Thursday, December 15, 2016

* የዶክተር መራራ ጉዲና እስር እያነጋገረ ነው።



Bilderesultat for መራራ ጉዲናከአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጋር በአንድ አዳራሽ መታየታቸው ለእስር ዳርጓቸዋል።
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር የሆኑት ዶር መረራ ጉዲና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መመሪያ አንድ ጥሰዋል ተብለው ለእስር መዳረግ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። ዶር መረራ ጉዲና ወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በአውሮፓ ህብረት ግብዣ መሰረት ምስክርነታቸውን የሰጡ ሲሆን በስብሰባ አዳራሹ ከተገኙት መካከል የአርበኞች ግንቦት 7 መሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እንዲሁም በሪዮ ኦሎምፒክ የብር ሜዳለያ አሸነፊ የሆነውና እጁን ግንባሩ ላይ በማጣመር የኢትዮጵያ መንግስት በዜጎቹ ላይ እየወሰደ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በአለም መደረክ የተቃወመው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ የተገኙ ሲሆን ዶክተር መራራ ጉዲናን ለእስር የዳረጋቸው የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአዳራሽ መገኘት ነው።
የዶክተር መረራን እስር ተከትሎ መንግስት በሰጠው መግለጫ ዶክተር መረራ የታሰሩት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈፀም የወጣውን መመሪያ ቁጥር አንድ በመታሳቸው ነው ያሉ ሲሆን የኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት መድረክ በበኩሉ ዶክተር መራረ የጋበዘው የአውሮፓ ህብረት ነው ስለሲህ ሊቀመጥበት የሚችለውን ቦታ ስብሰባውን ያዘጋጀው አካል ነው እንጂ ዶክተር መረራ እይደሉም የሚመርጡት እስራታቸው ምክንያታዊ አይደለም ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት ዶር መረራ ጉዲና በማእከላዊ ወንጀል ምርመራ የሚገኙ ሲሆን አራዳ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቀርበው የጸረ ሽብር አዋጁ በሚፈቅደው መሰረት የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል። ዶክተር መራራ እስከአሁን ድረስ አንድ ጌዜ ብቻ ጠበቃ ያገኙ ሲሆን ፖሊስ ከጎናቸው ቆሞ የሚያወሩትን ሲሰማ ስለነበረ ለማውራት እንደተቸገሩ የዶክተር መራራ ጉዲና ጠበቃ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

No comments:

Post a Comment