Monday, December 19, 2016

በካንሳስ ሲቲ ሙሱሪና አካባቢው የአርበኞች ግንቦት 7 በድምቀት ተከናውኗል

ag7-logo-150x150
በካንሳስ ሲቲ ሙሱሪና አካባቢው የሚገኙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የአርበኞች ግንቦት 7 እርዳታ ማስተባበር ዝግጅት በመሚገባና ውጤታማ በሆነ መንገድ እንደተከናወነ የአካባቢው የአባይ ሚዲያ የዜና ወኪል ዘግቧል። በዝግጅቱ ርእዮት ዓለሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተሟጋችና የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር አባል በዝግጅቱ ተግኝታ ገለጻ አድርጋለች።በህዝባዊ ውይይቱ ላይ ለተነሱ ጥያቄዎችም ተገቢ ምላሽ ሰጥታለች።አርቲስት ሻምበል በላይነህ በሙዚቃ ታጅቦ ለዝግጀቱ ድምቀትን ሰጥቶት እንደነበረም የአባይ ሚዲያ የዜና ወኪል ጨምሮ ገልጿል።በእለቱ የነበረው የአየር ንብረት ችግር ሳይበግራቸው በቦታው በመገኘት የተካፈሉትን በካንሳስ ሲቲ ሙሱሪና አካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ የአካባቢው የአርበኞች ግንቦት 7 ቻፕተር ምስጋናውን አቅርቧል።

No comments:

Post a Comment