Sunday, December 25, 2016

የአፈናውና ሰቆቃው መጠናከር ለነጻነታችን ከምናደርገው ትግል አይገታንም።

Image may contain: one or more people, people standing, child and outdoorህወሃት ህዝባችን ለነጸነቱ የሚያካሂደውን ትግል ለመቀልበስ የፈለገውን ያህል ጉልበት ለመጠቀም ቢፍጨረጨር ፤ እስር ግድያና የማሳደድ ተግባሩን አጠናክሮ ቢቀጥል ከህዝባችን ልብ የበለጠ እየራቀ፤ የጥላቻና የበቀል እርምጃ የሚቀሰቅስ ወኔ ለምናካሄደው ትግል ይፈጥር እንደሆነ እንጂ ከጀመርነው የነጻነት ትግል ወደ ኋላ እንደማይገታን አርበኞች ግንቦት 7 በጽናት ያምናል።
ፍትህ እኩልነትና ነጻነት የሰፈነበት አገር ባለቤት ለመሆን የጀመርነው ትግል የፈለገውን ዋጋ ቢያስከፍለንም በድል ይጠናቀቃል። ለዕለት ጉርሳቸው ሲሉ በውትድርና ተቀጥረው ለህወሃት የሥልጣን ዕድሜ ማራዘሚያ ውድ ህይወታቸውን እየገበሩ ያሉ ምስኪን ወገኖቻችን እየተካሄደ ያለው ትግል ለነርሱም ነጻነት መሆኑን ተረድተው የያዙትን መሣሪያ የደሃውን ልጅ እየገደሉና እያስገደሉ የማይጠረቃ የሃብት ዘረፋ ጥማታቸውን ለመወጣት በሚያዘምቷቸው አለቆቻቸው ላይ እንዲያዞሩና ትግሉንም እንዲቀላቀሉ ንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪውን ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

No comments:

Post a Comment