Wednesday, October 19, 2016

ሰበር ዜና፤ #AmharaResistance;


Muluken Tesfaw
በጎንደር ዙሪያ ወረዳ አቶ ዘመነ ምሕረትን ጨምሮ በ78 ሰዎች ላይ የማደኛና ግድያ ትዕዛዝ ወጣ፤
የመኢአድ ምክትል ፕሬዝዳንትና የሰሜን ምዕራብ ቀጠና ኃላፊ የነበረውና በቅርቡ ከወራት ስቅይት በኋላ ከእስር የተፈታውን አቶ ዘመነ ምሕረትን ጨምሮ 78 በሚሆኑ የጎንደር ዙሪያ ወጣቶች ማደኛ መውጣቱን ዛሬ ሰምተናል፡፡ እነ ዘመነ ምሕረት ላይ የወጣው ማደኛ ግለሰቦቹን መያዝ ካልተቻለም በተገኙበት እንዲገደሉም ትዕዛዝ መሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ 
ከጎንደር አካባቢ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ከአቶ ዘመነ ምሕረት ጋር በተፈላጊነት ስማቸው ከወጣው ዐማሮች መካከል 18ቱ የብአዴን አባላትና በአመራርነትም ላይ የነበሩ ናቸው ተብሏል፡፡ 
አቶ ማሙሸት አማረን እና አቶ አብርሃም ጌጡን ጨምሮ የመኢአድ ሕጋዊ አመራሮች በተለያየ ጊዜ ታስረው የተሰቃዩ ሲሆን በቅርቡም ብዙ የፓርቲው አባላት በእስር ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ከቀናት በፊት አቶ ጫኔ ዘየደ እና አቶ ኢዮብ ታስረው መፈታታቸው ይታወቃል፡፡ 
በተያያዘ ዜና ደግሞ በወገራ፣ በበለሳና አርማጭሆ አካባቢ ያሉ የዐማራ ገበሬዎችን ይቅርታ አድርገንላችኋል በሚል ትጥቃቸውን ለመቀማት አዲስ ስትራቴጂ መነደፉን ሰምተናል፡፡ መረጃውን ያቀበሉን ሰዎች እንደሚሉት ገበሬዎቹ ይቅርታውን ከተቀበሉ ለተሀድሶ በሚል ሰበብ ወደ ብር ሸለቆ ወስዶ ለማሰር እቅድ መኖሩን ጭምር ነግረውናል፡፡

No comments:

Post a Comment