የአሜሪካን መንግስት ልኡክ የኢትዮጵያ መንግስት ላይ ከተቃውሞው ጋር በተያያዘ የታሰሩ እስረኞችን እንዲፈታ ማስገደዱታወቀ።
በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ የሄደው የኦባማ አስተዳደር ሉእክ ከኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር ውይይት ካደረገ በሆላተከትሎ እሰረኞቹ እንዲፈቱ አድርገዋል።
ወደ 20ሺ በላይ የሚጠጉ ዜጎች በኢትዮጵያ በመካሄድ ላይ ካለው አመፅ ጋር ተያይዞ የታሰሩ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 9ሺየሚጠጉ እስረኞ ባለፈው ሳምንት መለቀቃቸው የታወቀ ሲሆን ይህንንም በኢትዮጵያ መንግስት ቴሌቪዥን “አይደገመንም”የሚል ቲሸርት ለብሰው የሚያሳይ ዘገባ መስራቱ ይታወሳል።
በአሜሪካን የተባበሩት መንግስት አምባሳደር ሰማንታ ፓወር የእስረኞችን መፈታት ተከትሎ መልካም ጅምር ሲሉገልፀውታል።
የአባይ ሚዲያ ዘጋቢ እንዳረጋገጠው የአሜሪካን ልኡክ ጠንከር ያለ ግፊት ማድረጋቸውን ተከትሎ ጉዳዩ በአዲሱ የአሜሪካንምክርቤት በኢትዮጵያ መንግስት ላይ እርዳታና ማእቀብ መጣልን የሚጨምር ውይይት ሊደረግ እንደሚችል አክለውአስጠንቅቀዋል።
ይህ በንዲህ እንዳለ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ከእስር የአይደገመንም ቲሸርት ለብሰው ከተለቀቁ ዜጎች መካከልባደረገው ቃለምልልስ ይህ በግዳጅ እንዲለብሱ የተደረገው “አይደገመንም” ቲሸርት እስረኞችን እንደማይገልፅና እንደማይወክልትግሉን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በቃለምልልሱ አረጋግጠዋል።
ይሁን እንጂ ይህ ዘገባ ከተሰራ በሆላ እንደገና በኮማንድ ፖስት በሚል በሚጠራው ወታደራዊ የማዘዣ መዋቅር አማካኝነት በርካታ ዜጎች ሰሞኑን እየታሰሩና ግድያም እየተፈጸመ መሆኑን ኣባይ ሚዲያ በዛሬው ዘገባው ኣስታውቆል::
እንደሚታወቀው የአሜሪካን መንግስት ወደ ኢትዮጵያ በሚሄዱ ዜጎቹ ላይ ተደጋጋሚ የጉዞ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ የሚታወቅሲሆን አሁንም ማስጠንቀቂያው በተግባር ላይ እንደዋለ ይገኛል።
No comments:
Post a Comment