አባይ ሚዲያ ዜና
(ዘርይሁን ሹመቴ)
የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች የኢትዮጵያ መንግስት ከጥቅምት 2014 እኢአ ጀምሮ በእስር ላይ ያቆየውን የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ወቅታዊ ሁኔታና የሚገኝበትን ቦታ እንዲያስታውቅ ከፍተኛ ጫና እያደረጉ ነው። የኒዮርክ ታይምስ ጋዜጣ የታሰረው ተወዳጁ ጋዜጤኛ ተመስገን የት ነው በማለት ያጠናከረውን ሪፖርት ለአንባቢያኑ አቅርቧል። ይህ ጋዜጣ አሶሼየትድ ፕሬስን ዋቢ በማድረግ የኢትዮጵያ መንግስት የጋዜጠኛነት እና የመናገር መብቱን በመንፈግ ለእስር የዳረገውን ተመስገንን የሚገኝበትን ወቅታዊ ቦታ ማሳወቅ እንዳልቻለ የኢትዮጰያ ፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የሆኑትን አቶ ግዛቸው መንግስቴ ለአሶሺየትድ ፕሬስ የሰጡትን መልስ በማስፈር ዘገባውን አጠናቅሯል።
የሰብአዊ መብት ተሟጋች ህብረቱ ከሁለት ኣመት እስር በሁዋላ ጋዜጠኛውን መሰወርና ስላለበት ሁኔታ ለቤተሰቦቹ ለመግለጽ ፈቃደኛ አለመሆን ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው ነው በማለት አክሏል። የኒዮርክ ታይምስ በተጨማሪም ኢትዮጵያ ውስጥ የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ መንግስት የአስቸኩዋይ ጌዜ አዋጅ ማውጣቱንና ይህንንም እንደ ምክንያት አድርጎ አገዛዙ በጋዜጠኞች ላይ የሚያደርገው እስራት እንደጨመረ ጠቅሷል።
No comments:
Post a Comment