Monday, October 31, 2016

ሲራጅ ፈርጌሳ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ተከትሎ የታሰሩትን ሰዎች ቁጥር ለመግለጽ ፈቃደኛ አይደሉም ኢሳት (ጥቅምት 21 ፥ 2009)


Bilderesultat for ሲራጅ ፈርጌሳበኢትዮጵያ የተደነገገውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተከትሎ የታሰሩ ሰዎችን ቁጥር ለመግለጽ የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተዘገበ።
የኮማንድ ፖስቱ ዋና ጸሃፊ ተደርገው የተሰየሙት የመከላከያ ሚኒስትሩ ሲራጅ ፈርጌሳ ዕሁድ በሰጡት መግለጫ፣ 2ሺህ ሰዎች ምክር ተሰጥቷቸው ተለቀዋል ቢሉም የታሰሩትን ቁጥር ለመገለጽ ግን ፈቃደኛ አለመሆናቸው ተመልክቷል።
በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ እምቢተኝነት ተከትሎ በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጅምላ አፈሳ የታሰሩ መሆኑ ይታወቃል።
በተለይም በመደበኛው የህግ ስርዓት ሃገሪቱን መምራት የተሳነው የህወሃት/ኢህአዴግ መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከደነገገ በኋላ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሰዎች በጅምላ እየታሰሩ መሆናቸው እንደቀጠለ ነው።
ባለፉት 10 ቀናት ብቻ 2ሺህ 6 መቶ ሰዎች መታሰራቸውን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።
በኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገጉን ተከትሎ የማህበራዊ ሚዲያና ሌሎች የኢንተርኔት ግንኙነቶች እገዳ እንደተጣለባቸው ይታወቃል።

No comments:

Post a Comment