Monday, December 12, 2016

በጎንደር አዘዞ የሚገኘው የ24ኛ ክ/ጦር ሆስፒታል በቁስለኛ የወያኔ ወታደሮች ተጨናንቋል ተባለ

Bilderesultat for ቁስለኛ ወታደርተጨናንቋል ተባለ ካለፋት 2 ሳምንታት በፊት ጀምሮ ሞልቶ የሚገኘው ይህው ሆስፒታል በተጨማሪም በያዝነው ሳምንት በሁለት ኦራል የገባው ቁስለኛ ከሰሜን ጎንደር የጦር ግምባሮች የተሰበሰበ እና በእየ አካባቢው ካሉ ጤና ጣቢያወች አገልግሎት ባለማግኘቱ እየተሰቃየ ይገኛል ተብላል። በአርበኞች ግንቦት 7 ና በአማራ ገበሬ አርበኞች አይቀጡ ቅጣትን እየቀመሰ ሙትና ቁስለኛ የሆነው ወታደር አስከሬናቸው ወደ አምባ ጊዩርጊስ እንደተወሰደም ታውቋል ። ከባድ ቁስለኞች ግን ጨርሱን እያሉ ህክምና ባልተገኘበት እንደሚሰቃዩ ታውቃላ።
በተያያዘ ዜና በሰሜን ጎንደር ጦርነቱ መቀጠሉ ይነገራል፥ የአርበኞች ግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ሰራዊት በኢትዩጲያ ምድር ስልጠና መጀመሩን ማስታወቁ ይታወሳል ። የወያኔን አገዛዝ ከድተው ከብዙ መሳሪያ ጋር አግ7 የሚቀላቀሉ ወታደሮች የጨመሩ እንደሆነ ተንግራል ። 46 ወታደሮች 18 የተለያዩ መሳሪያወችን እንደያዙ መቀላቀላቸው ባሳለፍነው ሳምንት ነበር የተሳማው።
ድል ለኢትዩጲያ ህዝብ !
ድል ለታጋይ አርበኞቻችን !

No comments:

Post a Comment