Wednesday, December 14, 2016

በሰሜን ጎንደር ቋራ ወረዳ በታጣቂ የነፃነት ኃይሎች እና በወያኔ ወታደራዊ ኃይሎች ተደረገዉ ፍልሚያና ትንንቅ በነፃነት ኃይሎች የበላይነት ተጠናቀቀ

አባይ ሚዲያ
ብርሃኑ አየለBilderesultat for የመከላከያ ሰራዊት አባላት
በሰሜን ጎንደር ቋራ ወረዳ  የታጠቁ የነፃነት ኃይሎች ከወያኔ ጠመንጃ አንጋች ኃይላት ጋር ቅዳሜ ከፍተኛ ጦርነት ማካሄዱቸው ታውቋል። በዚህ የጦፈ ጦርነትም የነፃነት ኃይሎች ድል የተቀዳጁ መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን በተለያየ ጥቅማ ጥቅም ተደልለውና ተታለው ወደ ጦርነት የተሰለፉ ታጣቂዎች መሳሪያቸውንና ትጥቃቸውን እየፈቱ ከነፃነት ናፋቂ ኃይሎች መሰለፋቸው ታውቋል።
 በርካቶች ታጣቂ ኃይሎች ይቀላቀሉ እንጂ በውጊያው ወቅት የነፃነት ኃይሎችን እንደብረት የጠነከረ ጡንቻ መቋቋም ተስኗቸው የተማረኩ እንዳሉና ሌሎቹም ውጊያዎቹን ሸሽተው እንደፈረጠጡ ከስፍራው የደረሰው መረጃ ያስረዳል። ይህም የነፃነት ኃይሎች የድል ትሩፋት  የወያኔን መከላከያ ሠራዊት እና ሌሎችንም በሥርዓቱ ዉስጥ ያሉ ባለሥልጣናትን ከማደናገጡም በላይ እርስ በእርሳቸውም  እንዳይተማመኑ እያደረገና እና እየተወነጃጀሉም  እንደሆነ የመረጃ ምንጫችን ያመላክታል። ከዚህ በተጨማሪም በነፃነት ኃይሎች እና በወያኔ ታጣቂ ኃይሎች መካከል በተደረገዉ ዉጊያ ብዛት ያላቸው የሥርዓቱ ታጣቂዎች ሙትና ቁስለኛ የሆኑ ሲሆን የተገደሉት እና የቆሰሉት የሥርዓቱ ታጣቂዎች በየጫካዉ ያለቀባሪ መቅረታቸዉን መረጃዉ ጨምሮ አስረድቷል።

በእዚህም የነፃነት ኃይሎች ድል የተደሰተዉ  የአካባቢዉ ሕዝብ የጀግና አቀባበል ለነፃነት ኃይሎች እንደአደረጉላቸዉ ለዝግጅት ክፍላችን የደረሰዉ  መረጃ ያመለክታል ሲል በዛሬዉ የሬዲዮ ዜናዉ አስደምጧል።

No comments:

Post a Comment