Saturday, December 10, 2016

“በጋራ ከማልቀስ፣ በጋራ መታገል አበበ ገላው


Bilderesultat for አበበ ገላው“ከ66ቱ አብዮት ወሳኝ ትምህርት መቅሰም አለብን። የኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ሁለት መሰረታዊ ጥያቄዎች መሬት ላራሹ እና ዳቦ ለተራበው ነበሩ። የኢትዮጵያን ህዝብ መሬት አልባ አድርጎ ሲያስገብር የነበረው ፊውዳላዊ ስርአት የተንኮታኮተው እነዚህ መሰረታዊ ጥያቄዎች በመነሳታቸው ብቻ አልነበረም። ኢትዮጵያውያን ሁሉ በገዥዎችና በተገዢው ጭቁን ህዝብ ያለውን የመደብ ትግል ተረድተው ከዳር እስከዳር በአንድነት መነቃነቅ በመቻላቸው ነበር።
በርግጥ ያለመታደል ሆኖ ያ ህዝባዊ አብዮት በወታደራዊ ሃይል ተቀልብሶ ሌላ አስከፊ አንባገነናዊ ስርአት ተተካ።ከዛ ዘመን በከፋ መልኩ ዛሬ የኢዮጵያን ህዝብ ከመሬቱና ከቀዬው እያፈናቀለ በረሃብ የቀፈደደውን የህዝብ ደም እየመጠጠ በዘር ከፋፍሎ እየቀጠቀጠና እየገደለ የሚገዛ ዘረኛ የውስጥ ቅኝ ገዢ አስተሳሰብ ያለው የጥቂቶች ዘውጋዊ ስርአት በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ተዘርዝሮ የማያልቅ ወንጀል እየፈጸመ ህዝብን በመግዛት ላይ ይገኛል።
ስለዚህም ነው የስርአቱ ሰለባ ሁሉ ልዩነቱን አቻችሎ በዘር ቆጠራ ላይ የተመሰረተውን የህወሃቶች ስርወ መንግስት ከስር መሰረቱ ለመጣል በጋራ መነሳትና መታገል የሚገባው። ሰሞኑን በኦሮሚያ የተነሳው ህዝባዊ አመጽም በድጋሚ ሊያስተምረን የሚገባው መሰረታዊ ጉዳይ ህወሃቶች የስልጣን እድሚያቸውን ለማራዘም የማይፈጽሙት ወንጀል እንደሌለ ነው። የህዝብ ጥያቄ ከመመለስ ይልቅ፣ የኦሮሞን ህዝብ በአሸባሪነት ፈረጆ ጦርነት ማወጅ የስርአቱን ቀቢጽ ተስፋነት በግልጽ አጉልቶ ያሳየ እውነታ ነው።
የህወሃቶች ስርወ መንግስት በስልጣን ላይ እስካለ ድርስ የየትኛው ህዝብ የመብትና የፍትህ፣ የእኩልነትና የነጻነት፣ የመሬትና የዳቦ ጥያቄ ፈጽሞ ሊመለስ እንደማይችል ግልጽ ነው። በመሆኑም በየአቅጣጫውና በየክልሉ የሚደረገውን ትግል ከፍ አድርጎ ብሄራዊ ንቅናቄ መጀመር የግዜው አንገብጋቢ ጉዳይ ስለሆነ ከውጭም ከውስጥም በህብረት ለመታገል ሁላችንም ልዩነቶቻችንን አቻችለን በቅን ልቦና እንነሳ።
በተለይ ደግሞ አክቲቪስቶችና የፖሊቲካ ፓርቲ መሪዎች ለሚቀርቡላችሁ የጋራ የትግል ጥሪዎች ፈጣንና አወንታዊ መልስ እድትሰጡ በጭቁ ህዝባችን ስም እማጸናለሁ።” አንድነት ሃይል ነው!

No comments:

Post a Comment