Wednesday, December 21, 2016

የሳዑዲ ባለ ሥልጣን ለኢትዮጵያ የአባይ ግድብ አገራቸው ምንም የገንዘብ ድጋፍ አታደርግም አሉ፤


በመሃከለኛው ምስራቅ የእቅድና ህግ ጥናት ምርምር ሃላፊ አንዋር እሽኪ፣ በመገናኛ ምንጮች ሳውዲ አርቢያ ለኢትዮጵያ የአባይ ግድብ ግንባታ ብድር ለመስጠት አስባ ነበር አስባ ነበር ተብሎ መመዝገቡ ትክክለኛ አይደለም ሲሉ ዚናውን አስተባበሉ።

ጡረተኛው ጄነራል አሽኪ ለሚስር አል አረቢያ ዜና ሲገልፁ የሳዑዲ አረቢያ ንጉሣዊ አካል አማካሪና የሳዑዲ የግንባታ ገንዘብ ክፍል ቦርድ ሰብሳቢ አህመድ አል ካታቢ፣ ስለ ሁለቱ አገሮች የጋራ ግንኙነት እና የምጣኔ ሃብት እቅዶችን ሊነጋገሩ እንደነበር ገልፅው፣ የአል ካታቢ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ያረጉት ጉብኝት፣ ግብፅ የሳዑዲ መንግሥት የሚቃውመውን በፕሬዝደንት ባሺር አል አሳድ ለሚመራው የሲርያ መንግሥት የሰጠችውን ድጋፍ ለመበቀል ነው ተብሎ የተዘገበው ሃሰት ዜና ነው በማለት አስተባበለውታል።

በኢትዮጵያ ገዢ ቁጥጥር ስር የሚገኘው ቴሌቪዥን የሳዑዲው አማካሪ ከጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደስ አልኝ ጋር አርብ መገናኘታቸውን አስታውቆ በግንኙንታቸውም ወቅት ጠ/ም ሃይለማርያም ደስ አልኝ ሳዑዲዎች ለግድቡ ወጪ አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ እንደጠየቁ ዘግብዋል። በመጨመርም ኢትዮጵያ ከሳዑዲ አረቢያ ጋር በኀይል መስክ፣ በግንባታ፣ በኤሌክትሪሲቲ፣ በግብርና እና በቱሪዝም ለመተባበር ፍላጎት እንዳላት መናገራቸውን ቴሌቪዥኑ አስታውቅዋል።
ጄነራል አሽኪ – ሳዑዲ አረቢያ ግብፅን የሚጎዳ ምንም ነገር እንደማታደርግ አበክረው ተናግረዋል። ጨምረውም የሪያድ መንግሥት ከአስር ዓመት በፊት በርካታ ለመዋዕለ ንዋይ ግንባታ ገንዘብ ለማቅርብ የተስማማ እንደነበር አስታውስው፣ ነገር ግን፣ ሁኔታዎች ተቀይረዋል፣ ቅያሬዎቹ ባለ ሃብቶችን ጉዳት ላይ የሚጥሉ ናቸው ብለዋል።

No comments:

Post a Comment