Wednesday, September 16, 2015

ኢሳት ዜና

Mola asgedomመስከረም ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢህአዴግ የቀድሞው የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( ትህዴን) ሊቀመንበር አቶ ሞላ አስጎደም ለ14 ዓመታት የነበሩበትን ድርጅት ከድተው ለኢህአዴግ ባለስልጣናት እጃውን መስጠታቸውን ተከትሎ ገዢው ፓርቲ እየሰራ ያለው የቅስቀሳ ስራ በህዝብ ዘንድ የተለያዩ አስተያየቶችን እያስተናገደ ነው። የመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ትህዴን የአርበኞች ግንቦት7 አንድ የጦር ክፍል እንደሆነ አድርገው ማቅረባቸው፣ እንዲሁም ውስጥ ለውስጥ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተያዘ፣ ድርጅቱ ፈረሰ እያሉ ማስራታቸው ብዥታ እንደፈጠረባቸው አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። መብራት በተደጋጋሚ መጥፋቱ ኢሳትን ለመከታታል እንዳላስቻለው የሚገልጹ አስተያየት ሰጪዎችም ፣ ትክክለኛውን መረጃ እንድናካፍላቸው ጥያቄ አቅርበዋል። አንድ አስተያየት ሰጪ የአቶ ሞላ በጊዜ መክዳት ለትግሉ የሚጠቅም መሆኑን ተናግረው ፣ አሁንም የማጥራቱ ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልጸዋል
። ሌላ አስተያየት ሰጪ ደግሞ ፣ የአገዛዙ ባለስልጣናት ከአቶ ሞላ ጋር ለአንድ አመት የቆዬ ስራ ሲሰሩ ቢቆዩ ኖሮ ፣ የአቶ ሞላ ሰራዊት ገሚሱ ሱዳን ገባ፣ ሌላው ኤርትራ ቀረ ብሎ መናገር አይችልም ነበር ገዢው ፓርቲ የደህንነት መስሪያ ቤቱን ብቃት ለማሳዬት የተጠቀመበትን የቅስቀሳ ስራ አጣጥለዋል። አቶ ሞላ በኢትዮጵያ የዲሞክራሲ፣ የመልካም አስተዳዳርና የኢኮኖሚ ጥያቄዎች በመመለሳቸው ትግሉን ለመተው እንደወሰኑ መናገራቸውን ያጣጠሉት ሌላ አስተያየት ሰጪ፣ ህዝቡ ሰውዬው ሳይሳካለት ሲቀር መመለሱን ህዝቡ ተረድቷል ብለዋል ሌላ አስተያየት ሰጪ ደግሞ " በትግል አለም ውስጥ መክዳት የተለመደ ነው" ካሉ በሁዋላ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ አሸናፊነታችን አይቀሬ መሆኑን መረዳት አለበት ብለዋል በማህበራዊ የመገናኛ መንገዶችም እንዲሁ የተለያዩ አስተያየቶች እየቀረቡ ነው። ፕ/ር ብርሃኑ ነጋን ወደ ኤርትራ ያስገባነው እኛ እና መንግስት ተመካክረን ነው ያሉት አቶ ሞላ፣ ፣ ፕ/ር ብርሃኑን የኤርትራ መንግስት ነው ያስመጣው፣ የኤርትራ መንግስት እሱን መሪ ሊያደርገው ይፈልጋል በማለት የሰጡት እርስ በርሱ የሚጣረስ መረጃ የብዙዎች አስተያየት ሰጪዎች የትኩረት ማእከል ሆኗል። አቻምየለህ ታምሩ የተባለ ጸሃፊ " ሞላ ለወያኔ አድሮ በወያኔ ህይወት ውስጥ ገብቶ በመንግስትነት ተሰይሞ በሚገኘው መደብ ውስጥ የተፈጠረውን መደናገጥና ቡድኑ የሚገኝበትን የጭንቅ ምጥ «በጋዜጣዊ መግለጫው» ለአለም በማጋለጡ ለነጻነት ትግሉ ያስገኘው ትርፍ አስመራ ተቀምጦ ከሚያስመዘግበው የጦር ሜዳ ውሎ ብዙ እጥፍ የላቀ ነው።" ሲል በአቶ ሞላ የተሰጠው መግለጫ የነጻነት ትግሉን የሚጠቅም እንጅ የሚጎዳ አይደለም ብሎአል፡፡ ሚከድ አስረስ የተባለ አስተያየት ሰጪ ደግሞ "የዛሬ አንድ አመት አካባቢ አንዳርጋቸውን ለማስገደል አንድ ሽጉጥ ወደ ኤርትራ ማዝለቅ ሰማይ እንደመቧጠጥ የሆነበት ቡድን ሞላ አስገዶም ከሚመራው ትልቅ ሃይል ጋር ሚስጥራዊ ግንኙነት ቢኖረው ኖሮ ይህን ያህል መልፋት ያስፈልገው ነበርን? " ሲል ጠይቋል። የገዢው ፓርቲ ደጋፊ ልሳን የሆነው ሪፖርተር ጋዜጣ የአቶ ሞላ ጋዜጣዊ መግለጫን የተለያዩ ጥአቄዎችን በማንሳት ይተቸዋል። "ኅብረቱ ከተመሠረተ ከጥቂት ቀናት በኋላ እነ ሞላ መልቀቃቸው ምን ያህል የታሰበበት ነው? ለምንስ ለቀቁ? " ሲል የሚጠይቀው ሪፖርተር ጋዜጣ፣ ለዚህ ጥያቄ አጥጋቢ ምላሽ የተሰጠበት አይመስልም" ብሎአል። " እነ ሞላ ከኤርትራ መንግሥትና ከሌሎች አማፂያን የሚያገኙትን መረጃ ለብሔራዊ የመረጃና ደኅንነት አገልግሎት በማቀበል አስፈላጊ ጥንቃቄ እንዲደረግ ማገዛቸውም ተጠቅሷል" የሚለው ጋዜጣው፣ " በመንግሥት በአሸባሪነት የተፈረጀው የግንቦት 7 ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ አሜሪካ ተቀምጠው አርበኞች ግንባርን ጨምሮ የተፈጸመውን ውህደት በሊቀመንበርነት መምራት የለባቸውም የሚል የጋራ አቋም እንዲይዙ በማድረግ፣ ዶ/ር ብርሃኑ ሳይወዱ ተገደው ወደ አስመራ እንዲገቡ መደረጉም እንደ ስኬት ተገልጿል፡፡ የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ አስመራ ለመሄድ መገደድ እንደ ስኬት የተወሰደበት ምክንያት ግን አልተገለጸም፡፡" ሲል ትችቱን ያቀርባል። ሪፖርትር አቶ ሞላ፣ ‹‹ከመንግሥት ጋር እየሠራን ስለነበር እኛ ነን ሆን ብለን ጥምረቱን የመሠረት ነው ብለው የተናገሩትን በሌላ መግለጫ ላይ "ጥምረቱን እንዲቀላቀሉ በኤርትራ መንግሥትና በግንቦት 7 ጥሪ እንደተደረገላቸው" መግለጻቸው እርስ በርሱ የተምታታ መሆኑን ጽፏል።

No comments:

Post a Comment