አባይ ሚዲያ ዜና
አክሊሉ ታደሰ
በኢትዮጵያና በአውሮፓ ህብረት ምካከል ያለው መልካም ትብብር እንዲቀጥል የፕ/ር መራራ ጉዲና ሁኔታና ስለ ተከሰሱበት ጉዳይ ግልፅ ማብራርያ እንዲሰጣቸው የህብረቱ ም/ቤት ፕሬዘዳንት ለኢትዮጵያው ፕሬዘዳንት በፃፉት ደብዳቤ አሳወቁ፡፡
የአውሮፓ ህብረት ም/ቤት ፕሬዘዳንት የሆኑት ሚስተር ማርቲን ሹልስ ለኢትዮጵያው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ በጻፉት ደብዳቤ ዶ/ር መራራ ጉዲና ባለፈው ወር ብራስልስ እንደነበሩና በቆዩበትም ጥቂት ቀናት ከህብረቱ የፓርላማ አባላት ጋር የተገናኙ መሆኑንና ወደ ሀገር ቤት ሲመለሱ ለእስር መዳረጋቸውን የጠቀሱ ሲሆን የታሰሩበትም ምክንያት ከአሸባሪነት ከተፈረጁ ሰዎች ጋር መሆኑንም መስማታቸውንም ገልጸዋል፡፡ ነገር ግን ሚ/ር ማርቲን የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ከውጭ መንግስታትና የተቃዋሚ ቡድኖች ተወካዮች የተለያዩ ድምጾች የሚሰሙበት የዲሞክራሲ ቤት ነው ሲሉም ይገልጻሉ፡፡
ሚ/ር ማርቲን ሹልስ ለዶ/ር ሙላት በጻፉት ደብዳቤ የዶ/ር ምራራ ጉዲና መታሰር ከአውሮፓ ህብረት ጋር የተያያዘ መሆኑ ያሳዘናቸው መሆኑን ጠቅሰው በመጨረሻም ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ያላት መልካም ትብብር እንዲቀጥል የዶ/ር መራራ ጉዲና ሁኔታና ስለ ተከሰሱበት ክስ ጉዳይ ግልፅ ማብራርያ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡
No comments:
Post a Comment