Friday, January 13, 2017

ስለሁለገብ ትግል .ከዶ/ር ታደሰ ብሩ



Image may contain: 1 person, standingስለሁለገብ ትግል የተሟላ ግንዛቤ መኖሩ ትግላችንን የምናይበት መንገድ ያሰፋልናል ብዬ አምናለሁ። አንዳንዱ ሁሌ ስለ አንድ የትግል ስልት ብቻ መወራት ያለበት ይመስለዋል። ይህንን ሀሳብ ለማጥራት በግማሽ ገጽ ስለሁለገብ ትግል ለመግለጽ ልሞክር።
ሁለገብ ትግል ቢያንስ የሚከተሉት አምስት የትግል ስልቶች ድብልቅ ነው።
1. ሕዝባዊ ተቃውሞ (Civic Protest) አምባገነኑ ሥርዓት ያወጣቸው ህጎች የሚሰጡት ትናንሽ ክፍተቶችን በመጠቀም አቤቱታን ወይም ተቃውሞን በህጋዊ መንገድ ማቅረብ። ምሳሌዎች አቤቱቶታዎችን በጽሁፍ በኮሚቴዎች አማይነት ማቅረብ፣ ሰላማዊ ሰልፎች፣ የፊርማ ማሰባሰብ ዘመቻ,፣ ሕዝባዊ ስብሰባዎች፣ የአቋም መግለጫዎች ወዘተ ....
2. ሕዝባዊ እምቢተኝነት (Civic Disobedience) አምባገነኑ ሥርዓትን ያወጣቸው ህጎችን መጣስ የሚያስከፍለውን ዋጋ አውቆና ዋጋ ለመክፈል ተዘጋጅቶ የሚደረግ ህግን ጥሶ “አልገዛም፣ አልታዘዝም“ ማለት። ህግ አድርግ የሚለውን አለማድረግ፤ አታድርግ የሚለውን ማድረግ።
3. ሕዝባዊ አመጽ (Civic Resistance) አምባገነኑን ሥርዓት በመሣሪያ ኃይል ጭምር መገዳደር። ሕዝባዊ አመጽ ከሌላው አመጽ የሚለየው ሕዝብ “ጥሩ ወይም መልካም” ለሚለው ዓላማ የሚደረግ መሆኑ ነው - ይህ ነው civic ያሰኘው።
4. ሕዝባዊ አሻጥር (Civic Sabotage) አምባገነኑን ሥርዓት ከውስጥ ማዳከም፤ ሥራዎች እንዳይፋጠኑ፤ የሥርዓቱ ልዩ ልዩ ክፍሎች እርስ በርስ እንዳይስማሙ ማድረግ፤ ማሰልቸት ..
5. ሕዝባዊ ስለላ (Civic Intelligence) ሁሉም በያለበት ራሱን የመረጃ ሠራተኛ በማድረግ የአምባገነኑ ሥርዓት ተዋንያንን እግር ከእግር በመከታተል እርፍት መንሳት፣ መሰለል፣ ማሳሳት፣ የእነሱን ምስጢር ቆፍሮ ማውጣት፣ የወገን መረጃን ከእነሱ መደበቅ ...
የእነዚህ ስልቶች ሁሉ ድብልቅ ነው ሁለገብ ትግል የሚባለው።

No comments:

Post a Comment