Friday, December 23, 2016

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ



በሰሜን ጎንደር የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄን ተከትሎ እስራትና ግድያው ተጠናክሮ እንደቀጠለ ሲሆን የማንነት ጥያቄ አቅራቢውም ህዝብ ትጥቁን እያጠባበቀ ወደ ጫካ እየከተተ መሆኑ ታውቋል ፡፡No automatic alt text available.
ባለፈው ታህሳስ 9 ቀን 2009 ዓ.ም. የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ አባላት የሆኑት አቶ ዘውዱ ገ/እግዚያብሄርና አቶ ሙላው ከበደ በመተማ ወረዳ ልዩ ስሙ ስናር በተባለው አካባቢ በወያኔ መከላከያ ሰራዊት ተከበው የነበረ ሲሆን ከዚህ ከበባ ለመውጣት ከስርዓቱ ታጣቂ ሃይሎች ጋር ውጊያ በማድረግ አቶ ዘውዱ ገ/እግዚያብሄር 5 የወያኔ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ገድሎ እርሱም በክብር ተሰውቷል ፡፡ ወያኔም እነዚህን ሁለት ሰዎች አስከሬን አይቀበርም ብሎ በጠራራ ፀሃይ መሬት ላይ አስጥቶ እንዲውሉ ቢያደርግም የአካባቢው ህዝብ ባደረገው ጫና ምክንያት ህዝቡ ቃፍታ ወስዶ ቀብሯቸዋል ፡፡
ህዝቡም እነሱን ከቀበረ በኋላ ከፍተኛ ተቃውሞን ያሰማ ሲሆን በአማራው ክልል በተለይ የወልቃይት ህዝብ ከፍተኛ ተቃውሞ እያሰማና አብዛኛው ህዝብ ደግሞ ወደጫካ እየወጣ እንደሆነ ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡ 
ከዚህም ጋር ተያይዞ በአካባቢው ብዛት ያላቸው ታጣቂዎች ማይሰገን ከተባለ ቦታ ከህዝብ ጎን በመቆም አንዳነድ እንቅስቃሴዎችን እያደረጉ መሆኑ የታወቀ ሲሆን አንድ የወያኔ ሰላይ የሆነና በኢንቨስተር ስም በአካባቢው የሚኖር በርሄ ጎሼ የተባለ የአገዛዙ ሰላይ ልጁና ወኪሉ በታጠቁ ሃይሎች ተጠልፈው የተወሰዱ መሆኑን አስታውቀው መረጃው ህዝብን እምባ እናብሳለን በሚል ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆናቸውንም ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀዋል፡፡ 
ይህንን የህዝቡንና የታጣቂዎችን እንቅስቃሴ ተከትሎ ወያኔ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ የገባ ከመሆኑም ባሻገር አብደራፊ ዳንሻና ሁመራ አካባቢ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት እያሰፈረ እንዲሁም በአካባቢው ያጠራጠራቸውን ሰዎች ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል ብዛት ያላቸው ሰዎችን በየጦር ካምፑ አገዛዙ በግፍ እያሰረ እየደበደበ መሆኑ ታውቋል፡፡

No comments:

Post a Comment