በአሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ምክትል ቃል አቀባይ የሆኑት ማርክ ቶነር ፕሮፌሰር መራራ ጉዲናን በተመለከተ ጥያቄ ቀርቦላቸው ማብራሪያ ሰጥተውበታል። ከአለም አገራት ውስጥ የኢትዮጵያ መንግስት ብቻ በሽብርተኛነት ከፈረጀው የግንቦት 7 ለፍትህና ዲሞክራሲ ግንባርና ከሊቀመንበሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጋር ግንኙነት አድርገዋል ተብለው ፕሮፌሰር መራራ ጉዲና በእስር ላይ ይገኛሉ።
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር እና የመድረክ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር መረራ ጉዲና እስራት እንዳሳሰበው የሚገልጽ የአቋም መግለጫ የአሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በቃል አቀባዩ በኩል አውጥቷል። በአሜሪካ መንግስት የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ምክትል ቃል አቀባይ የሆኑት ማርክ ቶነር እንዳሉት የኢትዮጵያ መንግስት ዶ/ር መረራ ጉዲና ማሰሩን የአሜሪካ መንግስት መንግስት እያሳሰበው መምጣቱን እና ሁኔታዎችንም በቅርበት መንግስታቸው እየተከታተለ መሆኑን ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ዶ/ር መረራ ጉዲናን ማሰሩ የሚያሳየው ነገር ቢኖር ኢትዮጵያ ውስጥ የነጻነት ድምጾችን ለማፈን በዜጎች ላይ የሚጣሉት ገደቦች እየተጠናከሩ መምጣታቸውን ማሳያ ነው። በአገሪቱ የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሕገ መንግስቱ የተረጋገጡትን ሕጋዊ መብቶችን ለማፈኛነት መንግስት እየተጠቀመበት መሆኑን ያመላክታል። የኢትዮጵያ መንግስት ለተፈጠሩት አገራዊ ችግሮች ፖለቲካዊ ለውጦችን አመጣለሁ ካለው ውሳኔ ጋር ተጻራሪ የሆነ ድርጊት መሆኑን እና ሁኔታዎች በቅርበት መንግስታቸው እንደሚከታተለው ቃል አቀባዩ ማርክ ቶነር አሳስበዋል።
በአማራና በኦሮምያ የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ እምቢተኛነት ተከትሎ የወያኔ አስተዳደር የ6 ወር የአስቸኩዋይ ጊዜ መደንገጉ ይታወሳል። መንግስት ባወጣው መረጃ መሰረት ከ16000በላይ የሆኑ ሰዎችን ባዋቀረው ኮማንድ ፖስት ማሰሩን መረዳት ተችሏል። አምባገነናዊ የወያኔን አገዛዝ በመቃወም በመላ ሃገሪቱ በተደረጉ ሰላማዊ የተቋውሞ እንቅስቃሴዎች ከ1000 በላይ ንጹሃን ሰዎች በመንግስት ታጣቂዎች ተገድለዋል።
No comments:
Post a Comment