ተደጋጋሚ ውጊያዎች ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት፣ የጸረ ሽምቅ አዛዡን ጨምሮ በጦር ሜዳ የተሰለፉትን ተዋጊዎቹን ሳይቀር ይዞ እያሰረ ነው።

የሳዑዲ ባለ ሥልጣን ለኢትዮጵያ የአባይ ግድብ አገራቸው ምንም የገንዘብ ድጋፍ አታደርግም አሉ፤


በመሃከለኛው ምስራቅ የእቅድና ህግ ጥናት ምርምር ሃላፊ አንዋር እሽኪ፣ በመገናኛ ምንጮች ሳውዲ አርቢያ ለኢትዮጵያ የአባይ ግድብ ግንባታ ብድር ለመስጠት አስባ ነበር አስባ ነበር ተብሎ መመዝገቡ ትክክለኛ አይደለም ሲሉ ዚናውን አስተባበሉ።

ጡረተኛው ጄነራል አሽኪ ለሚስር አል አረቢያ ዜና ሲገልፁ የሳዑዲ አረቢያ ንጉሣዊ አካል አማካሪና የሳዑዲ የግንባታ ገንዘብ ክፍል ቦርድ ሰብሳቢ አህመድ አል ካታቢ፣ ስለ ሁለቱ አገሮች የጋራ ግንኙነት እና የምጣኔ ሃብት እቅዶችን ሊነጋገሩ እንደነበር ገልፅው፣ የአል ካታቢ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ያረጉት ጉብኝት፣ ግብፅ የሳዑዲ መንግሥት የሚቃውመውን በፕሬዝደንት ባሺር አል አሳድ ለሚመራው የሲርያ መንግሥት የሰጠችውን ድጋፍ ለመበቀል ነው ተብሎ የተዘገበው ሃሰት ዜና ነው በማለት አስተባበለውታል።

ሰበር መረጃ — የላክናቸው ሁሉ አይመለሱም የሰሜን ዕዝ ስምሪት ማዘዣ!

በልኡል አለም በሕወሃት ኮማንድ ፖስት ቁጥጥር ስር የወደቀው የሰሜኑ እዝ ወደ ሰሜን እና ደቡብ ጎንደር የላካቸው በወታደራዊ ደህንነት እና በወታደራዊ ምህንድስና የተሰማሩ አባላቶቹ መገደላቸውንና መሰወራቸውን ለኮማንድ ፓስቱ በላከው ሪፖርት ለማወቅ ተችሎአል።Bilderesultat for የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ቀን በሪፓርቱ መሰረት፣ 1. ወታደር መሀንዲስ ትህትና በለው 2. ወታደራዊ የደህንነት አባል ቃሲም ይማም 3. ወታደር መሀንዲስ ዝናቡ ሕንጻ 4. ኮማንደር ማንያዝ ገብሬ 5. ወታደር ማሀንዲስ ቃቄ የደረሱበት ያልታወቀ መሆኑን መረጃዋች ሲጠቁሙ… 1. የ10 አለቃ ስንሻቅ 2. ጓድ መሪ ወ/ር መሀሪ ጎላ 3. ወታደራዊ ደህንንት አባል ወ/ር ሶስና ፍስሀዬ 4. ወ/ር ገላው ስንቄ 5. ወ/ር ምጅዱ 6. ወ/ር አለሞ አጋፋሪ 7. ጋረድ ብሻፍለጋው የተባሉ የመረጃና የቅኝት ወታደሮች በህዝባዊ ሃይሉ መበላታቸው ተረጋግጧል። በተያያዘ መረጃ ከኦጋዴን ነፃ አውጪ ግንባር ጋር ውጊያ የገጥመው የምሥራቅ እዝ ከሶማሌያ የተወረወረ የኦነግ ሐይል አስግቶኛል በሚልመነሻ ወደ ሰሜን ዕዝ የተዛወረው ብረት ለበስ ሜካናይዝድ ይመለስልን ሲል ለመከላከያ ሚንስቴር ዘመቻ መምሪያ አመራርሮች ጥያቄ አቅርቦአል። መከላከያ ሚኒስቴሩ በኮማንድ ፓስቱ ወታደራዊ ስልት በሚዘወርበት በዚህ ሰዓት መአክላዊ ዕዝ ውስጥ የተካተቱ ወታደሮች የፌደራል ፖሊስን ደርበን አናግዝም በማለታቸው በአዲስ አበባ ዙሪያ ሊቀሰቀሱ የሚችሉ ነውጦችን መቆጣጠር የማይቻልበት አደጋ እንደሚያመጣ ምንጮች ገልፀዋል። ዽል ለኢትዮጵያ ህዝብ! - See more at: http://ecadforum.com/Amharic/archives/17294/#sthash.YEw6SmWG.dpuf

ሞሮኮ የሚገኘው የሼክ አል አሙዲ ነዳጅ ማጣሪያ በፍርድ ቤት እንዲፈርስ ታዘዘ

የሼክ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ኩባንያ የሆነው ኮራል ፔትሮሊየም ሆልዲንግስ 67 በመቶ ድርሻ በመያዝ የሚያስተዳድረውና በሞሮኮ ብቸኛው የነዳጅ ማጣሪያ እንደሆነ የሚነገርለት ሳሚር ግሩፕ በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይፍረስ የተባለው ባጋጠመው የገንዘብ ቀውስ ምክንያት መሆኑ ታውቋል፡፡ የሞሮኮ መንግሥት 1.34 ቢሊዮን ዶላር የታክስ ዕዳ እንዳለበት አስታውቋል
http://amharic.abbaymedia.com
በቀን 200 ሺሕ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ የማጣራት አቅም ያለው ሳሚር ግሩፕ ባጋጠመው የፋይናንስ ቀውስ ሳቢያ፣ ካለፈው ነሐሴ ወር ጀምሮ ሥራ ለማቆም ተገዷል ያለው የሮይተርስ ዘገባ ሲሆን የሞሮኮ ፍርድ ቤትም ቀውሱን ተከትሎ ኩባንያው እንዲፈርስ ወስኗል፡፡ ኩባንያውን የማፍረስና በሽያጭ ወደ ሌሎች የማስተላለፍ ሒደት እንዲመሩ የንብረት ጠባቂ ግለሰብ በመሰየም ሽያጩ እንዲከናወን አዟል፡፡