በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመላው አገሪቱ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማክሸፍ ተግቶ እየሠራ ያለው የህወሃት መራሹ አገዛዝ በአማራ ክልል የሚገኙትን ወጣቶች በስብሰባና በሥልጠና ለቁጥጥር አመቺ ወደ ሆኑ ማዕከሎች ለማሰባሰብ ተግቶ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ለሥርዓቱ ቅርበት ካላቸው ምንጮች ለማወቅ ተችሎአል።
ህወሃት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ባለው በዚህ አዲስ ሴራ በስብሰባ ሥም ወደ ተለያዩ ማዕከላት እን
ዲሰባሰቡ እየተፈለገ ላለው ወጣቶች በቀን ከ30 እስከ 65 ብር የውሎ አበል እንደሚከፈልና የስልጠናውም ጊዜ እስከ 3 ወራት የሚዘልቅ እንደሆነ ታውቆአል። በዚህ በአዲሱ ዕቅድ ህወሃት ልባቸውና መንፈሳቸው በመንግሥት ተቃውሞ ጎራ የተሰለፉ በርካታ ወጣቶችን በቀላሉ በጥቅም መያዝ ይቻላል ከሚል ዕምነት በተጨማሪ ሥልጠናው በሚቆይባቸው ሦስት ወራት ውስጥ ወደ ተለያዩ ማዕከላት የሚሰባሰቡ ወጣቶች በየትኛውም ተቃውሞ እንዳይሳተፉ በመቆጣጠር ጊዜ መግዛት ይቻላል የሚል ተስፋ አገዛዙ ውስጥ አሳድሮአል።
ከዚህ በተጨማሪ ወጣቱ ካለበት የስራ አጥነት ችግር የተነሳ በገንዘብ ይታለላል ተብሎ ስለተገመተ በየቀኑ ከተመደበው የ30ና 65 ብር ዉሎ አበል በተጨማሪ ምግብና የማደሪያ ቦታዎች ይሰጣሉ። ።ከአዲስ ዘመን አካባቢ ያነጋገርናቸዉ ወጣቶች እንደሚሉት በአካባቢዉ ወጣቱ እየተደራጀ እና የነፃነት ታጋዮች ያሉበትን አድራሻ እየፈለገ ወደ ትግል በመቀላቀል ላይ እንደሆነ የመንግስት አካላት ስለሚያዉቁ፣ከፊታችን ባለዉ 6 ወር ዉስጥ በስልጠና ሰበብ ገንዘብ በመክፈል ወጣቱ አካባቢዉን ለቆ እንዳይሄድ ለማድረግ ነዉ በማለት ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል።
No comments:
Post a Comment