(ዘ-ሐበሻ) ንብረትነቱ የሼህ መሐመድ አላሙዲን እና የወ/ሮ አዜብ መስፍን ንብረት እንደሆነ የሚነገርለት ጉመሮ ሻይ መውደሙ ተሰማ::http://www.zehabesha.com/amharic/archives/67311
የኢሉባቦር አሌ ወረዳ ነዋሪዎች፥ በወረዳቸዉ ከሚገኘዉ ከጉመሮ ሻይ ፋብሪካ፥ በቂ ጥቅም እያገኘን አይደለም ሲሉ ቅሬታቸዉን ባለፈው ግንቦት ወር ማሰማታቸው ይታወሳል:: ነዋሪዎቹ በተለይ ፋብሪካዉ የሰዉ ኃይል ሲቀጥር በቂ ዕድል ለአካባቢዉ ነዋሪዎች እንደማይሰጥና የአዜብ መስፍን ዘመዶችና የዘር ሀረጓ ብቻ እየተመረጠ ይቀጠራል ሲሉ በተደጋጋሚ ሲቃወሙ ነበር::
የጉመሮ ሻይ ልማት ድርጅት በሚድሮክ ኢትዮጵያ የሚተዳደር የግል የሻይ ፋብሪካ ነው ቢባልም የአቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ አዜብ መስፍንም ባለቤትነት አላቨው:: በዊኪሊክስ የተለቆ የነበረው መረጃ እንደሚያስረዳው ወ/ሮ አዜብና አላሙዲ ይህንን ትልቅ ኩባንያው በ 24ሚሊዮን ዶላር ነው የገዙት:: ገንዘቡን ለመንግስት ይክፈሉ አይክፈሉ ግን የሚታወቅ ነገር የለም::
ባለፈው ሳምንት የ እሬቻን በዓል ተከትሎ ከ500 በላይ ሰዎች በሕወሓት መንግስት መገደላቸውን ተከትሎ ሕዝብ ባስነሳው ተቃውሞ በኤሊባቡር አሌ የሚገኘው ይሄው ጉመሮ ሻይ ዛሬ መንደዱ ተገልጿል:: ጉመሮ ሻይ ባለፈው ግንቦት ወር ላይም በተመሳሳይ በ እርሻው ላይ ቃጠሉ ደርሶበት የነበረ ሲሆን የዛሬው ግን የከፋ ነው ተብሏል::
No comments:
Post a Comment