አባይ ሚዲያ ዜና
(ዘርይሁን ሹመቴ)
የወያኔን አገዛዝ በመክዳት ወደ ትጥቅ ትግሉ እየተቀላቀሉ የሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት ቁጥር እየጨመረ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ። በቅርቡ በሰሜን ጎንደር ለነጻነት እየተዋደቁ ያሉትን ጀግኖች የአማራ ተወላጆችን ለመጨረስ ወያኔ ከላካቸው ወታደሮች አብዛኞቹ ወደ አርበኞች ግንቦት 7 ግንባር መቀላቀላቸው ይታወቃል። በቆራጥነት ቤተሰባቸውን ጥለው በየጫካው የሽምቅ ውጊያ በማድረግ ወያኔን እያርበደበዱ ያሉትን የአማራ ታጋዮችን ትጥቅ ለማስፈታት የሚልካቸው ወታደሮች ከነሙሉ ትጥቃቸው ወያኔን እራሱን ለመውጋት ከህዝቡ ጎን ለመቆም ግንባሩን ተቀላቅለዋል።
አገዛዙ የአርበኞች ግንቦት 7 ሰርጎ ገቦች ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ ያዝከዎቸው ከማለት በስተቀር ከመከላከያ ሰራዊት እየከዱ አርበኞች ግንቦት 7ን ስለሚቀላቀሉ ሰራዊት መግለጫ ሲሰጥ አይሰማም። በብዛት ኤርትራ የሰለጠኑና የሰፈሩ ብሎ ወያኔ የሚፈርጃቸው የአርበኞች ግንቦት 7 ወታደሮች በተቃራኒው በመላ ኢትዮጵያ በተለያየ መልኩ በጥልቀት ገብተው ራስ ምታት እየሆኑበትና የነጻነት ትግሉን እዚያው አገር ውስጥ እያደረጉ እንደሚገኙ ወያኔ ራሱ ለመካድ አዳጋች ደረጃ ላይ ደርሷል። በቅርቡም በሰሜን ጎንደር ህዝቡን በማነሳሳት በማደራጀት እንዲሁም ወታደራዊ እርምጃ ሲወስዱ በቁጥጥር ስር አዋልኩዋቸው ባላቸው የአርበኞች ግንቦት 7 ና የኦነግ አባላት ላይ ክስ መስርቻለው በማለት አገዛዙ በርግጥም የትጥቅ ትግሉ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረገ እንደሆነ ማመን ችሏል።
በመከላከያ ሰራዊት ውስጥም ሳይቀር የአርበኞች ግንቦት 7 አባላት ሰርገው ገብተውብኛል በማለት የተለያዩ ክሶችን አሁን አሁን እያቀረበ የሚገኘው የህውሃት አገዛዛ ከዚህ ቀደም ይህን በይፋ ለማመን ተቸግሮ እንደነበር ይታወቃል። የአርበኞች ግንቦት 7 ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተደጋጋሚ ለመከላከያ ሰራዊቱ የወያኔ መጠቀሚያ ከመሆን የህዝብ አጋርነትን እንዲያሳይና ግንባሩን ተቀላቅሎ በአገዛዙ ላይ አፈ ሙዙን እንዲያዞር ያደረጉት ጥሪ በብዙ ለሚቆጠሩ ወታደሮች መክዳትና ወደ ነጻነት ጉዞው መቀላቀል አስተዋጾ አድርጋል።
አገዛዙ በአቃቢ ህጉ በኩል የአርበኞች ግንቦት 7 የአገር ውስጥ አባላት በተንቀሳቃሽ ስልክና በፌስቡክ በመጠቀም አዳዲስ አባላትን በደብረ ዘይትና በተለያዩ የመከላከያ ሠራዊት እየመለመሉ እንደሚገኙ ደርሸበታለው በማለት ባሳለፍነው አርብ ክስ መስርቷል። ከዚህ በተጨማሪም የአርበኞች ግንቦት 7 የአገር ውስጥ እንቅስቃሴ መረቡን በማስፋት በመረጃና ደኅንነት መስሪያ ቤትም ውስጥም ዘልቆ እንደገባ ክሱ ያመለክታል። በዚሁ እለት በቀረበው ችሎት ወያኔ ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር በመተባበር ሲሰሩ የነበሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላትንም ወደ ክስ አቅርቢያለው ብሏል።በአጠቃላይ ከወያኔ ጋር የሚደረገው ትግል በርግጥም በኤርትራ ምድር ሳይሆን በኢትዮጵያ ውስጥ መሆኑንና የህዝቡ እምቢተኛነት የነጻነት ታጋዮችን እንቅስቃሴ ወደ ፊት እየመራው እንደሆነ አገዛዙ በአቃቤ ህጉ ያቀረባቸው ክሶች ማመሳከሪያ ሆነዋል።
No comments:
Post a Comment