Friday, October 16, 2015

የዞን 9 ጦማሪዎች ሶሊያና ሽመልስ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፉ ብርሃኔ፣ እና አቤል ዋበላ ነፃ ተባሉ * ጦማሪ በፈቃዱ ኃይሉ ክሱ ተቀይሮ ይከላከል ተባለ -

Soliana Shimeles zehabeshaየፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በዞን 9 ጦማሪዎች ላይ ውሳኔ ለመስጠት ዛሬ በተሰየመው ችሎት በሌለችበት በሽብር ወንጀል ተከሳ የነበረችውን ጦማሪት ሶልያና ሽመልስ የቀረበባትን ክስ መከላከል ሳያስፈልጋት በነፃ እንድትሰናበት ወሰነ::
አሁን በደረሰን ዜና ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፉ ብርሃኔ፣ እና አቤል ዋብላ መከላከል ሳይጠበቅባቸው በነፃ እንዲሰናበቱ ተወስኗል:: እንዲሁም ጦማሪ በፈቃዱ ሃይሉ አንቀጹ ተቀይሮ እንዲከላከልና የዋስ መብቱ ተጠብቆ እንዲከላከል ተወስኖበታል::
የዞን ዘጠኝ አባል የሆኑትና በሽብር ወንጀል ተከሰው እስር ላይ ከነበሩት 10 ጦማሪዎች መካከል አምስቱ ከዚህ ቀደም በነፃ መለቀቃቸው ይታወሳል::
ከሶሊያና ሽመልስ በስተቀር ዛሬ በነፃ የተሰናበቱት የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች 541 ቀናት እስር ቤት ቆይተዋል::

- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/47453#sthash.OqdB8CAN.dpufZONE 9

No comments:

Post a Comment