አባይ ሚዲያ
ናትናኤል ኃይለማርያም
በዉጭ ያለዉ ኢትዮጵያዊ ስደተኛ በአገር ዉስጥ ባለዉ ፖለቲካ ከፍተኛ ተፅዕኖ መፍጠር መቻሉ ተዘገብ። በተለይ ባለፈዉ ኦክቶምበር 2 2016 የኦሮሞ ማሕበረሰብ የኢሬቻን ባሕል ለማክበር በወጡበት ጊዜ ከ750 ሰዉ በላይ በሒሊኮፕተር ጭምር በመተኮስ ከገደሉ በኋላ በዉጭ የሚገኘዉ ኢትዮጵያዊ በሶሻል ሚዲያዎችና በሳተላይት ቴሌቪዥን የፖለቲካዉን መስመር እያስያዘ መምጣቱን አሜሪካ ዘገበች።
ከዚህ የኢሬቻ በዓል ማግስት ጀምሮ በአገሪቷ ዉስጥ የሚካሔደዉ ችግር እየተባባሰ በመሔድ በነበረዉ ቀጣይ ሳምንት የዉጭ አገር ሰዎች ሃብት የሆኑትን ፋብሪካዎች፤ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን፤ የጎብኝዎችን ማረፊያ እና የአገዛዙን ሃብትና ንብረት የሆኑትን መቃጠላቸዉ የታወሳል። ይኽንንም ተከትሎ የሕዉሐት አገዛዝ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሲያዉጀ በዉጭ የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊ የኢንተርኔት ግኑኝነት በመጠቀም አገር ዉስጥ ባለዉ ፖለቲካ ላይ ተፅዕኖ አሳድረዋል። አገር ዉስጥ ሚያካሒዱትንም እንቅስቃሴዎች በቅርበት ይከታተሉ እንደነበርም ተዘግቧል።
በአለም ላይ የሚገኘዉ ኢትዮጵያዊ ወደ 2 ሚሊዮን የሚጠጋ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ ከ 250 ሺህ እስከ 1 ሚሊዮን ሚደርሰዉ የሚገኘዉ በዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካ ነዉ። ሕዉሐት የኦሮሞ መሬትን በነጠቀም ጊዜ በአሜሪካ የሚገኙት የኦሮሞ ማሕበረሰቦች ተቃዉሟቸዉን ያሰሙ ሲሆን በቁጥር 2ኛ የሆነዉ የአማራ ማሕበረሰብም ይህንኑ የተቃዉሞ ሰልፍ በመቀላቀል አጋርነቱን አሳይቷል። ዉጤቱም የአለም ሚዲያዉን ትኩረት መሳቡንም አስታውሷል።
በአገር ዉስጥ ያሉት ተቃዋሚዮችም ደካማና የተከፋፈሉ ናቸዉ የሚለዉ ይኸዉ ሪፖርት አቶ ሐሰንን በዕማኝነት ጠቅሶ የሕዉሐት አስተዳደር በሚያደርገዉ ተንኮልና ሴራ እንዲሁም ተፅዕኖ ተቃዋሚዉን እንደሚያዳክም ሲታወቅ አብዛኛዉንም የተቃዋሚ ፓርቲዎች እርዳታም ሚያገኙት ከዉጭዉ ካለዉ ደጋፊዎቻቸዉ ሲሆን አገር ዉስጥ ያሉት ደጋፊዎቻቸዉ ለደህንነታቸዉ ስጋት ስላለባቸዉ እርዳታ መስጠት የማይችሉበት ደረጃ ላይ መሆናቸዉን በመግለፅ የፖለቲካዉ ምህዳር ትንሽ ክፍተት ቢኖረዉ ከዛዉ ከአገር ዉስጥ ካሉ አባላቶችና ደጋፊዎቻቸዉ በቂ የገንዘብ እና ቁሳቁስ ማግኘት እንደሚችሉም ገለጸዋል። በማያያዝም በኢትዮጵያ ዉስጥ ምንም አይነት የመቻቻል ፖለቲካ እንደማይካሔድም ሲገልጽ ለዚህ ጉልህ ማሳያ ሚሆነዉም በ2005 በተደረገዉ ምርጫ ተቃዋሚዉ ከፍተኛ ቁጥር መቀመጫ አሸናፊ መሆኑ ሲታወቅ ነገር ግን ሕዉሐት ድምፅ መስረቅና በማጭበርበር ዉጤቱን መቀየሩ ይታወሳል በዚህም ሳቢያ በዉጭ ያለዉ የተቃዋሚዉ ደጋፊ ከፍተኛ ተፅዕኖ ማሳደራቸዉ የሚታወቅ ነዉ።
ሚዲያንም በተመለከተ የመንግስት የዜና አዉታር ታማኒነት የሌለዉ ሲሆን መንግስት የኢንተርኔት አጠቃቀምን ዉስን በማድረጉ ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበት ራሱን ለጉዳት መዳረጉን አና የገባዉንም ቃል መጠበቅ ባለመቻሉ እንዳፈረ የዲጂታል መብትና አጠቃቀም በአለም ላይ ካምፓይን የሚያደርጉት አቶ ዲጂ አሉኮቱን ዋቢ በማድረግ አትቷል። ሌሎች በኢትዮጵያ ኦን ላይን ሚዲያ ከሚሳተፉት አንዱ የአዲስ አበባ ብሎገር አቶ ዳንኤል ብርሓኔ ሕዉሐት ዉጭ ባሉ ኢትዮጵያዉያን የሚደርስበትን ወቀሳ በጥሩ ጎኑ ከመመልከት ይልቅ ወቀሳውን በክፉ በማየት የሶሻል ሚዲያ፤ የራዲዮ እና የቲሊቪዥን ስርጭቶችን ማፈኑ በማስረጃ የሚታይ መሆኑንም ገልጿል። የሚዲያው መታፈን በኢኮኖሚዉ ላይም ጉዳት ማድረሱን ከ2015ዓ.ም አጋማሽ እስከ 2016ዓ.ም አጋማሽ ድረስ 8 ሚሊዮን ዩሮ ኪሳራ እንደደረሰበት መቀመጫዉን አሜሪካ ያደረገዉ Center of technology innovation ይፋ አዉጥቶታል። አገር ዉስጥ ያሉትም ኢትዮጵያዉያኖች የመንግስትን ሚዲያዎች ላይ አመኔታ ሰለሌላቸዉ አብዛኛዉን ዜናም ሆነ መረጃ የሚያግኙት ኢሳት እየተባለ መቀመጫዉን አሜሪካና አዉሮፓ ካደረገዉ የሳተላየት ቲሌቪዥን መሆኑንም አትቷል።
ከዚሁ የኢንተርኔት አፈና ጋር በተያያዘ አገሪቷ ዉስጥ ከአካባቢዉ ነጋዴ አንስቶ እስከ ኢምባሲ ከኢንተርናሽናል እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች እስከ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የችግሩ ሰለባ መሆናቸዉን ኬንያ የሚገኘዉ ስታርት ሞር ዩኒቨርስቲ ዉስጥ የኢንተርኔት ፖሊሲ ጥናት ሚያደርጉት ሞስስ ካራንጃ ሲገልፁ አያይዘዉም ኢንተርኔት በማፈንና በመሰለል የሚካሔደዉን ትግል መግታትም ሆነ ማቆም እንደማይቻልም አስረድተዋል።
I hate reading your page because of the color of your font and background
ReplyDelete