Sunday, February 28, 2016

ከወልቃይት ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በወልቃይት ምድርና አካባቢው የሰፈነው ውጥረት አይሎ ሊፈነዳ ተቃርቧል፡፡(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)


ህወሓት ደጋፊዎቹን ከትግራይ በማጓጓዝ የወልቃይት ህዝብ የማንነቱን ጥያቄ ተቃውሞ አደባባይ የወጣ በማስመሰል የውሸት ሰላማዊ ሰልፎች እያደረገ ነው፡፡ ከሰሞኑ በጠገዴ ወረዳ ከተካሄደው የሀሰት የድጋፍ ሰልፍ በተጨማሪ ህወሓት 16 አውቶብስ ሙሉ ህዝብ ከመሃል ትግራይ አጓጉዞ በጠለምት፣ ደጀና፣ አደባይ እና በሌሎችም ቦታወች የወልቃይትን ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ የሚቃወሙ ሰልፎች አካሂዷል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የሽፍቶች ቡድን ህወሓት በወልቃይት ህዝብ ላይ የሚያደርገውን እስር፣ አፈና እና ማዋከብ በእጅጉ አበርትቶታል፡፡ የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄውን ህወሓት እመራበታለሁ በሚለው ህገ መንግስቱ መሰረት በሰላማዊ መንገድ ይፈቱልኛል ብሎ የመረጣቸው ወኪሎቹ እየታደኑ በመታሰር ላይ ናቸው፡፡ ህዝቡን ያስተባብራሉ ተብለው የተጠረጠሩ ቁጥር ስፍር የሌላቸው የወልቃይት ወጣቶችም በየቀኑ እየታፈኑ ደብዛቸው እየጠፋ ነው፡፡ በተለይም ደግሞ ህወሓት ህዝብ ከመሃል ትግራይ አጓጉዞ በወልቃይት ህዝብ ስም “እኛ ትግሬዎች ነን አማራዎች አይደለንም” በማሰኘቱ የወልቃይት ህዝብ ከመቸውም ጊዜ በላይ ውስጡ እንደሻከረ እየተነገረ ነው፡፡
በመሆኑም በወልቃይት ሰማይ ስር ሊፈነዳ ከጫፍ የደረሰ የአመፅና የቁጣ ድባብ እያንዣበበ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment