አባይ ሚዲያ ዜና
ናትናኤል ኃይለማርያም
የአርበኞች ግንቦት ሰባትሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ለመከላከያ ሰራዊት አባላት፣የፌደራለ እና የክልል ፖሊስ አባላት፤ለአጋዚ ልዩ ጦር አባላት እና ለሌሎች ስርአቱ ታጣቂዎች ያደረጉት ጥሪ በሰራዊቱ ዉስጥ ከፍተኛ መነጋገሪያ ከመሆኑም በተጨማሪ ሰራዊቱ ከህዝብ ጋር ለመቆም የመጨረሻ ዉሳኔ ላይ እንዲደርስ ያደረገዉ ጥሪ ነዉ ሲሉ እነዚሁ ምንጮች ጠቅሰዋል።የተደረገዉን ጥሪ መቀበላቸዉን ለማመላከት ሀሳባቸዉን የገለጹት የሰራዊቱ አባላት እንዳሉት “ መከላከያዉ የህዝብ ሳይሆን የህዉሀት ቡድን አገልጋይ እየሆነ መምጣቱን ሙሉ በሙሉ ያወቁበት ደረጃ ላይ መድረሳቸዉን እና ሊቀመንበሩ እንዳሉት ሰራዊቱ የቁም እስረኛ ሲሆን በተለይ ህዝባዊ እምቢተኝነቱ ከተጀመረ ጀምሮ ምን እንደሚያደርግ እና ወዴት እንደሚሄድ የጠራ አቅጣጫ ባለማግኘቱ እና ባለበት ከፍተኛ ጫና የተነሳ አማራጭ በማጣት በሰራዊቱ ዉስጥ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
አክለዉም በአሁኑ ሰአት አዛዦቻቸዉ ድንጋጤ ዉስጥ ከመሆናቸዉ የተነሳ በሰራዊቱ ላይ ያለዉ ቁጥጥር እና ማስጠንቀቂያ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን እንዲሁም ከአንድ ብሄር የሆኑ አባላት ባንድ ላይ ለግዳጅም ሆነ ለስምሪት እንደማይመደቡና በግል ህይወታቸዉ ዉስጥ ስለላን እያካሄዱ ነጻነታቸዉን ፍጹም እንደነጠቋቸዉም ገልጸዋል፡፤በዚህም ምክንያት ከሰራዊቱ መካከል ያሉ አንዳንድ አድር ባይ አባላትን ሳይቀር የሕዉሐት ገደብ ያለፈ ጥርጥር ወደተቃዋሚነት ስለለወጣቸዉ በአሁኑ ሰአት በጥቂት ቁጥር ከሚቆጠሩ የግል ሰዎቻቸዉ በቀር ሰራዊቱ ልቡ ከህዝብ ጎን ሆኗል ብለዋል፡፤ በየጊዜዉ ለግዳጅ ሲወጡ ወደነጻነት ታጋዮች ከነትጥቃቸዉ የሚቀላቀሉ እና በቡድን በመደራጀት በየጫካዉ የሚመሸጉ የሰራዊት አባላት ቁጥር ከቀን ወደቀን እየጨመረ መምጣቱንም አመልክተዋል።
ፕሮፈሰር ብርሀኑ ነጋ ለሰራዊቱ ያደረጉትን ጥሪ በርካታ ሰዎች ለዉጥ የሚያመጣ ጥሪ መሆኑን በመግለጽ እነሱን ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ መከላከያ ሰራዊቱ ወገኑ ላይ መተኮስ እንዲያቆም እና የመሳሪያ ነጠቃን እና በ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሰበብ የሚደረግባቸዉን የጅምላ አፈሳ እንዲሁም ግድያ በመቃወም ወደጫካ ከገቡ ወጣቶች እና አርሶ አደሮች እንዲቀላቀል ጥሪ አቅርበዉ፤ ከሳምንታት በፊት በፍኖተ ሰላም ከተማ 18 የመከላከያ ሰራዊቶች እና አራት ያጋዚ አባላት ሰራዊቱን ከድተዉ መዉጣታቸዉን አስታዉሰዋል።በተለይ በአማራ ክልል አገዛዙ በስፋት ለማከናወን አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ያለበትን የመሳሪያ ነጠቃ ሽሽት ወደየጫካዎች በመግባት ላይ ያለዉ ህብረተሰብ እየጨመረ መምጣቱን እና የኮማንድ ፖስት አባላት ወጣቶችን ያለምንም ምክንያት ስለሚያስሩዋቸዉ በፍኖተ ሰላም በከተማዋ ዉስጥ አዛዉንቶች፤ሴቶች እና ህጻናት ብቻ እየቀሩ እንደሆነ ገልጸዋል።
በተያያዘ ዜናም በባህር ዳር ከተማ ከስድስት ሳምንት በፊት ወቶ የነበረዉና መመዘኛዉ ከ10ኛ ክፍል በላይ የነበረዉ የመከላከያ ምዝገባ ፤ተመዝጋቢ በማጣቱ ምክንያት ማስታወቂያዉ ከወጣ ከሁለት ሳምንት በሗላ መስፈርቱ ወደ 6ተኛ ክፍል ዝቅ ብሎም ባለመሳካቱ በአሁኑ ሰአት ወጣቶች ወደ መከላከያ ቢገቡ ጥቅማጥቅሞችን እንደሚያገኙ ዉስጥ ዉስጡን በቅስቀሳ መልክ እየተወራ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ይህ በእንዲ እንዳለ የክልሉ አየር መንገድ ለአዉሮፕላን አብራሪነት እና ለቴክኒሺያንነት የቅጥር ማስታወቂያ ማዉጣቱን ተከትሎ ምናልባት በስራ አጥነት ሲሰቃይ የከረመዉን ወጣት በዚ መልክ በመመዝገብ ወደመከላከያ ስለጠና ሊወስዱት ይችላሉ የሚል ስጋት እንዳላቸዉም ጠቁመዋል። የህዋት መንግስት ለመከላከያ እና ለፖሊስ አባላት መላቀቂያም ሆነ ፈቃድ መጠየቅ እንደማይቻል ቢያስተላልፍም እየከዱ እና እየጠፉ በሚለቁ አባላት ምክንያት አለመተማመን የመጣዉን የሰራዊቱን ቁጥር ለመጨመር በሰበብ አስባቡ በቁጥጥር ስር ያዋላቸዉን ወጣቶች በማባባል እና በማስገደድ ወደ ስልጠና ለማስገባት ሙከራ እያረገ ይገኛል ሲሉም ተደማጠዋል።
ከአመት በፊት ጀምሮ ሰራዊቱን እየለቀቁ የሚሄዱ አባላት ቁጥር በተለይ ህዝባዊ ትግሉ ከተጀመረ በሁዋላ በመጨመሩ፤የህዋት መንግስት በየክልሉ የመከላከያ ሰራዊትነት ምዝገባን ለማካሄድ ከጥሩ የደሞዝ ክፍያ ጋር ጥሪ ቢያደርግም የሚመዘገብለት ማጣቱ በሌሎች አስገዳጅ መንገዶች ወጣቶችን በማታለል በግዳጅ ወደ መከላከያ ያስገባበት ሁኔታ መኖሩን ሲዘገብ መቆየቱ ይታወሳል።
No comments:
Post a Comment