Saturday, October 22, 2016

ይቅርታን ከእምየው ❖❖❖


- አጼ ምኒልክ ከመቅደላ ወጥተው ወደ አንኮበር ሊገቡ ሲሉ የሸዋ ገዥ የነበረው
አቶ በዛብህ አይገቡም ብሎ ተዋጋቸው፡፡ አጼ ምኒልክም ድል
አርገውት አንኮበር ከገቡ በኋላ ሁሉን ረስተው ለአቶ በዛብህ
ይቅርታ አደረጉለት፡፡
- አጼ ምኒልክ ከጎጃሙ ንጉሥ ተክለሃይማኖት ጋር ስለተጋጩ
እንባቦ በሚባል ቦታ ጦርነት አድርገው የምኒልክ ጦር አሸነፈ
አጼ ምኒልክም በጦርነቱ የተጎዱትን ንጉሥ ተክለሃይማኖትን
በመንከባከብ እንኳን ተረፉ እያሉ ቁስላቸውን በማከም ይቅር
ተባብለው መልካም ወዳጅ ሆኑ፡፡
❖❖
- አጼ ምኒልክ ወደ ሐረርጌ ለጦርነት በሄዱ ጊዜ ራስ ጎበና
በአዲስ አበባ ሆነው መንግስት ሊገለብጡ ነበር ተበለው
ተከሰሱ በመኳንንቱም ዘንድ ጥፋተኛ ተብለው ሞት ተፈረደባቸው፡፡
አጼ ምኒልክም የሞት ፍርዱን እንዲያፀኑ ሲጠየቁ"ጎበናን እዚህ
ለማድረስ ሰላሳ ዓመት ፈጅቶብኛል ለአንድ ቀን ጥፋቱ ብዬ
የሰላሳ ዓመት ድካሜን አላበላሽም ምሬዋለሁ እንደጥንቱ ይኑር"
ብለው ይቅርታ አደረጉ፡፡
❖❖
- ኢጣሊያዎች በመቀሌ ጠንካራ ምሽግ ሠርተው ከባድ ውጊያ
በሚያረጉ ጊዜ ለውሃ ይጠቀሙበት የነበረውን ወንዝ የኢትዮጵያ
ሰራዊት በመቆጣጠሩ ኢጣሊያዎቹ በዛው በምሽጋቸው እንዳሉ
በውሃ ጥም ማለቅ ጀምሩ ፡፡አጼ ምኒልክም ሁሉንም እዛው
መጨረስ ሲችሉ ሠላሳ በርሜል ውሃ እና የሚጓጓዙበት በቆሎ
ጭምር ሰጥተዋቸው በይቅርታ ሸኞቸው፡፡
❖❖
- ታላቁን የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ሰራዊት ድል ማረጉን ተከትሎ
አጼ ምኒልክ የኢጣሊያን ምርኮኞች ላይ መከራ ያደርሳሉ ተብሎ
ሲጠበቅ አጼ ምኒልክ ግን ሁሉን ጠብቀው አቆይተው በሠላም፣
ወደ ሀገራቸው በመስደድ ይቅር ባይነትን ለዓለም አሳዩ፡፡
❖❖❖
የይቅርታ ቀን ይሁንልን!!!!..
የሺሀሳብ አበራ

No comments:

Post a Comment