Friday, October 30, 2015

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ




በአርባ ምንጭ ከተማ አፈሳው እና እስሩ አሁንም ተባብሶ እንደቀጠለ ነው፤ እስካሁን በቁጥጥር ስር የዋሉት በርካታ ወጣቶች በዛሬው ዕለት ወደ አዲስ አበባ /ማዕከላዊ እስር ቤት/ ተወስደዋል፡፡
====================================================
የህወሓት ጆሮ ጠቢዎች ሙሉጌታ አባ፣ ፀጋዬ ገብረ ፃድቅ እና በኃይሉ ሲሳይ ፎቶግራፎች በማህበራዊ ሚዲያዎች በመሰራጨታቸው እና ወንጀላቸው ለህዝብ በመጋለጡ ምክንያት በአርባ ምንጭ ከተማ ዕረቡ ለሐሙስ አጥቢያ ከእኩለ ሌሊት በኋላ የተጀመረው ወጣቶችን በገፍ እያፈሱ የማሰሩ የህወሓት ደህንነቶች እና ፌደራል ፖሊሶች ተግባር አሁንም ተባብሶ በሰፊው ቀጥሏል፡፡ 
የአርባ ምንጭ ህዝብ እያፋፋመው ከሚገኘው የህዝባዊ እምቢተኝነት ትግል ባሻገር ዕልፍ አዕላፍ ወጣት ልጆቹ በረሃ በመውረድ አርበኞች ግንቦት 7ን ተቀላቅለው በታላቅ የአርበኝነት ተጋድሎ ላይ ይገኛሉ፡፡ ዕለት ከዕለትም ከከተማዋ ወደ በረሃ የሚወጣና ህወሓትን ለመውጋት ነፍጥ የሚያነሳ ወጣት ቁጥሩ በእጅጉ እየናረ መጥቷል፡፡ 
በመሆኑም የህወሓት ደህንነቶችና የታጠቁ ኃይሎች አርባ ምንጭ ውስጥ በህዝቡ መካከል ተሰግስገው የሚያደርጉት ጭንቅ ጥብብ ቢላቸው ወደ በረሃ የወጡ አርበኞችን ወላጆች፣ ወንድሞች እና እህቶች እየያዙ ማሰር ጀምረዋል፡፡
ከሐሙስ ዕለት አንስቶ ደግሞ ምስላቸው በኢንተርኔት ለህዝብ ተሰራጭቶ በህዝብ እና በአገር ላያ የፈፀሙት ክህደትና ግፍ የተጋለጠባቸው የህወሓት ጆሮ ጠቢዎች ብስጭታቸው ንሮ አፈናውንና እስሩን አበርትተውታል፡፡ ከዕረቡ ሌሊት ጀምሮ በወቁጥጥር ስር የዋሉት በርካታ ወጣቶች በዛሬው ዕለት ወደ አዲስ አበባ /ማዕከላዊ እስር ቤት/ ተግዘዋል፡፡
በህወሓት ዘረኛ ቡድን ደህንነቶችና ፌደራል ፖሊሶች ታፍነው ወደ አዲስ አበባ /ማዕከላዊ/ ከተወሰዱት በርካታ የአርባ ምንጭ ወጣቶች መካከል
• ሉሉ መሰለ /የሰማያዊ ፓርቲ አባል/
• ዓለም ክንፉ /የሰማያዊ ፓርቲ አባል/
• ጨንቾ
• ያደርጋል
• ደረጀ
• ውብሸት ጌታቸው... የተባሉት ይገኙበታል





No comments:

Post a Comment