ኅዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወታደሮቹ ከአርበኞች ግንቦት7 ጋር ተቀላቅለው በስልጣን ላይ ያለውን ሃይል ለመዋጋት ቃል መግባታቸውን የግንባሩ የአመራር አባል ገልጸዋል። ወታደሮቹ 9 መትረጊስ፣ 6 ስናይፐር፣ሁለት ዲሽቃና አንድ አርፒጂ መያዛቸውን አመራሩ ተናግረዋል። “ወታደሮቹ ግንባሩን የተቀላቀሉት ኤርትራ ነው ወይ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ፣ አመራሩ ሲመልሱ፣ “ እኛ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ስልጠናውን የምንስጠው፣ የእኛ ሰራዊት ዋናው ማሰልጠኛው ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኗል። ከአሁን በሁዋላ እኛን የሚቀላቀሉ ወታደሮችም ሆኑ አዲስ ምልምሎች ስልጠና የሚሰጣቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ይሆናል ብለዋል። አገዛዙን ከድተው ወደ አርበኞች ግንቦት 7 የተቀላቀሉትን ወታደሮች በተመለከተ በገዢው ፓርቲ በኩል እስካሁን የተሰጠ መግለጫ የለም። አርበኞች ግንቦት7 ኢትዮጵያ ውስጥ ወታደራዊ ስልጠና መስጠት መጀመሩን መግለጹ ይታወቃል። በሰሜን ጎንደር አካባቢዎች የሚደረገው ጦርነት እየተጠናከ መምጣቱን ምንጮች ይገልጻሉ።
No comments:
Post a Comment