Saturday, October 22, 2016

የአሜሪካ መንግስት ተወካዮች ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ተወያዬ:: በጉዳዩ ላይ ሠኞ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል


U.S. State Department (Photo by Alex Wong/Getty Images)WASHINGTON, DC - SEPTEMBER 12:  A sign stand outside the U.S. State Department September 12, 2012 in Washington, DC. U.S. Ambassador to Libya J. Christopher Stevens and three other Americans were killed in an attack on the U.S. Consulate in Benghazi, Libya.  (Photo by Alex Wong/Getty Images)
የአሜሪካ መንግስት ተወካዮች ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ዛሬ ረፋድ ሲወያዬ አርፍደዋል፡፡ በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የኢህአዴግ አባል ስለጉዳዩ እንደገለፁልኝ ከሆነ በአሜሪካዋ አምባሳደር ፓትሪሽያ ኃስላች ሰብሳቢነት በተካሄደው በዚህ ውይይት ላይ ከኢህአዴግ በኩል አቶ በረከት ስምኦን፣ አቶ ደብረፅዮን፣ አቶ ስብሃት ነጋ፣ አቶ ደመቀ መኮንን እና ሌሎችም የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን የተወሰኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና የተለያዩ የሲቪል ተቋማት አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ስብሰባው በዋነኝነት ባለፉት ሁለት ዓመታት በኢትዮጵያ በተከሰቱ ህዝባዊ ተቃውሞዎች ዙሪያ ሲሆን ስለጉዳዩ የመንግ
ስት ባለስልጣናት ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ችግራቸውንም ለመቅረፍ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ ውይይቱን ይመሩት የነበሩት አምባሳደር ፓትሪሽያ ኃስላች እንደተናገሩት ከሆነ የኢትዮጵያ መንግስት ያለአግባብ ያሰራቸውን እስረኞች መፍታት እንዳለበት ብሎም በሀገር ቤት ከሚገኙት የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች በተለይም በርካታ ደጋፊ ካላቸው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ፣ መኢአድ እና ሰማያዊ ፓርቲ በጋራ መስራት ብሎም ሁሉንም ያሳተፈ ፖለቲካዊ ስርዓት መገንባት እንዳለበት የገለፁ ሲሆን ፍርድ ቤቶች፣ ምርጫ ቦርድና ሲቪል ተቋማት ከመንግስት ጫና ውጭ ሆነው ገለልተኛ በሆነ መልኩ እንደአዲስ እንዲዋቀሩ ተናግረው የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ የተረጋጋ መንግስት እንዲፈጠር እንደሚፈልግ ገልፀዋል፡፡
በውይይቱ ላይ የተገኙት ግለሰብ ጨምረው እንደገለፁት ውይይቱ የአንድ ወገን የበላይነት የታየበት ከመሆኑም በላይ ስብሰባው ከውይይት በላይ የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ እንዲሆን የሚፈልገውን ብቻ የገለፀበት የነበረ ሲሆን በመጪው ሐሙስ በዚሁ የአሜሪካ ኤምባሲ ኬነዲ ሆል የኢህአዴግ፣ የኦፌኮ፣ የሰማያዊና የመኢአድ አመራሮች በተገኙበት ተጨማሪ ውይይት እንደሚካሄድም ታውቋል፡፡ በጉዳዩ ላይ ሠኞ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

No comments:

Post a Comment