Monday, December 26, 2016

አዲስ አበባ በእሳት አደጋ ታመሰች 8 መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል በሚሊዮኖች ብር ንብረት በ24 ሰአታት ተቃጥሏል

አባይ ሚዲያ ዜና
ዘርይሁን ሹመቴ
አዲስ አበባ ከወትሮ ለየት ባለ ሁኔታ በበተለያዩ ስፍራዎች 24ሰአት በልሞላ ሰአት ውስጥ አስተናግዳለች። የእሳት አደጋው በንብረት ላይ ከፍተኛ ጎዳት አድርሷል። ከመረጃዎች መረዳት እንደሚቻለው በአብዛኛው የንግድ ሱቆች በእሳት አደጋው ወድመዋል።
የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ መከላከያና መቆጣጠሪያ ባለስልጣን የኮምንኬሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ ንጋቱ ማሞ እንደገለጹት አደጋው የተከሰተው በዋናው ፖስታ ቤት በአራዳና በጉለሊ ክፍለ ከተማ እንደሆነ መረዳት ተችሏል።
የዋናው ፖስታ ቤት ንብረት የሆኑት ሱቆች በእሳት በመንደዳቸው በግምት ከ500 ሺህ ብር በላይ ንብረት ጠፍቷል። ይህም በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከሌሊቱ ሰአት እንደሆነ ከኮምንኬሽኑ ገለጻ መረዳት ተችሏል።

በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ በተለምዶ ሃብተ ጊዮርጊስ ድልድይ አከባቢ በተከሰተው የእሳት አደጋ መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለው ሙሉ በሙሉ ወድመዋል።
በጉለሌ ክፍለ ከተማ ከመድሃኒአለም ቤተክርስትያን አጥር ጥግ የሚገኙ የንግድ ሱቆች ላይ በደረሰው ቃጠሎም ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰ ታውቋል።
በአጠቃላይ በ24 ሰአታት ውስጥ በመዲናችን የተለያዩ ቦታዎች በተከሰቱት የእሳት አደጋዎች በግምት ከሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሞል። በህይወት ላይ የደረሰ አደጋ እንዳልተከሰተ አቶ ንጋቱ ሞሞ ገልጸዋል። የኮምንኬሽን ባለሙያው ህዝቡ የእሳት አደጋ መንስኤ የሚሆኑ ነገሮችን መጠንቀቅ እንዳለበትም አሳስበዋል።

No comments:

Post a Comment