Thursday, December 29, 2016

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በሽብርተኝነት ወንጀል ሊከሰሱ ነው። ታኅሣሥ ፳ (ሃያ)ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-

Bilderesultat for መራራ ጉዲናባለፈው ወር በብራሰልስ አውሮፓ ህብረት ፓርላማ ለስብሰባ መጥተው ሲመለሱ ለእስር የተዳረጉት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በሽብርተኝነት ሊከሰሱ መሆናቸውን  ምንጮች ገልጸዋል።
ፕሮፌሰር መረራ  ከሁለት ሳምንታት በፊት ፍርድ ቤት ቀርበው የ28 ቀን ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ወደ ማእከላዊ የተመለሱ ሲሆን፤ መርማሪዎች የኢሜይልና የፌስቡክ አካውንታቸውን አስገድደው በመውሰድ  በሽብርተኝነት ሊያስከሣቸው ይችላሉ ብለው የሚያሥቧቸውን መረጃዎች እያሰባሰቡ ይገኛሉ። እንደ ኢሳት የውስጥ ምንጮች ዘገባ፤ የፕሮፌሰር መረራን ጉዳይ በዋነኝነት የያዘው  የፌዴራል ፖሊስ አባል የሆነው የሽብር ምርመራ ዳይሬክተሩ ኮማንደ ተክላይ ነው።
የፕሮፌሰር መረራ ምክትል የሆኑት የኦሮሞ ፌዴራሊስ ኮንግረስ ምክትል ሰብሳቢ አቶ በቀለ ገርባ በተመሣሳይ ወደ አሜሪካ ለስብሰባ አቅንተው ሲመለሱ በሽብርተኝነት ተከሰው መታሰራቸው ይታወቃል።
በፕሮፌሰር መረራ እስር ጉዳይ የአውሮፓ ህብረት ፓርላማ ፕሬዚዳንት በቀጥታ ለጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ደብዳቤ ቢጽፉም፤ አገዛዙ  ይባስ ብሎ ፕሮፌሰሩን በሽብርተኝነት ለመክሰስ መዘጋጀቱ ፤በህብረቱና በህወኃት- ኢህአዴግ መንግስት መካከል ያለውንና ቀዝቀዝ እያለ የመጣውን ግንኙነት ይበልጥ ያሻክረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

No comments:

Post a Comment