Tuesday, December 27, 2016

የአስቸኳይ ጊዜ የዉጭ ምንዛሬ ማዕቀብ አዋጅ!

ውድ ኢትዮጵያዊያን፣
ሁላችንም በሚገባ እንደምናውቀው፤
  • ሀገራችን ኢትዮጵያ በሕወሓት መራሹ ዘረኛ የግፍ አገዛዝ ሥር ሆና ዜጎች እንደ እንስሳ እየተገደሉ ባሉበት በዚህ ፈታኝ ወቅት፣ አስከፊውን ስርዓት ከስሩ ነቅለን ሕዝባችንን እና ሀገራችንን ለመታደግ ዛሬ ነገ የማይባልበት አጣዳፊ ጊዜ ላይ የደረስን በመሆኑ፤
  • ጠላት ሌት ተቀን ሥልጣኑን ለማራዘም በሽዎች እያሰረ፣ እያሰቃየና እየገደለ ባለበት ወቅት፣ ዝም ብለን በመቀመጥ ወይንም ወያኔ በሚፈፅመው ግፍ በማዘን እና በመቆጨት ብቻ ተጠምደን እያንዳንዳችን የቻልነውን ያህል ጠጠር ከመወርወር ከተቆጠብን ፣ “ነገ ሀገር እና ሕዝብ የሚባል ይኖረናል ወይ?” ብለን የምንጠይቅበት ደረጃ ላይ የደረስን በመሆኑ፣
  • በሀገር ቤት ያሉ ወገኖቻችን የእለት ጉሮሯቸውን ዘግተው እየተራቡ እና እየተጠሙ በሕዝባዊ እምቢተኝነቱ ዐውድ የሚያደርጉትን የሞት ሽረት ትግል፤ በውጭ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ወገን የበኩሉን እርምጃ በመውሰድ  አጋርነቱን ማሳየቱ ትግሉን እንደሚያጎለብት የታመነበት በመሆኑ፣
  • ሀገራችን ኢትዮጵያን ለ25 ዓመታት በግፍ እንዲገዛ የኢኮኖሚው ጀርባ አጥንት ሆኖ ያገለገለው ከውጭ ሀገራት በተለያዬ መንገድ እና ምክንያት የሚገባው የውጭ ምንዛሬ በመሆኑና ከዚህም ዉስጥ በዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ለግንባታ፣ ለንግድ እና ለዘመዶቻቸዉ በባንክ በኩል የሚልኩት ህዋላ (remittance) ከፍተኛ ድርሻ ያለዉ በመሆኑ፣
  • በህዝባዊ እምቢተኝነቱ መቀጣጠል ምክንያት ወያኔ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ የገባ በመሆኑ እና ወደ ሀገር ቤት በተለያዬ ምክንያት በሚላከው የውጭ ምንዛሬ ላይ ውጤታማ ተአቅቦ ከተደረገ ሕወሓት መራሹን ዘረኛና ወንበዴያዊ አገዛዝ ውድቀት በእጅጉ የሚያፋጥነው በመሆኑ፣
እኛ ስማችን ከታች የተጠቀሰው የሲቪክ እና ፖለቲካ ድርጅቶች፤ ከላይ የተዘረዘሩቱን ወቅታዊ የሀገራችንን ሁኔታዎች ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እና  መነሻ በማድረግ፣ በውጭ የምንኖር፣ ፍትህ፣ እኩልነት እና  ነፃነት ወዳድ ኢትዮጵያዊያን፣ በሕወሓት መራሹ ዘረኛ አገዛዝ ላይ የዉጭ ምንዛሬ ማዕቀብ እንድናደርግ ወገናዊ ጥሪ እናቀርባለን።
  1. ከዚህ ‘ከዲሴምበር’ ወር ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ የኢኮኖሚያዊ ማዕቀብ አዋጅ በማወጅ፣ወደ ሃገር ቤት ለግንባታም ይሁን ለቤተሰብ ድጎማ ላከ የውጭ ምንዛሪ እን
  2. የሦስት ወሩ አስቸኳይ የኢኮኖሚ ማእቀብ የጊዜ ገደብ ከተጠናቀቀ በኋላ፤ የስርቱን የገንዘብ አቅም የበለጠ ማሽመደመድእንዲቻል፣ ቢያንስ ለስድስት ወር ያህል የሚላከው ገንዘብ በአንድ ሶስተኛ እንዲቀንስ ማድረግ። ይህም ማለት መቶ ዶላርየሚልክ ሰው ሰባ ዶላር እንዲልክ ወይም በአመት አምስት ጊዜ የሚልክ ሦስት ጊዜ ብቻ እንዲልክ ማድረግ፣
  3. የማእቀቡ ጥሪ በተላለፈበት የጊዜ ገደብ ውስጥ የግድ ለቤተሰብም ይሁን ለሌላ ጉዳይ ገንዘብ መላክ ካለበት፤ ገንዘቡ ለስርሊደርስ የማይችልበትን መንገድ በምንኖርበት ከተማ በማፈላለግ ገንዘቡን መላክ። ይህ ማለት ከባንኮች እና ገንዘብ አስተላላፊድርጅቶች እንዲሁም የወያኔ አባላት እና ደጋፊዎች ከሚቆጣሩት የአላላክ ዘዴ ውጭ የውጭ ምንዛሬውን መላክ።
ውድ ወገኖቻችን፣
ወያኔን የውጭ ምንዛሬ ማሳጣት በእጃችን ውስጥ ያለ የትግል መሳሪያ ስለሆነ ለተግባራዊ እርማጃ በመነሳት ኢትዮጵያዊ ግዴታችንን እንድንወጣ ለነፃነቱ እና ለእኩልነቱ ከፍተኛ ዋጋ እየከፈለ ባለው የኢትዮጵያ ህዝብ ስም እንጠይቃለን።

ድል ለሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ!!

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ /Ethiopian National Movement/
የአፋር ህዝብ ፓርቲ /Afar People’s Party/
የሲዳማ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /Sidama People’s Democratic Movement/
ኦሮሞ ዴሞክራቲክ ግንባር /Oromo Democratic Front/
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነት እና ዴሞክራዊ ንቅናቄ/Patriotic Ginbot 7 Movement for Unity and Democracy/
ዲሲ የጋራ ግብረ ሀይል/DC Area Ethiopian Community Joint Task Force/
የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ህብረት/United Ethiopian Muslims Peaceful Movement Support Group/
ኢትዮጵያ ህዝብ አብዮታዊ ፓርቲ /Ethiopian People’s Revolutionary Party/
የኢትዮጵያ ሽግግር ምክር ቤት/Ethiopian National Transitional Council/
ማህበረ ኢትዮጵያ/Mahbere Ethiopia/
ነጻነት ለኢትዮጵያ ሬዲዮ /Netsanet Radio/
የኢትዮጵያ ፖለቲከኛ እስረኞች አንድነት ኮሚቴ /Solidarity Committee for Ethiopian Political Prisoners/
የኢትዮጵያዊያን ህዝባዊ ፎረም በሲያትል /Ethiopian Public Forum in Seattle/
የኢትዮጵያዊያን ትብብር ህብረት በስዊድን /Alliance for Ethiopian Solidarity in Sweden/
ዴሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጭ በኖርወይ /Democratic Change in Ethiopia Support Organization in Norway/
የኮሎራዶ የኢትዮጵያዊያን ግብረ ሀይል /Colorado Ethiopian Task Force/
የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማህበር በደቡብ አፍሪካ /Ethiopian Community Association in South Africa/

ሀዋላን /remittance/ አስመልክቶ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ የሚከተሉትን ድረ ገፆች ይጎብኙ፦

No comments:

Post a Comment