አባይ ሚዲያ ዜና
ናትናኤል ኃይለማርያም
በኦጋዴን ኢትዮጵያዉያን ሴቶችና ሕጻናቶች በሚሰቀጥጥና በቃላት መግልጽ ከሚቻለዉ በላይ እየተሰቃዩ መሆናቸዉን እና በ 10 ሺዎች የሚቆጠሩት ሴቶች ደሞ በኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮችና ፖሊሶችን ጨምሮ በማሰቃያ ካምፕ ዉስጥ በማጎር በሴቶቹ ላይ የወሲብ ጥቃት ግርፋት እና ስብዕናቸዉን ዝቅ በማድረግ እያሰቃዩቸዉ መሆኑን በኬንያ በሚገኘዉ ዱብ የስደተኞች ካምፕ ድረስ በመሔድ በቦታዉ ላይ ያገኛቸዉን የስቃዩ ሰለባ የሆኑትን ግለሰቦች በአካል አነጋግሮ የተመለሰዉ ጋዜጠኛ ድርጊቱ መፈፀሙን ማረጋገጡን የኦጋዴን የወጣቶች አባል በጄኔቭ በተደረገዉ የ2016 ፎረም ስብሰባ ላይ ለተሰብሳቢዎቹ ባቀረቡት ሪፖርት አስረድተዋል።
በኦጋዴን የሚገኙ ሴቶችና ሕፃናቶች በደረሰባቸዉ ሰቆቃ ምክንያት አካለ ስንኩል የሆኑም እንዳሉ የገለጹት የኦጋዴን አባሏ እነዚሁ ተሰቃዮች አገር ሸሽተዉ ከሔዱም በኋላም የኢትዮጵያ ወታደሮች ቦርደር አቋርጠዉ ጥቃት እንደሚፍፀምባቸዉም ገልፀዋል። በመሆኑም የአለም አቀፉ ሕብረተሰብም ይህንን ሰቆቃ ዝም ብሎ ማለፍ ሰለሌበት ይኽንን መከራ ሚደርስባቸዉን የኦጋዴን ሴቶችና ሕፃናቶች እንዲታደጋቸዉና ጉዳዩንም በመከታተል ድርጊቱን በሚፈፅመዉ የኢትዮጵያ ወታደሮችንና አዲስ ከተቋቋመዉ እና ከወታደሩ ጋር በትብብር የሚሰራዉን የክልሉን ፖሊስ ጨምሮ ምርመራ እንዲካሔድና ፍርድ እንዲሰጥ በማለት የተጠየቀ ሲሆን በማያያዝም የአለም አቀፉ ሕብረተሰብ የኦጋዴን ሴቶች እና ሕፃናት ላይ እየደረሰ ያለዉን ሰቆቃ ትኩረት የሰጠዉ አይመስልም ነገር ግን የኦጋዴን ሴቶችና ሕፃናቶች ከሌላዉ የአለም አቀፉ ሕብረተሰብ የተለዩ ባለመሆናቸዉ ተመሳሳዩን እንክብካቤ ሊያገኙ ይገባልም በማለት መድረኩ የተፈቀደላቸዉ የኦጋዴን ወጣት ግሩፕ አካል የሆኑት እኚሁ ሴት ገልፀዋል።
ንግግራቸዉን በወያኔዉ አፈቀላጤ ለማደናቀፍ ሙከራ የተደረገባቸዉ እኚሁ የኦጋዴን ተናጋሪም በማያያዝ ኦጋዴን አካባቢ የሚኖሩ ሕጻናት በምግብ እጥረትና አካባቢዉ የጦር ቀጠና መሆኑን አያይዞ እናቶችና ልጆች በከፍተኛ ስጋት ዉስጥ እና ጦርነቱን ተከትሎ በሚደርስባቸዉ የተለያዩ ችግሮች ሰላባ ሲሆኑ በመንግስት በኩልም ከቦታ ወደ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ በማገዱ ምክንያት ልጆቻቸዉ የጥይት ሰለባ እንድሚሆኑም ጭምር ገልፀዋል። ተናጋሪዋ በመቀጠልም የአለም አቀፉን ማሕበረሰብ አፅንዖት በመስጠት በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ መንገስት ለሚሰቃዩት ወገኖቻችን በሚቻለዉ ሁሉ ከለላ እንዲያደረግላቸዉ እና አስገድደዉ የደፈሩትን ወታደሮችንም አስፈላጊዉን ምርመራ በማካሔድ ለፍርድ እንዲያቀርብና ተጎጂዎችንም ሰላም ሚያገኙበትን መፍትሔ እንዲያፈላልግ ሲሉ አጥብቀው ጠይቀዋል።
የወያኔዉ አፈቀላጤ የኦጋዴን ወጣት አባል የሆኑትን ንግግር ለማቋረጥ ያደረገዉ ጥረት ሳይሳካለት መቅረቱም ተዘግቧል። –
No comments:
Post a Comment